Friday, December 31, 2010

በኢሜል ከደረሰን

ውሸታም ሰው ተፈጥሮው ነው። ተቀብሎ ውሸትን የሚያሟሙቀው ግን አደገኛ ነው።

ወድ አንባብያን በዚህ ጽሁፍ ብዙ ለማለት አልፈልግም። በቅርቡ ሰፋ ያለ በእውነት የተደገፈ  ማስረጃ በዳላስ ኢኦቲሲ ጦማር (DALLASEOTC.BLOG)ላይ በወዳጄ  በአቶ  ተኮላ መኮንን ላይ የተነዛውን በሬ ወለድ ጽሁፍ ወደ መጣበት ይመለስ ዘንድ ሙግቴን አቀርባለሁ። ለዛሬ ግን በዚህ በዳላስ ኢኦቲሲ በሚባል ጦማር ላይ የሚነዛው የውሸት ቧንቧ በተለይ ሰሞኑን በሃዘን ሁሉም የዳላስ ኢትዮጵያዊ ባዘነበት ሰሞን ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በጎደለው መንገድ ስለሃዘኑ የጻፉት ሲያሳዝነኝ ይባስ ብለው የውሸት ወሬ ተቀብለው ሲደልቁት ሳይ በዝምታ መታለፍ እነደሌለበት በማመኔ ትንሽ ለመጫር ተገደድኩኝ። ለማንኛውም በቅርቡ በሰፊው እመለስበታለሁ ለዛሬው ለሁላችሁም መልካም አዲስ አመት እያልኩ ከበሬ ወለደ ወሬኞች ያድነን እያልኩ እሰናበታችኋለሁ።


ደም መላሽ ደበበ
ከዳላስ
12/31/2010 4:00 ፒ መ




መከበር ላልፈለጉበተደጋሚ ለማስፈራራት በማሰብ የስድብ ውርጅብኝ በዳላስ ኢኦቲሲ ሲሰነዘርብኝ ቆይቷል። ሁሉንም በንቀት በማለፌ ዛሬ በሬ ወለደ አሉባልታ እየነዙ ይገኛሉ። ለተጻፈው ውሸት በዳስ የሚኖሩ ሳይቀር በብዛት የሕይወት ምስክሮች በአሜሪካ ስለሚገኙ ደንታም አይሰጠኝም። የውሸት ስም ማጥፋትና የአንድ ወር ማስጠን ቀቂያ ግን ሕጋዊ መብቴን መጋፋት በመሆኑ ቤተሰቤንና ሕይወቴን ለመጠበቅ የሚቻለኝን ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ተገድጃለሁ። መረዋ ባይኖር ኖሮ መተንፈሻ ቦታ አናገኝም ነበር።



From: TEKOLA MEKONEN Add to Contacts


To: Yetayal ewnetu





ለመረዋ ምስጋናዬ የላቀ ነው።



ተኮላ መኮንን

t.mekonen@verizon.net

Wednesday, December 29, 2010

በሐዘን የሚቀልድ ደካማ ሰው ብቻ ነው። ቁጥር ፶፬

ውድ የመረዋ አንባብያን ሰሞኑን የደረሰብን ሐዘን መሪር ነበር።  ሁሉም በወጣቱ ልጃችን በማትያስ ከበደ ብርሃኑ ሞት እጅጉን ለማዘኑ በወቅቱ ተሰብስቦ የነበረውን ምእመን ለቅሶ በማየት መገመት ይቻል ነበር። ወጣቶችና ሕጻናት ከመካከላቸው የተለየውን ጨቅላ ለመሰናበት ተሰብስበው የተናገሩትን ሁሉ ስናስታውስ ልጆቻችን ከኛ የተለየ አመለካከት፤ ከእኛ ዘንድ የራቀ ፍቅር እንዳላቸው አየንና በነሱ ተስፋ ተጽናናን። የቤተክርስቲያኑ መሪዎችም ልባቸው በሐዘኑ ተነክቶ የቤተክርስቲያኑን  አዳራሽ መፍቀዳቸውን ስናይ ደግሞ ሚካኤል ዋጋቸውን ይክፈላቸው እንዳልን ሁሉ በሐዘንም ፖለቲካ ሲጠቀሙ ማየታችን ግን አሳዝኖናል። ሊነበቡ የተዘጋጁትን ጽሑፎች እንዳይነበቡ  መከልከል አግባብ አልነበረም። ጽሑፉን ያዘጋጁትን ግለሰቦች ለመቅጣት በማሰብ ሃዘንተኛውን አብሮ መቅጣት በኛ አመለካከት ትክክል አልነበረም። አቶ አበበ ጤፉና አቶ ሙሉአለም ስለ ግለሰቦች ከመፍረዳቸው በፊት እራሳቸውን ቢያስተውሉ ኖሮ   እንደዚያ አይነት ውሳኔ ላይ ባልደረሱም ነበር።  ሰውን በፍቅር እንጂ በጥላቻ ማሸነፍ አይቻልም። ያም ሆነ ይህ ሐዘኑን ተወጣነው። በድጋሜ ዛሬም ለልጃችን ዘለዓለማያዊ እረፍትን ለወላጆቹ ጽናትን ለቤተሰብና ጓደኛ ብርታትን እንለምናለን።

በዚሁ ባለፈው ሳምንት ለብዙ ጊዜ አብረውን የነበሩ እናታችን ወይዘሮ ሰናይት ኃይሌም ከመካከላችን ተለይተውናል። ከጅምሩ የዚህ ቤተክርስቲያን መስራች የነበሩት ወይዘሮ ሰናይት ኃይሌ ለዳላስ ሚካኤል ያበረከቱት አስተዋጽኦ ቀላል አልነበረም። ልጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጭምር ለሚካኤል እድገት አስተዋጽኦ ያደረጉ ግለሰቦች ሥም ሲጠራ የመጀመሪያውን ስፍራ እንደሚይዙ የማይስማማ  ግለሰብ ቢኖር የቤተክርስቲያናችንን ታሪክ የማያውቅ ወደ ከተማችን በቅርቡ ጎራ ያለ ብቻ ይሆናል።  ለወይዘሮ ሰናይት መንግስተ ሰማያትን ለልጆቻቸውና ቤተሰባቸው  መጽናናትን መረዋ  እየተመኘ፡ የሐዘናቸው ተካፋይ እንደሆነም  ይገልጻል።

ይህንን ካልን ዘንዳ፡

በዛሬው እለት የምናስነብባችሁ የዳላስ ምእመን በመላ በሐዘን ላይ እያለን የቦርድ ደጋፊዎች ነን የሚለው ጦማር (BLOGS)በገጹ ላይ የለጠፈውን ጽሑፍ ነው። ጽሑፉን እንዳለ ገልብጠን ለአንባብያን አቅርበነዋል። ከዚህ በታች ያለውን አንብቡና ፍቀር እምነት እያሉ የሚሰብኩን አስመሳዮች ለሐዘን ደንታ የሌላቸው ፈሪሃ እግዚአብሔር የራቃቸው ለመሆናቸው ምስክር የሆነውን ብእራቸውን እዩላቸው።እኛ ባባላቸው ካዘንን በ ድርጊታቸው ከተጸጸትንላቸው ቆየን። የጻፉት ጽሑፍ ከዚህ በታች አቅርበንላችኋል መልካም ንባብ። 
[Post a Comment On: Dallaseotc"የተጀመረው መሻሻል ከግቡ እንዲደርስ"




2 Comments - Show Original Post

በጎረቤታችን ላይ የተንኮል ተግባር ከመፈጸማችን በፊት በአምላክ ፊት ምን እንደሚጠብቀን አስቀድመን ብናውቅ ሁላችንም የመጀመሪያውን ድንጋይ ለመወርወር ባልቃጣን ነበር። በዚህ በያዝነው ሳምንት ውስጥ ፈጣሪያችን አምላካችን ለ ዳላስ አካባቢ የክርስቶስ አማኞችና የቅዱስ ሚካኤል ምእመን ብዙ ተአምር አሳይቶናል። እንድንጠነቀቅም ፊታችንንም ወደ ፈጣሪያችን እንድንመልስ ሊያደርገን ሁለት ተአምር አሳይቶናል። አንደኛው የቤተክርስቲያናችን አባል የሆነው ጸሃፊያችን የልቡን አይቶ ሃጢአት ውስጥ እንዳይገባና እንዳይረክስ መልአኩን በ ፖሊስ መልክ ልኮ ከ መጥፎ ተግባር እንዲድን አድርጎታል።




ባኳያውም የዚህን ግለሰብ ኅጢአት ከፖሊስ ሰነድ ውስጥ አውጥቶ በየታክሲያችን ላይ ሲበትንና ያገሩን ልጅ ስም ሲያጠፋ የነበረው ( ስሙን በደረሰበት አደጋ ምክንያት ለመጥቀስ በማንፈልገው ግለሰብ ) ላይ በደረሰው የአባት ሃጢአት ለልጅ በተላለፈ አደጋ ልጁን ያጣው ሰው የቅዱስ ሚካኤልን ደጀ ሰላም መጥናኛ እንዲሆን ያውም በትምህርት ቀን ያስፈቀደለት ማን ይመስላችኋል!


መድረኩን ማስፈቀድ ብቻ ሳይሆን ቀሳውስቱና ዲያቆናት እንዲተባበሩ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረገው ሰው ነው። አሱም ፤በ እኔ ላይ የራሱን ጉድ ደብቆ ልጆቹን በትኖ ብህግ ያገባት ሚስቱን የልጆቹን እናት


ጥሎ ወደ ሴተኛ አዳሪ ቤት የገባ ሰው የኔን ሃጢአት እያጋነነ ለጠላት ስለሰጠብኝ ብሎ አልተቀየመውም። ይሄን ያልነው እኛ ጉዱን የምናውቅ ነን። ይልቅስ በማያውቀው ሓጢአት ዉስጥ ገብቶ ልጁን ማጣቱ አሳዝኖት እንደማንኛችንም ሲያለቅስ አምሽቷል። ታዲያ እኛ እን ማን ሆነን ነው የቅዱስ ሚካኤልን ሥራ ነገ በኛ ላይ የሚደርሰውን አዉቀን የሰው ስም ለማጥፋትና በሃሰት ሰው ለመክሰስ እምንመኘው።


ለዚህ ነው ነገ የሚደርስብንን ብናውቅ ዛሬ እማጥ ውስጥ አንገባም ነበር ያልኩት። በሰው ላይ ተንኮል ለመስራት አንሯሯጥ ሰው ባያውቅብን እግዚአቤሔር ያውቀዋልና፤ ከሱ የሚሸሸግ ነገር እንደሌለ እንወቅ።


አሜን;






December 18, 2010 1:52 PM]

ይህ የኛ ሳይሆን የአስተያየት ሰጭዎች ነው ሊሏችሁ ይነሱ ይሆናል። እውነቱ ግን እነሱ አንብበው ያጸደቁት ብቻ እንደሚወጣ እራሳቸው የሚክዱ ካለመሆኑም በላይ በጦማራቸው BLOGS በአስተያየት መስጫ አምዳቸው በግልጽ ሃላፊነት እንደሚወስዱበት አንብበው እንደሚለጥፉት የተጻፈ ነው። 
እነዚህ ከሆኑ የእምነት ሰዎች በእውነት ብዙ የሚያነጋግረን ጉዳይ አለን። እነዚህ ከሆኑ የመሪዎቻችን ደጋፊዎች ወንድሞቼ ቤታችንን ለማፍረስ ትልቅ ትግል እየተካሄደ ነው። እነዚህ ከሆኑ የቤተክርስቲያናችን አንጋፋዎች ቤተክርስቲያናችን ሽማግሌ የለበትም የሚያሰኝ ነው። ይህ ከሆነ ሐዘንተኛን ማጽናናት ወንድሞቼ ለእናንተው ፍርዱን እንተዋለን። በባህላችን ከምንም በላይ ሃዘንን እናከብራለን። ያንን የማይቀበል ስለሐዘን ደንታ  የሌለው ብቻ  ነው። በመሳደብ ለወጥ ሲመጣ አላየንም። በማስፈራራት ደግሞ ፍቅር አይገነባም።   

የሳምንት ሰው ይበለን።

Saturday, December 18, 2010

ለጭቅጭቅም ለሐዘንም ጊዜ መምረጥ የተገባ ነው። ፶፫

ውድ አንባብያን

ሰሞኑን ያጋጠመን ሐዘን በጣም የከፋ ነው። ሐዘኑን የከፋ  የሚያደርገው ቆመን ያዋለድነውን ማቲው ሃይሌን እድገቱን ሳይጨርስ ቆመን ለመቅበር በመነሳታችን ነው።  ማቲውን ስናስብ ልጃችን ነውና  ልጆቻችን ይታዩናል። ማቲውን ስናስብ የዓለማዊ ሽኩቻችን የእድሜ ገደብ እንደሌለን አድርገን የምናስበውን  እንደገና እንድንመረምር ይገፋናል። ስለሆነም መረዋ የዚህን ከመካከላችን የተወለደውን በጨቅላ  እድሜ የተቀጨውን ወጣት ዜና እረፍት ምክንያት በማድረግ አስከሬኑ ግብአተ  መሬት ሳያርፍ ምንም አይነት እትምት ላለማውጣት ወስኗል።

ለማቲው ደስታዊ ዘላለማዊ እረፍትን
ለቤተሰቡ መጽናናትን እንመኛለን

በዚህ አጋጣሚ በነገው እለት በቅዱስ ሚካኤል አስተባባሪ ኮሚቴ ተጠርቶ የነበረው የምእመናን  ስብሰባም በሐዘኑ ምክንያት ለሚመጣው ወር አጋማሽ መተላለፉን ከኮሚቴው የወጣው መግለጫ አስታውቋል። በበለጠ ለመረዳት የምትፈልጉ የኮሚቴውን ጦማር በመጎብኘት መረዳት ትችላላችሁ።


የሳምንት ሰው ይበለን

Monday, December 13, 2010

የተደናቀፈ ሰው አጠገቡ ያለውን ይዞ ይወድቃል ቁጥር ፶፪

ቴክሳሶች አንድ መኪና ላይ የሚለጠፍ መፈክር አላቸው። IF YOU GO TO HELL DON'T BLAME IT ON JESUS  "ሲኦል ብትገባ በክርስቶስ አታመካኝ" የሚል ነው። ወደ ገሃነም እንዳትገባ ክርስቶስ ላንተና ለኔ ሐጥያት ደሙን እስከማፍሰስ ደርሷልና  ማለታቸውም ነው። ታዲያ

ለሠራንው ምስጋና እንደምንቀበል ሁሉ  ለጥፋታችንም ሃላፊነት መውሰድ ካልቻልን ደካሞች ነን።
ስለሌላ ሰው ድክመት ማውራት ቀላል ነው ስለራስ ድክመት መናገር ግን ቆራጥነትን ይጠይቃል።
ሰው ያልዘራውን አያጭድም።
አለማወቅን መቀበል አዋቂነት ነው።
በንስሐ የማያምንን ሰው ቅስፈት አለ  ብሎ  ለማስተማር መሞከር የዋህነት ነው።

ውድ የመረዋ አንባብያን። የቤተክርስቲያናችን ችግር እየባሰ እንጂ እየተሻለው እንዳልመጣ ምስክሮቹ እናንተው ናችሁና መናገር አስፈላጊ አይመስለንም። ፍቅራችን የትሄደ? ብሎ ለጠየቀ አንድ ወንድም "አሁንስ ድሮም እንደነበር እየተጠራጠርኩ ነው።" ያሉት እናት ተስፋ ቆርጠው ለመናገራቸው ጠቋሚ አላስፈለገንም። እኚህ በየሳምንቱ በማዶው ጦማር ስማቸው እየተጠቀሰ የሚሰደቡትን አዛውንት ለመሆኑ ጥንካሬና ትእግስት ከየት አመጡ? ተብለው ሲጠየቁ ጠዋት ከምደግማት ውዳሴ  ማርያም  ማታ ከማነበው መጽሐፍ ቅዱስ ነዋ ልጄ ማለታቸውን የነገረን በቅርብ የሚያውቃቸው ጓደኛቸው ነው። ገንዘባቸውን ባፈሰሱ፤ ቀሳውስቶችን በረዱ፤ አበስ ገበርኩ ብለው ሥጋወደሙ በተቀበሉ የዚህ ቤተክርስቲያን አመራር ደጋፊዎች ነን ባዬች በየጦማሩ ሲያብጠለጥሏቸው፤ ከትዳራቸው ሊያፋቱ፡ ቤተሰባቸውን ሊበትኑ ሲዘምቱ "ፍቅር ብናሳያቸው እናሸንፋቸዋለን" ብለው ተሰዳቢው መልስ ሲሰጡ መስማት ላዳማጭ ውሸት ቢመስል ምን ይገርማል። ነገሩ ግን ባይገርማችሁ እውነት ነው።

የሰደቧቸው ሰዎች የሰደቡት ሁላችንንም ነው። የተሳደቡት የከተማውን አንጋፋዎች ነው። የተሳደቡት እራሳቸውን ነው። "ጎጃሜ ነኝ የሚለው ዘሩ ትግሬ የሆነ" ሲሉ የተባለው ግለሰብ የትግራይ ተወላጅ አለመሆኑን ስላወቅን ብቻ  ሳይሆን ቢሆንስ ከትግራይ መወለድ ሃጥያት ነውን? ብሎ  የሚጠይቃቸው ሰው የጠፋው ነገ  እኔን ደግሞ  ብናገር ያልተወልድኩበትን ሰፈር ይለጥፉብኛል ብሎ  በመስጋት ይመስለናል። ከተወሰነ ብሔር መወለድ ክብር የሚመስላቸው አሁንም ከዘር አረንቋ ውስጥ የተዋጡ ጊዜአቸው ያለፈባቸው ትምክህተኞች ብቻ  ናቸው።

ፖለቲከኛ ለመሆን እኮ እውቀትን ይጠይቃል።
ለዘረኝነት ግን መሃይምነት መፈልፈያ ቅርጫቱ ነው።

በዛሬው ምሽት የምስራች ይዘንላችሁ አልቀረብንም። የደሰታ መረዋ ልንመታ አልተነሳንም። የሃዘን ማቅም አላጠለቅንም። እንዳንናገረው እየፈራን እንዳንተወው እያናደደን ይዘንው ቀረብን እንጂ። ነገሩ እንዲህ ነው።

የሚካኤል ደብር አስተዳዳሪ ቦርድ ጸሐፊ የሆኑት አቶ  አበበ (ጤፉ) ባለፈው ዓርብ እለት ከፍርድ ቤት ውሎ ምሽት መሆኑ ነው: የመንገድ ሴትኛ አዳሪ ሲያነሱ ተገኝተው ታስረው እንደነበር የዳላስ ፖሊስ በድህረ ገጹ ላይ ከነፎቶግራፋቸው እንዳወጣ ተደውሎ  ሲነገረን ያልነው ነገር ቢኖር "ሚካኤል እውነትም ተቆጥቷል" የሚል ነበር። በተለይም ድርጊቱ ተፈጸመ  የተባለው በቀጠሮው ቀን መሆኑ ሁላችንንም ሳያስገርም አልቀረም። አቶ አበበ ዓርብ ታስረው እሑድ ከቤተክርስቲያን መጥተው የምእመናንን  ዓይን እያዩ  ማስታወቂያ መናገራቸው ቢገርመንም የሳምንቱ እሑድ ሳይደርስ የተከበረ  ቤተክርስቲያናችንን እንደተከበረ  እንዲኖር ባስቸኳይ ከሃላፊነታቸው እንዲለቁ መረዋ  ምክሩን ይለግሳል። የተደናቀፈ ሰው አጠገቡ ያለውን ይዞ ይወድቃልና፡ አብረው ያሉትም የቦርድ አባላት ሰላሙን ለመፍጠር በፈቃዳቸው ቢሰናበቱ ለሚመጣው ችግር መፍትሄ ይሆናል ብለን እናምናለን።

መረዋ ለአቶ  አበበ ጽናቱን እንዲሰጣቸው ይጸልያል።

ከፈተና ያድናችሁ።

Friday, December 10, 2010

የፍርድ ቤት ውሎ ቁጥር ፶፩

እንደምን ዋላችሁ

ከትላንትና ወደ ዛሬ  በዳኛው ጥያቄ  የተዛወረው የፍርድ ቤት ቀጠሮ በዛሬው  እለት ከሳሾችና ደጋፊዎቻቸው፤ ሰዎስት የቦርዱ "ሹማምንት" በተገኙበት ሲሰማ  ውሏል። በወቅቱ "ከሳሾቹ አባላት ባለመሆናቸው ብሎም ከዚህ በፊት በዚህ ፍርድ ቤት በከሳሽነት ቀርበው የተበየነባቸው በመሆኑ ክሱ ተደጋጋሚ ነውና ዛሬውኑ ተሰርዞ በነጻ አሰናብተን" ብለው ጉዳዩን ወደ ዳኛው ያመጡት የቦርዱ ጠበቆች ሲከራከሩ ስናይ  ባለፈው  እንደ ሰማነው እንጂ የተቀየረ  ነገር እንዳልነበረበት ለመታዘብ ችለናል። ከዚህ በፊት የነበረውን ክስ እንደማያውቁ የተናገሩት የከሳሾች ጠበቃ ዳኛው ከዚህ በፊት የወሰኑትና ይህ እሳቸው የመሰረቱት ክስ እንደማይመሳሰል ለዳኛው አስረድተዋል። በመሆኑም ዳኛው ባለፈው የወሰኑት ቦርዱ መተዳደሪያ ደንቡን መቀየር ይችላል አይችልም በሚል ላይ መሆኑን የጠቆሙት የከሳሾች ጠበቃ አንድም ቦታ መተዳደሪያ  ደንቡ ትክክል ነው ብለው ዳኛው እንዳልወሰኑ በተለይም የቦርዱ ምርጫ ሕገወጥ መሆኑን አስመልክቶ ምንም የተናገሩት እንደሌለ ጠቁመው የሳቸው ክርክር መሰረቱ የቦርድ አባላት ከሕግ ውጭ የተመረጡ በመሆኑ ይህንን በማስረጃ  አስመርኩዤ ለመከራከር የሚከለክለኝ ምንም ነገር ሊኖር አይችልም ብለዋል። ዳኛው በዚህ ጉዳይ ላይ ውሳኔ መስጠቴን የሚያሳይ መረጃ አላችሁ ወይ? ብለው የተከሳሾችን ጠበቆች ቢጠይቁም የቦርዱ ጠበቆች ሊያቀርቡ የቻሉት ባለፈው ክስ ላይ የድሮው ጠበቃ የተናገሩት ንግግር ብቻ ነበር። የቦርዱ ጠበቆች ያቀረቡትን ያለፈ የጠበቃ የመከራከሪያ ነጥብ ንግግር ዳኛው አንብበው ይህንን ሳይሆን እኔ የወሰንኩበትን ነው የምለው በማለት በድጋሜ ጠይቀው የተከሳሾች ጠበቆች ሊያቀርቡ አልቻሉም።

አባላት አይደሉም ለሚለው የከሳሽ ጠበቃ የቦርዱ አባላት ባወጡት የመተዳደሪያው ደንብ መሰረት የከሰሰ አባል መሆን አይችልም የሚል አንቀጽ እንዳለበት ሲናገሩ፤ ዳኛው እውነትክን ነው እሱን ነገር  እኔም አስታውሳለሁ በማለት ሲስቁ ተመልክተናል።

በተጨማሪም በሚመጣው 12/20/10 በቦርድ አባላት የይግባኝ ጥያቄ መሰረት በዚሁ ፍርድ ቤት ተቀጥሮ የነበረው ቀነ ቀጠሮ አስመልክቶ ወደ እረፍት በዚያን ወቅት እንደሚሄዱ ጠቅሰው እንዲቀየርላቸው የከሳሾች ጠበቃ የጠየቁትን ዳኛው በመቀበል ወደሚመጣው ወር ማለትም 1/20/11 ሲቀይሩት በ1/10/11 የነበረውም ቀጠሮ  እንዲሁ እንዲራዘም ዳኛው ተስማምተዋል። ይህም የሆነው የቦርድ አባላት የተጠየቁትን ጥያቄዎች መመለስ ይኖርባቸዋል ብለው ዳኛው እረዳት ዳኛቸው የበየኑትን ብይን ቢያጸኑት ካጸኑት በኋላ ቢያንስ 30ቀን እንደሚያስፈልጋቸው የከሳሾቹ ጠበቃ በመጠየቃቸው ነበር።  

በወቅቱ ቦርዱን በመወከል ዶክተር ግርማ አቶ  ዮሴፍ ከናባለቤታቸው አቶ አበበ ሲገኙ በታዛቢነት ደግሞ የአቶ አበራ ፊጣ ባለቤትና ወይዘሮ አባይነሽ አብረዋቸው እንደነበሩ አስተውለናል። ከከሳሾቹ ወገን ከሳሾቹ በሙሉ የተገኙ ሲሆን ደጋፊዎቻቸው ባንድ በኩል ተቀምጠው አስተውለናል። ከቦርድ ባለፈው ጊዜአቸውን ጨርሰው የወረዱ ግለሰብ ሳይቀር ሁኔታውን ለማዳመጥ መጥተው እንደነበርም ልንነግራችሁ  እንወዳለን።

በመጨረሻም የተከበሩት ዳኛ ለሁሉም መልካም ገና በመመኘት ውሳኔአቸውን  በሚመጣው ሳምንት እንደሚያስታውቁ ተናግረው የችሎቱ ፍጻሜ  ሆኗል። በስፍራው የተገኙት የመብት ትግሉ ደጋፊዎች ዳኛው ምንም አይነት ውሳኔ ይስጡ ትግሉ እንደማይቆም ቃል ሲገባቡ ለመመልከትም እድል ገጥሞናል።

መረዋ የፍርድ ቤቱ ብይን እንደደረሰው ብይኑን ለአንባብያን እንደሚያቀርብ ካሁኑ ቃል እየገባ በሚመጣው 12/19/10 በድሪምስ አዳራሽ በ1:00 PM ሁላችሁም እንድትገኙ ጥሪውን እንድናሰማ በመጠየቃችን ሁላችሁም ከቅዳሴ መልስ ወደዚያ እንድታመሩ ልናሳስባችሁ እንወዳለን።

እውነት ምን ጊዜም ያሸንፋል

ቸር ወሬ  ያሰማን።

Monday, December 6, 2010

ዘግይቶ የደረሰን

በሚመጣው ሐሙስ DECEMBER 9, 2010 ተቀጥሮ  የነበረው የፍርድ ቤታችን ቀጠሮ በዳኛው ጥያቄ መሰረት በማግስቱ ለ 12/10/2010 በ 9:00 ሰዓት መዛወሩን ዛሬ  ቀትር ላይ ለማወቅ ችለናል። ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ፈቃድ ጠይቃችሁ ሐሙስ እለት ፍርድ ቤት ለመገኘት ተዘጋጅታችሁ የነበራችሁ በሙሉ በተፈጠረው የቀጠሮ መጋጨት ከልብ እንደምታዝኑ ይገባናል። አሁንም የቻላችሁ ዓርብ እለት በተባለው ሰዓት በፍርድ ቤት   በመገኘት ለማዳመጥ ብትሞክሩ ምሥጋናችን የላቀ  ነው።

"ሰው ያስባል እግዚአብሔር ይፈጽማል"


Sunday, December 5, 2010

እምነት ያልገዛውን ቡድን ሕግ ያስተካክለዋል ቁጥር ፶

ቤተክርስቲያን እንዴት ይከሰሳል? የሚል ጥያቄ ለሁለት ዓመት ሲጠየቅ መቆየቱ የሚዘነጋ አይደለም።በተለያየ ወቅት ይህንን ጥያቄ አስመልክቶ ባጥጋቢ መልስ የተሰጠበት በመሆኑ ዛሬ በዚያ ላይ ጊዜ ማጥፋት አንፈልግም። እንዳዲስ ተነስተው "ቤተክርስቲያን እናት ነችና እናት እንዴት ትከሰሳለች?" እያሉ ለሚጠይቁ ግን ያገሩን ሕግ ካለማወቅ የመጣ ጥያቄ በመሆኑ እናት መከሰስ አይደለም የእናትነት ግዳጇን ካልተወጣች የእናትነት መብቷ ተገፎ ልጆቿን እንደምትነጠቅ መጠቆም እንወዳለን።ቤተክርስቲያንን እናስተዳድራለን ብለው በደል የሚፈጽሙትን ደግሞ ከመክሰስ ሌላ አማራጭ አይኖርም። አማራጭ ቢኖር በጉልበት መፋለም ይሆናል። ያንን ደግሞ እኛ አጥብቀን እንቃወማለን። በተራችን ለጠያቂዎቹ የምንጠይቃቸው ጥያቄ ግን  አለን። እምነት የማይገዛውን የአመራር ቡድን፤  ሽማግሌ የማያከብረውን የአመራር ቡድን ፤ አዛውንቶችን ለማናገር እንኳን ፈቃደኛ የማይሆንን የቦርድ ተመራጮች፤ የምእመናንን ፊርማ  ያዘለ የስብሰባ  ጥሪ አሽቀንጥሮ  የሚጥልን አንባ ገነን፤ ሕገ ወጥ አሰራሩን ማስቆም የሚቻለው እንዴት ነው ብለው ያስባሉ?

አባትና እናት እየበተኑ፡፡ ወላጆችን ከቤተክርስቲያን እያባረሩ። ልጆቹን እያስተማርን ነው ብለው ሲናገሩ አይቀፋቸውምን?የልጆች ነገር አይሆንልኝም የሚሉት አዛውንትስ የወላጆችን  መበተን  በጸጋ  መቀበላቸው ለምን ይሆን? የሚፈሩት ነገርስ ምንድነው? ይህ ባደባባይ የሚነገር ጥያቄ  ሆኖ እየሰማነው ነው።

ባለፈው ሳምንት ካህኑ "ልጆቼንና ባለቤቴን ሸጠህ ትምህርት ቤት አሰራ"  ብለውኛል ተብሎ ከመቅደስ ሲነገር ተገርመን ነበር። ቤተክርስቲያናችን የሰውን ልጅ መሸጥና መለወጥ የማትደግፍ መሆኗን አለማወቅም አስመስሏል።ነገሩ ለአባባል ተብሏል ሊባል ይችል ይሆናል። ነገር ግን የሚነገሩ ቀልዶች የሚያመጡት መዘዝ እንዳላቸው ማሳሰብ ፈልገን ነው። ያንን ማየት መረዳት ደግሞ የማመዛዘን እውቀትን ይጠይቃል።

ባለፈው እንደነገርናችሁ በአቶ ሰይፉ ይገዙ የሚመራ  የሽማግሌዎች ቡድን የአማራጭ አፈላላጊ ኮሚቴንና የቦርዱ ደጋፊዎች ነን የሚሉ ግለሰቦችን ማነጋገራቸው የሚታወስ ነው። የሽማግሌዎቹ ቡድን ይህንን ካደረገ  በኋላ  ከቦርዱ ጋር ቀጠሮ ይዘው በብዙ ውጣ ውረድ በቀጠሮው ቀን ሲሄዱ ለማነጋገር የጠበቃቸው ቦርዱ ብቻ  ሳይሆን የቦርዱ አጃቢዎች ጭምር ነበሩ። ሽማግሌዎቹ እኛ ልናነጋግር የመጣነው ቦርዱን ነውና አጃቢዎቹን አስወጡልን አላሉም። አብረው መወያየታቸውን ቀጠሉ እንጂ። የቦርዱም አባላት ከአጃቢዎቻቸው ውጭ ለመነጋገር ፈቃደኞች  አልነበሩም።ታዲያ ሽማግሌዎቹ ለመናገር ለምን ፈሩ?  ለሚለው አሁንም መልስ ያላገኘ በግልጽ መቅረብ ያለበት ጥያቄ  ይመስለናል። አቶ  ሰይፉን የተሳደቡት የቦርድ ተመራጭ ባለቤት በአቶ ሰይፉ አንደበት ሲወደሱ የሰማ ግለሰብ ጆሮውን አላምን ብሎ እጎኑ ያነበረውን ግለሰብ ምን እየተናገሩ ነው? ብሎ  እንደጠየቀ ሰምተን ተገርመን ነበር።

ለመሆኑ የቦርዱ አጃቢዎች እነማን ነበሩ

የኢንጅነሩ ተጠሪ  አቶ  አበበ
የቅንጅቱ            አቶ  ደጀኔ
የኢሕአፓው       አቶ  ከተማ
ቶውትራኩ           አቶ መሰለ እንደሚገኙበት ለማረጋገጥ ችለናል።

ሽማግሌዎችን ወክለው የተሰበሰቡት ደግሞ

አቶ  ሰይፉ ይገዙ
አቶ  በትሩ ወልደ አማኑኤል
አቶ  ጌታቸው ትርፌ  እንደ ነበሩም አረጋግጠን ነበር።

ስብሰባው እንደተጀመረ "የምን ብጥብጥ ነው ቤተክርስቲያናችን ሰላም ሰፍኗል" ያሉት የቦርድ ተመራጭ የግንዛቤ እንጂ የአካል እይታ ችግር እንደሌለባቸው ብናውቅም አባባላቸው አንድ ነገር አስታወሰን።

ለጥየቃ  ኢትዮጵያ ሄዶ የመጣ ግለሰብ ዘመዶቼ ደህና ናቸው ቢሆንም እናቴ አርፋለች። አባቴ እኔ እዛ ሄጄ በሚስቱ ሞት ደንግጦ ወደቀና ሞተ። እህቴ በቤተሰብ ሐዘን ተጎድታ አርባቸውን ሳታወጣ እንኳን አለፈች። የቀረ  ዘመድ የለኝም ያለውን ማለታችን ነው።

በስካር መንፈስ በየመጠጥ ቤቱ እደባደባለሁ እገላለሁ እያሉ የሚጋበዙት የቅንጅቱ  አቶ አበበ ዛሬ የትጥቅ ትግል ያሉበትን ያልያዙትን ጠመንጃቸውን  ጥለው መስቀል ይዘው ማየታችን ቢገርመንም ይህ ደግሞ ለመልካም ሆኖላቸው ከስካር ቢያድናቸው መልካም በሆነ ነበር። እንደ ቅንጅቱ ማሕተም የቤተክርስቲያኑን ማሕተም ለንግድ ማዋል ይቻላል ብለው በማሰብ ገብተው ከሆነ እንደማይሳካላቸው ካሁኑ ሊነገራቸው ይገባል።ለማንኛውም በዛሬው እለት በመለከት ጦማር ላይ የወጣው የሽማግሌዎችና የአማራጭ አፈላላጊ ኮሚቴ የመጨረሻ ስብሰባ ያረጋገጠልን ነገር ቢኖር ተመራጮቹ ሰላምን እንደማይፈልጉ ቀደም ብለን የተናገርነውን ማረጋገጡ ብቻ ነው። ሽማግሌዎቹ ካሁን በኋላ ያላቸው ምርጫ ቢኖር ብዙሃን ምእመንን ተቀላቅለው በሕግ መፋለሙን መቀጠል ብቻ ይሆናል። ካልሆነ ዝምታን እንመርጣለን ማለት ሳይመለስ ተንጠልጥሎ ያለውን ጥያቄ ይኸውም የሚያስፈራቸው ምንድነው? የሚለውን የሚቀሰቅስ ይሆናል። ዛሬ ያለው ምርጫ አንድ ነው። የተደፈረውን የምእመናን መብት በሕግ ማስከበር ብቻ ነው። እራሳቸው አውጥተነዋል የሚሉትን ሕግ እንኳን የማያከብሩ የቦርድ ተመራጮች ከዛሬ  ነገ ልባቸው ይራራል ብሎ የሚጠብቅ ካለ፡ የዝሆን ጆሮ አሁን ካሁን ይወድቅ ይሆናል ብሎ  እንደሚከተለው ጅብ አይነት መሆን ይመስለናል።

አቶ  አበበ ጤፉ
አቶ  አበራ ፊጣ
አቶ መሰለና
የቦርዱ ዶክተር ዘማሪ ሆነው መመረቃቸውን ስናይ መመረቅ የማይሰለቻቸው ዶክተር አላልንም ዳላስ በመሪነትና  በዘማሪነት የሚያቀርበው እነዚህን ብቻ ከሆነ  እውነትም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለነው አልን እንጂ።

ይህንን ቤተክርስቲያን ወደነበረበት ለመመለስ ብዙ የበኩላችንን ጥረናል። ታግሰናል። ሲሰድቡን አልተሳደብንም። ሲያስፈራሩን ፍርድ ቤት አልሄድንም። ሕይወታችን አደጋ ላይ እንደሆነ ሲነገረን ፈርተን አላፈገፈግንም። አሁንም የተረገጠ መብታችንን ሳናስከብር ወደኋላ አንልም። ለሽማግሌዎች ልንናገር የምንወደው ስለህጻናት ብዙ ተብሏልና የእኛም ልጆች ሕጻናት መሆናቸውን ነው። የእኛም ልጆች የኦርቶዶክስ ልጆች መሆናቸውን ነው። ወላጆችን አባሮ ልጆቹን እንፈልጋለን ማለት ደግሞ ሕዝብን ገድሎ  አገርን ማስቀረት አይነት መሆኑን እንዲገነዘቡትም እንወዳለን። ከስጋው ጦመኛ የሆነ  ሰው ከመረቁ አይከጅልምና።

በልጆች ስም መነገድ መቆም ይኖርበታል። የሁሉም ልጅ እኩል ነው ብለን እንቀበል።
አቋም ከሌለው ወዳጅ ይልቅ አቋሙ የሚታወቅ ጠላት ይከበራል።

በ DECEMBER 9 በፍርድ ቤት

በ DECEMBER  19 በተጠራው ስብሰባ ላይ ለመገኘት ተዘጋጁ።

በቸር ይግጠመን።

Thursday, November 25, 2010

መረዋ ዛሬ ዓመት ሞላው ቁጥር ፵፱

እነሆ መረዋ ከተመሰረት ዛሬ አንድ ዓመት ሞላው። ባለፈው እንዳልነው አሁንም እንኳን አደረሳችሁ እንላለን። ዓመት ማለፉን ከማስላት በስተቀር የተቀየረ ነገር ግን የለም። የሚገርመው የዛሬ ዓመት መረዋ የጻፈውን ስናነብ ዛሬ የተጻፈ መሰለን። አንባብያን እንድታነቡና እንድትፈርዱ የዛሬ ዓመቱን እትምት እንዳለ ከዚህ ጽሑፍ ግርጌ እናቀርብላችኋለን።
ዛሬ ዓመት ሞላን ብለን ሻማ አናበራም ሰላሙን ስጠን ብለን እንጂ።
የማንወዳቸውን አጥፋልን ብለን አንጠይቀውም ልቦናቸውን ክፈትላቸው  ብለን እንጂ። በሞቱ አንደሰትም፥ በታሰሩ ጮቤ አንረግጥም ከክፉ ሁሉ አድነን እንላለን እንጂ።
ትዝ ቢላችሁ የዛሬ ዓመት መረዋ ከሌላ ጎን የሚረጨውን የውሸት ወሬ ለመቋቋም ብሎም እውነተኛውን ዜና ለምእመናን ለማዳረስ ይህንን ጦማር ከፈተ። ጦማሩ በመከፈቱ  የተናደዱ ቢኖሩ እውነት መስማት የሚያስፈራቸው በስድብ የተካኑ ስም በማጥፋት የነገሱ ምእመናንን  በትነው ቤተክርስቲያኑን ሳይሆን ንብረቱን እንካፈላለን ብለው የሚያልሙ ደካሞች ብቻ ናቸው። ይህ ደግሞ  ቅዠት ሆኖ ይቀራል እንጂ ሕልም እንኳን እንደማይሆን አሁንም ቃል እንገባላችኋለን። የኛ ጥንካሬና ጉልበት የሚካኤልና የምእመናን ድጋፍ ነውና። በድጋፋችሁ እዚህ ደርሰናል የምስራቹን አብረን እንደምንሰማ አሁንም አንጠራጠርም።

ለእምነት መሰደብ አይደለም መገደልም ያለ ነው። በዛኛው ብሎግ በወሲብ የተሰደባችሁ፤ ትዳራችሁ እንዲፈርስ የውሸት ወሬ የተነዛባችሁ። ሰላም ይፈጠር በማለታችሁ ከካህን ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት አላችሁ ተብሎ የተጻፈባችሁ። የከሰሱት እውነት አላችው በማለታችሁ የውሸት አሉባልታ የተነዛባችሁ። ቤታችሁ በድንጋይ የተደበደበ። መኪናችሁ የተሰበረ። ማስጠንቀቂያ በግለሰብ የደረሳችሁ። አገርቤት ያለው መንግሥት ሰላዬች ተብላችሁ የተወነጀላችሁ። የመንግሥት ግብር አልከፈላችሁም ተብላችሁ ማስፈራሪያ የደረሳችሁ። ሁሉ ዛሬ ከተሳዳቢዮቹ በላይ መሆናችሁን እንዳትጠራጠሩ። እዚህ አካባቢ የግለሰብ ሕይወት  ቢጠፋ ተጠያቂዎቹ ደግሞ የስድቡን ጦማር የሚያቀነባብሩት ግለሰቦች ለመሆናቸው ካሁኑ ማሳሰብ እንወዳለን። እኛ ግን እየተሰደብንም ማስፈራሪያ  እየደረሰንም ለመብታችን መታገላችንን  አናቆምም። እውነትን በመያዛችን ትላንት ከማዶ  የነበሩ ዛሬ ከብዙሃኑ እየተቀላቀሉ ነውና። በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ!!!!! 
DECEMBER 9, 2010
ባለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ሁላችሁም እንድትገኙ  ጥሪያችንን እያቀረብን።
የዛሬ  ዓመት የተጻፈውን መረዋ እንደገና እንድታነቡት እንጋብዛችሁ።

ይቅርታ የክርስቲያን ባህርይ ነው ቁጥር ፩


                                                                                                 Thursday, November 26, 2009

በዛሬው (THANKSGIVING) የፈጠረን አምላካችንን ተሰባስበን በምናመሰግንበት እለት፡የሰላም ንፋስ እንዲነፍስ፡ የፍቅር ዝናብ እንዲያካፋ፡ የይቅርታ ጥላ እን ዲያጠላብን መፀለይ የተገባ ከመሆንም አልፎ ክርስቲያናዊ ግዳጅችን መሆኑን መቀበል የግድ ይሏል። በቂም በቀል የሚመራ ክርስቲያን ከመሃከላችን ካየን በጸሎት በምክር መርዳትም እንደዚሁ ክርስቲያናዊ ግዳጃችን መሆን ይኖርበታል። እንዳንስማማ የተስማማን ይመስል በሁሉ ነገር ተጣልተን እስከመቼ እንዘልቃለን? ብለንም እራሳችንን ብንጠይቅ ምን አልባት ካንቀላፋንበት እንባንን ይሆናል። ውድ የቤተክርስቲያን አባላት በዛሬው የፈረንጆቹ በዓል እንድታደርጉ የምነጠይቃችሁ ነገር ቢኖር ሁላችሁም በቤተክርስቲያናችን የተከሰተውን መለያየትና መናቆር እንዲቆም በጸሎት እንድታስቡት ብቻ ነው። ከደጋፊና ከተቃዋሚ እየተባለ የሚጻፈውን የስድብ ውርጅብኝ፡ የቃላት ሽኩቻ አንብበናል። "መሳሪያ የታጠቀ ሁሉ ነፃ አውጭ ነው" ማለት ስህተት እንደሆነ ሁሉ፡ የተነገረው በሙሉ እውነት ነው ብሎ መቀበል የዋህነት ይሆናል። እያንዳንዳችን ምን እያደረግን ነው? ብለን እራሳችንን ብንጠይቅ ምንአልባትም የችግሩ መልስ በቀላሉ የሚገኝ ይመስለናል። "ሽማግሌዎች ቢኖሩ ኖሮ እዚህ አንደርስም ነበር" ለሚሉት እውነት አላችሁ እያልን፡ አባባላቸውን ስንጋራ፡ "አሁን ለምን ሽማግሌዎች ሊያስታርቁ ተነሱ" ብሎ መተቸትና መሰናክል ለመፍጠር መነሳት ግን ሌላ ስህተት ነው ብለን ደግሞ እናምናለን። በፍርድ ቤት ትእዛዝ ችግራችን ይፈታል ብሎ የሚያምን ካለ የዋህ ነው ብሎ መናገር ማስፈራት የለበትም። ፍርድ ቤት በሚሰጠው ብያኔ ፍቅር አይመጣም አንድነት አይፈጠርም። ይህ ሊሆን የሚችለው የተለያየ ሃሳብ ይዞ የሚከራከረው ቡድን ተቀምጦ መነጋገር ሲችል ብቻ ነው። ክስ የመሰረቱትን ለምን ክስ መሰረቱ ብሎ መኮነን ደግሞ ሲደረግ የነበረውን መካድ ይህንን ባያደርጉ ኖሮ ዛሬ እንደዚህ ለመናገር የማንችልበት ሁኔታ ላይ እንሆን እንደነበር አለመቀበል ይሆናል። የቤተክርስቲያን ገንዘብ ስላለ ከሳሾቹን ገንዘባቸውን አስጨርሰን እንዲሸነፉ እናደርጋለን የሚሉት የቤተክርስቲያኑ ተመራጮች ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር የተመኩበት ገንዘብ ከምእመናን የተዋጣ መሆኑን ነው። ምእመኑ ካልደገፈ የገንዘቡ ቌት እንደሚሟጠጥ ከሳሾችንም ከአሁኑ በበለጠ እየደጎሙ እየደገፉ እንዲቀጥሉ ሊያበረታቱ እንደሚችሉ ማሰብም የተገባ ነው። ከሳሶችም ሆኑ የቤተክርስቲያኑ ተመራጮች ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር ያለ ምእመን ድጋፍ የትም ሊሄዱ እንደማይሄችሉ ነው። በተናጠል ቤተክርስቲያን አይገነባምና። ተሰዳደብን፡ ተካሰስን፡ ተወነጃጅለን አሁን ደግሞ ወደ አንድነት ለመምጣት ምን አስተዋጽኦ እናድርግ ብሎ መነሳት ክርስቲያናዊ ነውና ሁላችንም በተናጠል እራሳችንን ጠይቀን ለሰላም እንነሳ። እከሌን ብናገረው እንጣላለን ከመሃበር ያባርሩኛል ያልሆንኩትን ስም ይሰጡኛል፡ ዝምድናችን ይፈርሳል ጔደኝነታችን ይቀራል በቡድን ያጠቁኛል ብሎ በመፍራት ለእውነትና ለመብት አለመነሳት ደግሞ በሕሊና ማስጠየቅ ይኖርበታል እንላለን። ስለሆነም ለሁላችሁም ዛሬ ጥያቄዎች ማቅረብ እንወዳለን። በግል ምን እያደረግን ነው? ሰለኛ ሌሎች እስከመቼ ይወስናሉ? መብትና እምነት፡ ሕግና አምልኮን መለየት የምንችለው መቼ ነው? ከራሳችን ጋር እንዴት እንታረቃለን? መንፈሳዊ አባት እየዘለፍን እንዴት መንፈሳዊ ነን ማለት እንችላለን? መንፈሳዊ አባቶቸስ ከተሰጣቸው ስልጣን ውጪ ሲያልፉ እንዴት እናስቆማቸዋለን? የነዚህን ጥያቄዎች ከመለስን የችግሩን ብዙውን ጎን ቀረፍነው ማለት ነው ብለን እንስማማ።
አሁን ምንእላለሁ ከምንስ ላይ ቆሜ፡
የገደለው ባሌ የሞተው ወንድሜ።ይሉ አልነበር።






Sunday, November 14, 2010

ጥርስ የሌለው ውሻ ጉልበቱ ከጩኸቱ ላይ ነው ቁጥር ፵፰

እንዴት ከረማችሁ

አዲስ የተከሰተ ነገር ባለመኖሩ ጊዜአችሁን ልናጠፋባችሁ አልፈለግንም፡፡ ለሥራ መሯሯጥ ደግሞ በዚህ አገር የግድ ነውና እንደምንራወጥ መሯሯጣችሁ ይገባናል ማለታችን ነው። ቢሉም ያራሩጣል ይሉ የለ። ሁሉም ነገር ትግል ሆነ። "ለምታበራቱን ድጋፋችሁ ላልተለየው ሁሉ ምስጋናችንን አድርሱልን። በረዳችሁን ቁጥር ሃላፊነት እየጣላችሁብን የጀመርነውን እንድንጨርስ እያደረጋችሁ ግፊት እየጣላችሁብን ነው ብላችሁ ንገሩልን"  ያሉት ለቤተክርስቲያናችን የመብት ትግል ግንባር ቀደምት ሚና  የሚጫወቱት ናቸው። እውነትም እኛም  ስናስተውለው ለጠበቃ የሚወጣውን ወጭ እናንተ  ምእመናን ባትጋሩት ኖሮ ለጥቂቶች ይከብድ ነበር ብለን አሰብን። የቦርዱ አባላት አሁንስ በቃ  እስክትሏቸው ድረስ እንደልብ የሚጽፉት ለጊዜው የማያልቅ የሚመስል ገደብ የሌለበት የባንክ ደብተር አላቸው። ገንዘብ ያላግባብ ማባከን አያስጠይቅም እንዴ? ብለው ሲጠይቁ ለነበሩ አባት በቦታው መልስ መመለስ አልቻልንም ነበር። አሁን እንመልስላቸው። አዎ  ያስጠይቃል ጠያቂው ግን  ምእመን መሆን አለበት። እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት ያለውን ጉዳይ ብትመለከቱት በዋናው ጉዳዩ ላይ ክርክር ሳይጀመር በስነስርዓት ነጥብ (PROCEDURAL ISSUE) ላይ መሆኑን እንደኛ ታዝባችኋልን? እኛ ካስተዋልነው ውሎ  አደረ።

ፖሊስ አታስመጡ፤ ምእመንን  ማባረር አትችሉም፤  ዶሴዎችንና ማናቸውንም የቤተክርስቲያኑን መረጃዎች አታጥፉ ተብለው ታዘዙ  ይግባኝ አሉ። ይህ ጉዳይ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ  እየጠበቀ  ያለ ነው።

ከከሳሾች ጠበቃ የቀረቡትን መጠይቆችን አንመልስም ብለው የቦርድ አባላት አሻፈረኝ አሉ። ይባስ ብለው የተከሳሾቹ  ጠበቃ ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ አስቁሙልን ብለው ተማጸኑ።  ባለፈው እንደነገርናችሁ የሁለቱንም ጠበቆች ክርክር ሰምተው የተከበሩት ዳኛ ጥያቄዎችን የመመለስ ግዳጅ አለባችሁ ብለው ወሰኑባቸው። ይግባኝ ለማለትም 3 ቀን እንዳላቸው ነገሯቸው። አሁን የደረሰን ዜና እንደሚያስረዳን ይህንንም የዳኛውን ውሳኔ በመቃወም የተከሳሾቹ ጠበቆች ይግባኝ ብለው ጉዳዩ  ለ DECEMBER 20  ተቀጥሮ ሁኔታውን የተከበሩት ዳኛ ስሚዝ በተባለው ቀን እንደሚያዩት ለመረዳት ችለናል።

በተጨማሪም በ DECEMBER 9 አሁንም የቦርዱ ጠበቆች ባጠቃላይ ክሱ ይሰረዝልን በማለት ለተከበሩ ዳኛ ስሚዝ የመከራከሪያ ዶሴ ( SUMMERY JUDGMENT) ማስገባታቸውና ይህም ለ DECEMBER 9, 2010 መቀጠሩን እንደነገርናችሁ የሚታወሰ ነው።

ባጠቃላይ ቀደም ሲል ሕጉን መቀየር ትችላላችሁ ተብሎ ከተወሰነላቸውና ይህም በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ካለው ጉዳይ ሌላ ይህንን አደረግን  የሚሉት የላቸውም። ይህንን ለማድረግ የከሰከሱት ገንዘብ ደግሞ ወደ $100,000 ደርሷል ወይንም አልፏል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ይህ ታዲያ ቤተክርስቲያኗ ከምእመናን ያጣችውን የገንዘብ ገቢ ሳያጠቃልል ነው። ይህንን ጉድ አናይም ብለው የተበተኑትን ምእመናን ደግሞ ወደ ገንዘብ መቀየር ስለማይቻል እንጂ ጉዳቱን የበለጠ የሚያስከፋ ያደርገዋል። በእኛ እምነት ከገንዘቡ የበለጠ የምእመናን ሽሽት ጎጅ ነው እንላለን። ታዲያ ሁኔታው የመብት ነውና የአማንያን መብት ሳናከበር ወደ ነበረበት መመለስ ይቻላል ብለው የሚሉትን ግለሰቦች መረዋ ሊጠይቅ የሚፈልገው ነገር ቢኖር የሚከተሉትን ነው፤

ማን ነው ሁለተኛ ደረጃ  ዜጋ ሆኖ የሚኖር?
ተመራጮች ነን ባዬች ፈላጭ ቆራጭ ያደረጋቸው ማን ነው?
የምእመን የበላይነት እንዴት ይከበራል?
ወጣቶችን አይደለም ሽማግሌን ከሚንቁ የቦርድ አባላት ጋር እንዴት መነጋገር ይቻላል?
አምባ ገነን ሆነው ቤተክርስቲያኑን  እየበተኑት ያሉትን መፍራት የሚቆመው መቼ ነው?
የሚቃወማቸውን ለማጥፋት ታጥቀው የተነሱ የቦርድ አባላት ሲያሰኛቸው ካህኑን፤ በረድ ሲሉ ጽዋ የሚጠጣውን፤ በፈቃደኝነት ሱቅ ውስጥ የሚያገለግሉትን፤ በፈቃደኝነት ወጣቶች የሚያስተምሩትን፤ በደጀሰላም የሚተባበሩትን ተባራችኋል እያሉ የሚበትኑን እስከመቼ  ነው?
ቤተክርስቲያኑን በጥቂት ተቆጣጥረው የሚበትኑበትን ቀን የሚጠብቁ መሪዎችን ከውጭ ስናወራ አይሰሙም እያልን እየተናገርን ስናያቸው ግን የምንሸማቀቀውና አንገት የምንደፋው እስከ መቼ  ነው?
የነሱ ጉልበት ሚካኤል ሳይሆን በድብቅ የሚጻፈው ጦማር (BLOGS) ሆኖ የሚቆየው እስከመቼ  ይሆን?
ፍቅር በመከባበር እንጂ በፍርሃትና በስድብ ይመጣልን?
በሕግ አምላክ ብሎ ወደ ሕግ መሄድ ነው የሚያስነውረው ወይንስ በተፈጠረ ጦማር መሳደብ?
የሚሰደቡት ናቸው ጥፋተኞች ተሳዳቢዎቹ? መመለስ ያለብን  እንደ ግለሰብ እያንዳንዳችን መሆን አለብን።

ለማንኛውም የሚነዛውን የውዥንብር ወሬ  ሳይሆን እውነቱን በራስ ተመራምሮ  ማግኘት ክርስቲያናዊ ግዴታም  ነው እንላለን።

ባለፈው እንደነገርናችሁ "እኛ እንዳየነው ጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ የመልከኛው  ነው ካሳውን ግን ገበሬው ይካስ" አይነት ፍርድ የሚቀረው መቼ ነው?  አንድ እናት ባንድ ግብዣ ላይ "ልጆቼ ካወቃችኋቸው እነዚህን ከሳሾች ክሱን አቁሙ በሏቸው" ብለው ሲናገሩ አንዱ አዳማጭ እማማ የቦርዱን ተመራጮች ለምን ተው በሏቸው አላሉም?  ብሎ ለጠየቃቸው ሲመልሱ  "እያወቃችሁ እነሱ እንኴን ሰው ሚካኤልንም አያዳምጡም" አሉ ተብሎ  ነበር። ይህንን ያመጣነው ለቀልድ  ሳይሆን ያለውን ስሜት ለማሳየት ነው።

ለመብት የተነሱት ከሳሾች በእምነት አልከሰሱም በደረሰባቸው የመብት እረገጣ እንጂ። ክስ የመሰረቱት እናት የከሰሱት እንደሰማነው በሃይማኖት ጉዳይ አይደለም በደረሰባቸው በደል እንጂ። ታዲያ ይህንን ያደረገውን ዝም ብለን እናያለን የሚሉ ሁሉ ቤተክርስቲያኑን እያፈረሱ መሆኑንን  መረዳት ይኖርባቸዋል። 

ሁላችሁም ከቻላችሁ በሚመጣው DECEMBER  9 ከፍርድ ቤት በመገኘት የፍርድ ቤቱን ጉዳይ እራሳችሁ እንድትከታተሉ ጥሪ እናቀርባለን። ዜና ስትፈልጉ  ወደ መረዋ  ስድብ ለመስማት ደግሞ ወደሌላው ጦማር ጎራ  በሉ።

የሳምንት ሰው ይበለን።


Monday, November 8, 2010

በእንጎቻ ያመሸ እረኛ እራቱ እንጀራ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ፵፯

እንደምን ከረማችሁ ምእመናን

ዛሬ የምንጽፈው ባለፈው ቃል እንደገባንላችሁ የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ ለናንተ የሰማነውን ለማካፈል ነው። እንደ ሌሎቹ "ምሑራዊ" ትንተና ልንሰጣችሁ አይደለም። አንባቢዎቻችን ክፉና  ደጉን ማበጠር  እንደምትችሉ፤ እውነትና ውሸትን እንደምትለዩ፤ የነገሮችን አካሄድ ጠንቅቃችሁ እንደምትገነዘቡ እናውቃለንና። ዛሬ በዛኛው ጎራ እንዳነበባችሁት ሥም እየጠራን ልንሰድባችሁ አይደለም። ይህ የነሱ እንጂ የኛ ባሕርይ አይደለምና። ለዚህ አይነቱ ስድብ አስተዳደጋችንም ሆነ ኢትዮጵያዊ ባህላችን ስለሚገታን። ሌላውን ስንሳደብና ስናንቋሽሽ የሚታዩን ያሳደጉን ቤተሰቦቻችን በመሆኑ፡ አሳዳጊ የበደለው ተሰኝተን መሰደብ አንወድምና። ሃላፊነታችን የነበረውን እንዳለ  ማቅረብ ብቻ  ይሆናል። ፖለቲካ ከቤተክርስቲያናችን መውጣት አለበት ስንል ካየነውና  ከታዘብነው ብሎም ከሚጽፉት በመነሳት ነው። ከዋሸን እነሱ ጋ  ጎራ  በማለት በማንበብ ማመዛዘን ይቻላል። እኛ ደግሞ  ቃላችንን  ከወለድነው ልጅ የበለጠ እናከብረዋለን። እኛ አፕልና  ብርቱካን እንደማናደባልቅ ደግሞ ምስክሮቻችን እናንተ  ናችሁ። ስለብርቱካን  እያወራን ስለ አፕል መዘባረቅ አለመደብንም። ይህንን የሚያደርግ በግንዛቤ ሰንካላ ወይንም ድኩም የሆነ  ብቻ ነው ብለን ስለምናምን።

ለመግቢያ  ይክል ይህንን ካልን በኌላ  በዛሬው እለት ስለዋለው ችሎት እናውሳችሁ።

በቦርዱ ጠበቆች ማመልከቻ  መሰረት ለዛሬ ተቀጥሮ  የነበረውን  ጉዳይ የተመለከቱት ዳኛ የተከበሩ ሸርሊን ማክፈርላንድ ነበሩ። ዳኛዋ የካውንቲው እረዳት ዳኛ (ASSOCIAT JUDGE) ናቸው። ጉዳዩን ስላላነበብኩት አስረዱኝ ያሉት ዳኛ ከቦርዱ ጠበቆች የቀረበ ገለጻና የከሳሾችን ጠበቃ መልስ አዳምጠዋል። በመሰረቱ ክሱ የከሳሽ ጠበቃ ይሰጡኝ ብሎ  የጠየቀውን ከ50 በላይ የሆኑ ጥያቄዎች አንሰጥም በማለት የቀረበ  ክርክር ነበር። በጥቅሉ የቦርዱ ጠበቆች ክርክር የነበረው ከሳሾች  የሌላ  እምነት ተከታዬች በመሆናቸው፡ ከዚህ በፊት በሌላ  ክስ የከሰሱ በመሆኑ፡ አባላት ባለመሆናቸው፡ ይህ የእምነት ጉዳይ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የማየት ስልጣን ስሌለለው ጥያቄውን ያስቁምልን የሚል ነበር።  የከሳሾች ጠበቃ በበኩሉ የጠየቃቸው ጥያቄዎች አንድም የእምነት ነገርን እንዳልያዘ በመጥቀስ ለናሙና ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

1 የአባላት ዝርዝር 
2 የቦርድ አመራረጥን የሚያሳይ ሰነድ
3 የገንዘብ ወጪና  ገቢ ሰነድ
4 ቃለጉባኤ   
5 የደብዳቤ ልውውጦች ወዘተረፈ መሆናቸውን አስረድቷል።

የተከበሩ የፍርድ ቤቱ ዳኛ ሁኔታውን  ካዳመጡ በኋላ  የቦርዱ ጠበቆች የተጠየቁትን  ሰነድ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንዲሰጡ ወስነዋል። ተከሳሾቹ በውሳኒያቸው ካልተስማሙ ለዋናው ዳኛ  3 ቀን ባልበለጠ ጊዜ  ውስጥ ይግባኝ ብለው በተከበሩ ዳኛ ስሚዝ ፊት በመቅረብ መከራከር እንደሚችሉ ነግረዋቸዋል። የተከሳሾች ጠበቃ በውሳኔው ላይ ማሻሻያ  ለማድረግ የጠየቁትንም ሆነ ዶሴዎቹን ከእኔ  ቢሮ  መጥተው እንዲያዩ ይታዘዝልኝ ብለው ያሳሰቡትን ዳኛዋ ሳይቀበሉት ቀርተዋል።

ይህ የዛሬው የከሳሾች ድል ጉዳዩ የሃይማኖት ሳይሆን የመብት ጉዳይ ለመሆኑ ሌላ  ማረጋገጫ መሆኑን የሕግ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በሚመጣው ወር ማለትም በ12-09-2010 የቦርዱ ጠበቆች ክሱ ይሰረዝልን በማለት ሌላ የፍርድ ሃሳብ ያስገቡ መሆናቸውን እየነገርናችሁ በዚያም ቀን በተከበሩት ዳኛ ስሚዝ ችሎት የሚደረገውን ክርክር ውሳኔ እንደምናቀርብላችሁ ካሁኑ ቃል እንገባለን።

እውነት ሁልግዜም እውነት ነው።

እውነት እንደሚያሸንፍ የሚጠራጠር ደግሞ እምነተቢስ ነው።




Saturday, October 30, 2010

ከሰገነት ያለ ሰው እይታው ሁል ጊዜ ቁልቁል ነው ቁጥር ፵፮

እንዴት ከረማችሁ ላላችሁን ሁሉ ሰላሙን ያድላችሁ እያልን ከልብ ለሚያበረታታው የ E MAIL መልክታችሁ  አሁንም  በምእመናን ስም ምስጋና እንድናቀርብ ፍቀዱልን። የፈጣሪና የእናንተ እርዳታ ባይታከልበት ኖሮ እዚህ እንደማንደርስ መናገር ደግሞ እውነት ነው። በመሃከሉ የራስም የሕይወት ትግል ያዘንና ስንሯሯጥ ከረምን።ያም ሆኖ አዲስ የተከሰተ ነገር ባለመኖሩ "ከቤተክርስቲያኑ ሱቅ ሰራተኞች መባበር"  ሌላ እሱንም ባለፈው የተናገርነው መሰለን፡ ብዙ ያጋጠመን የለም ለማለት ነው። መረዋ የናንተ ነውና የሰጣችሁንን ምክር በመቀበል አሁንም በከፍታው ላይ ለመራመድ ቃል እንገባለን።

በምንም ዓይነት እረግረግ ውስጥ ገብተን በቆሻሻ ዋልካ ተጨማልቀን፡ በስድብ ተበሻቅጠን አታዩንም።
በምንም ዓይነት በመብታችን ተደራድረን በፍራቻ አጎብድደን አታስተውሉንም።
በምንም ዓይነት ከመልአኩ እግር ሥር እንጂ ከግለሰብ እግር ሥር ወድቀን አታዩንም።
በምንም ዓይነት ለፈጣሪ ካልሆነ  በስተቀር ለግለሰብ አናጎበድድም።
በምንም ዓይነት ለፍቅር እንረታለን እንጂ ለጥላቻ አንበረግግም።
በምንም ዓይነት የሚያከብሩንን እናከብራለን እንጂ አንፈራም። ስለሆነም እናንተው እንዳላችሁት " ለሚሳደቡ ጸልዩላቸው" ለሚታገሉ እንዱሁ ለብርታታቸው ሁሌ በጸሎት አትርሷቸው።

አንድ መንፈሳዊ አባትን አንዱ ምእመን አባቴ ዋና የሚያጸድቅ ነገር ምንድነው? ብሎ  ለጠየቃቸው ሲመልሱ "የሚያጸድቀው ለማድረግ የሚከብደው ነገር ነው። የሚያስኮንነው ግን በየቀኑ የምታደርገው ቀላሉ ነገር ነው" አሉት። እንዲያ ካሉ እግዚአብሔር የለም ማለት እኮ ቀላል ነው አላቸው። እሳቸውም "አሁን የሲኦልን ቁልፍ አገኘኸው"  አሉት።   ሰውን መግደል እኮ  እንደዚሁ ቀላል ነው ሲላቸው "አሁን ደግሞ  የሲኦልንም የዘብጥያውንም ቁልፍ ተረከብከው ማለት ነው" አሉት ይባል ነበር።

ባጋጣሚ ሰሞኑን የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩትን የቢል ክሊንተንን MY LIFE  "ሕይወቴ"  የሚለውን  መጽሐፍ ስናነብ ያየነውን እናካፍላችሁ። ፕሬዚዳንት ክሊንተን ሁለተኛ ደረጃ  እንደገቡ የጻፉትን ድርሰት አስታውሰው ሲያስነብቡ (PAGE 58) ......."I, ME, MY, MINE........ THE ONLY THINGS THAT ENABLE WORTHWHILE USES OF THESE WORDS ARE THE UNIVERSAL GOOD QUALITIES WHICH WE ARE NOT TOO OFTEN ABLE TO PLACE WITH THEM - FAITH, TRUST,LOVE, RESPONSIBILITY, REGRET, KNOWLEDGE." ብዙ ጊዜ አናደርገውም እንጂ እኔ በግሌ  የኔ የግሌ ........የሚሉትን ቃላቶች ከአምልኮ ከእምነት ከፍቅር ከሃላፊነትመቀበል ከቁጭትና ከእውቀት ጋር ብናጣምራቸው አለማቀፋዊ ስምምነት ያለው መልካም ምግባር ይሆን ነበር። ትርጉም የራሳችን።

ይህንን ያነሳነው እያንዳንዳችን ያደረግነውን መጠየቅ ብንጀምር ስህተትን ለማረም ይረዳ ነበር ለማለት ያክል ነው።

ሚስቴ ለምን ፈታችኝ ከማለት ይልቅ? ምን ብበድላት ነው የተጣላችኝ? ማለት የተለያየ ትርጉም እንዳለው ሁሉ የተለያየ መፍትሄ  ላይም ይጥላል።

ይህንን ካልን ዘንዳ ወደ ጉዳያችን ስንመለስ ባለፈው በ DECEMBER ወር ተቀጥሮ  የነበረው ቀጠሮ አሁን ወደ 192 ፍርድ ቤት በመዛወሩ ዳኛው ካላቸው የቀጠሮ ቅደም ተዋረድ ጋር በማዛመድ ለJANUARY 10 2011 ለክርክር  መቀጠሩን ስንነግራችሁ፡ ሌሎች እንዳስፈራሩን መንፈቅ ሳይሆን አንድ ወር ብቻ በመራዘሙ ደስተኞች መሆናችንን በመግለጽ ጭምር ነው። ፍርድ ቤት ለችግራችን ሙሉ ለሙሉ መፍትሄ ይሰጣል ብለን አስበን እንደማናውቅ ሁሉ መብታችንን እንደሚያስከብርልን ግን ለሴኮንድም ተጠራጥረን አናውቅም።

ለእምነቱም እኮ  መብት መኖር አለበት
ለማስቀደሱም መቆሚያ
ለማስጠመቁም ማጥመቂያ
ለማስፈታቱም መጠጊያ  ሲኖር ነው።


እናት ሃገር ቢሞት ባገር ይለቀሳል
አገር የሞተ እንደሁ ወዴት ይደረሳል ያለውን ያስታውሷል።

አንዴ በደርግ ዘመን መሆኑ ነው ባለቤቷ ፊቱን እያዞረ ያስቸገራት ሚስት ወደቀበሌ ሄዳ ችግሯን ለቀበሌ ትናገራለች። ቀበሌም ሁኔታውን አዳምጦ ባልየው ፊቱን ሁልግዜ  እያዞረ  መተኛት እንደሌለበት ይነገረውና ትእዛዙን ተቀብሎ ማታ ሚስቱን አቅፎ ያድራል። በነጋታው ካሁን በኋላ  አላደርገውም ብሎ ለሚስቱ ሲነግራት ባለቤቱ "ወደህ በቀበሌ ተገደህ" ብላ አለች ይባል ነበርና እኛም ለጊዜው በቤተክርስቲያን ማስቀደስ መቻላችን በሕግ ግዳጅ እንጂ ተወርውረን ተጥለን እንደነበር ለመጥቀስ ያክል ነው። ማንም ለማስቀደስ የቦርዱን ቡራኬ  ማግኘት ይኖርበታል ብለን አናምንምና። እዚህ ቤተክርስቲያን ደግሞ  ከዚህ በፊት እንደተናገርነው አንዱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ ሆኖ መቀጠል አይቻልም። ሁሉም እኩል ነው ማለት እስካልተቻለ  ድረስ ደግሞ ትግሉ ይቀጥላል። ለአምልኮ ቡድን የሚያስፈልግበት ምክንያት አይታየንም። እንዴውም ቤተክርስቲያን ዘመድ ለሌለው ብቸኛ ለሆነ አልነበረም እንዴ?
በቅዳሴ ሰዓት ከሰገነት ተቀምጠው ቁልቁል በማየት ንቀት የለበሱ ካሉ ማንጋጠጥ መልመድ አለባቸው እንላለን። ካልሆነ መጨረሻው አያምርምና። አቶ ሃይሉ እጅጉን ጠርተው እንከስሃለን ብለው የተሳደቡ የቦርድ አባላት። ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ለሚያደርጉት ሥራ  ሁሉ በግል ተጠያቂ እንደሚሆኑ የዘነጉ ይመስላል። ባለፈው በደጋፊዎቻቸው ብሎግ ላይ እንዳሉት እኛ ምን እንሆናለን የመድሕን ድርጅቱ ይጨነቅበት ማለት አይቻልም። እዚህ አገር ደግሞ  እንኳን የዚህ የቤተክርስቲያን የቦርድ አባላት ቀርቶ የአሜሪካዊውም ፕሬዚዳንቱም ካጠፉ ፕሬዚዳንት ነኝ አልጠየቅም ማለት አይቻላቸውም። የኒክሰንን የዋተር ጌት ቅሌት ያስታውሷል። ማንም በድርጅት ሽፋን ተነስቶ  ምእመናንን መተናኮል አይችልም ለማለት ነው። ይህንን ስንል ደግሞ ለማስፈራራት ሳይሆን በመብታችን ላይ ለደረሰው በደል ተጠያቂዎች እንዲጠየቁ ለማድረግ እንደምንታገል ለመግለጽ ጭምር ነው።

ለተሳዳቢዎቹ ሰው ላንመስላቸው እንችላለን እኛ ግን ሰው መሆናችንን እያወቅን ላላወቁ ለማሳየት በሕግ እንታገላለን።

በቅርቡ ቸር ወሬ እንደምንሰማ እርግጠኞች ነን።

ለዛው ያድርሰን

ልትገናኙን ለምትፈልጉ አሁንም አድራሻችን

YETAYALEWNETU@GMAIL.COM  ነው። መልካም ሳምንት።

Monday, October 18, 2010

"ውዳሴ የደገመ ሞኝ ተማሪ ደብተራ የሆነ ይመስለዋል።" ቁጥር ፵፭

አምናና  ካች አምና  ደህና  ሰው ነበረች፤
በሽታዋ  መጣ ትተኩስ ጀመረች።
ብለው የተቀኙት አዋቂ ሽክላ መተኮስ ነውር በነበረበት ሰዓት ለመወለዳቸው ምስክር አያስፈልግም። ነገሩን እንዴት በተሸፋፈነ መንገድ እንዳቀረቡት የተረዳ ሰው ደግሞ ያነጋገር ዘይቤአቸውን የቅኔ ችሎታቸውን ማድነቁ የማይቀር ነው። አባቶች ሲያሳሰቡም ሲያስተምሩም በምሳሌና በጥበብ እንደነበረ ብዙ መረጃ መጥቀስ ይቻላል። እኛን ዛሬ የቸገረን ያካባቢያችን የኃይማኖት ጋቢ የለበሰው የተንኮል ቅኔና ዘለፋ  ነው። ባለፈው የመረዋ እትምታችን የኪዳነምሕረትን ማህበር ያባረሩትና እንዲፈርስ ያደረጉት የሚካኤል ሊቀመንበር እነሆኝ በትላንትናው እለት ደግሞ በፈቃደኝነት ለዓመታት ያገለገሉትን የቤተክርስቲያን  ሱቅ (GIFT SHOP)  ከፍተው መጻሕፍትን የመዝሙር ቅጅዎችን የተለየዩ የቤተክርስቲያን ቁሳቁሶችን ለምእመናን በመሸጥ ለቤተክርስቲያኑ ገቢ በማስገኘት ያገለገሉትን አንጋፋ የቤተክርስቲያን አባላት እናቶች "ካሁን በኋላ  ስለማንፈልጋችሁ የሱቁን ቁልፍ አስረክባችሁ እንድትሄዱ ቦርዱ በወሰነው መሰረት ባስቸኳይ ቁልፉን እንድታስረክቡ"ብለው ፈርመው እንደሰጧቸው የደረሰን ዜና  ያረጋግጣል። ደብዳቤው በማ እንደተጻፈ ባናውቅም የፈረሙት ግን ሊቀመንበሩ አቶ  ዮሴፍ እንደሆኑ  አስረክቡ የሚለው ደብዳቤ  ላይ  ባሰፈሩት ፊርማቸው ለማረጋገጥ  ችለናል።
ይህ ለምን ተደረገ?  ብላችሁ ለምትጠይቁ ግለሰቦች መልሱ "የስደት ሲኖዶስ"  የነ አባ  መልከጸዲቅ መዝሙርና  ሰበካ ሲዲና ክር በእነወይዘሮ ብኩሪ አሳላፊነት በሱቁ ውስጥ እንዲሸጥ በማቀድ እንደሆነ ታዛቢዎች ይናጋገራሉ። እኛም ጥርጣሬውን ሙሉ በሙሉ እንጋራለን። ሰሞኑን  መቅደስ እንዳይገቡ የተከለከሉ ዲያቆን መኖራቸውን ስንሰማ አልተገረምንም። ትላንት ከመቅደስ የተከለከሉ ካህን አይተናልና። እስካሁንም መቅደስ ውስጥ እንዳይገቡ የተከለከሉት ካህን  ከሽማግሌዎች  ጋር ተቀምጠው ማስቀደሳቸውን አላቋረጡም። ለነገሩማ  ካህኑ የተበተነው የአማካሪ ኮሚቴ አባል አልነበሩ ከኮሚቴው ሊቀመንበርና ከአባላቱ ጎን ሆነው ቢያስቀድሱ ምን ይገርማል።

በተለያዩ ብሎጎች ላይ ይህንን ብሎግ አስመልክቶ ብዙ የተጻፈ የስድብ ውርጅብኝ በማንበብ  ለምን መልስ እንዳልሰጠን የጠየቃችሁን ብዙዎች ናችሁ። ነገር ግን መረዋ የብዙሃኑ ንብረት እንጂ የግለሰብ ንብረት ባለመሆኑ የግለሰቦች ስም በተነሳ ቁጥር ምንም እንኳን ያለማወላወል የምንደግፋቸው ግለሰቦች ቢሆኑ አካኪ ዘራፍ ማለት አልፈለግንም። በተለየዩ ወቅቶች ሁኔታው እንደፈቀደ ስማቸው የጠፋውን ግለሰቦች በመደገፍ የተሰማንን መግለጻችን ደግሞ ለሁላችሁም ግልጽ ነው። በነገራችን ላይ ግማሾቹ የመረዋን አ ቋም የማይደግፉ ግለሰቦች መሆናቸውን እያወቅን እንኳን መሰደብ እንደሌለባቸው መናገራችንን እናስታውሳለን። በእኛ እምነት ሰውን በመስደብ መጣላት እንጂ መፋቀር ይመጣል ብለን አናምንምና። ባለፈው እንዳልነው "እዳሪና አፈር የሚለየው በሽታው ነውና። " እናንተ እየለያችሁ እንደወንፊት እንደምታበጥሩት ደግሞ ሙሉ እምነታችን ነው። ክርስቲያን ነን የሚሉት እነዚህ ሰዳቢዎች በዚህ መጽደቅ ከቻሉ ደግሞ ማንም ጽድቁ ይቅርብኝ ቢል እውነት አለው እንላለን። ውዳሴ  ማርያም የደገመ ሞኝ ተማሪ ደብተራ የሆነ  ቢመስለው ሞኝነቱን አረጋገጠ እንጂ ደብተራ  አልሆነምና።
ክርስቲያን ወንድሙን ይወዳል እንጂ አይሳደብም
ክርስቲያን ለእውነት ይሞታል እንጂ አይዋሽም
ከርስቲያን ለይቅርታ  ይነሳል እንጂ ክርስቲያንን ሊያባርር አይነሳም
ክርስቲያን መንፈሳዊ አባቶችን አያቀልም
ካህንን አይዘልፍም
ክርስቲያን አይሰርቅም
ክርስቲያን ድሃ  ወንድሙን ይረዳል እንጂ በድህነቱ አያፌዝም
ለዚያውስ መጽሐፉ "ሃብታም ይጸድቃል ከማለት ይልቅ ግመል በመርፌ  ቀዳዳ መሹለክ ትችላለች ማለት ይቀላል"  አይልምን።
ለነገሩ ቢገርመን ተናገርን እንጂ ባለፈው እንዳልነው ካሜከላ ብርቱካን አንጠብቅም።
እንደ ማስፈራራታችሁ ሰሚ ብታገኙ እስካሁን ተገድለን ነበር። አልሞትንም ለመብት በመጣ ደግሞ ብንሞትም አይቆጨንም።
እናንተ አስፈራሩን እኛ አሁንም በሕግ እናስቆማችኋለን። እምነት ሊያቆመው የሚችል እኮ የሚያምንን ብቻ ነው። እናንተ  እንደምትሰብኩት እምነት ስድብና ዛቻ  ከሆነ እኛ የናንተን ሳይሆን የሕግን ከለላ  እንጠይቃለን።
ውድ አንባብያን
አንዳንድ የጠየቃችሁን መልስ ለመስጠት ለጊዜው የምንጠቅሳቸው ነገሮች አሉን። ሽማግሌ በቤተክርስቲያኑ ክስ ውስጥ ገብቷል ወይ?  ብላችሁ ለጠየቃችሁን እኛም እንደናንተ መስማታችንን ያረጋገጥን  ይመስለናል። በተለይም የሚካኤል መፍትሄ  አፈላላጊ ኮሚቴ ልሳን የሆነው WWW.MELEKET4U.BLOGSPOT.COM  የዘገበውን ሄዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። ዋሽተን አናውቅም ስንል ለአፋችን ሳይሆን ከልባችን ነው። ዋሽተን ያገኛችሁን እለት የመሞቻችን የመጨረሻውም የመጀመሪያውም ወቅት ሆነ  ማለት ነው።

ከደረሱን መረጃዎች ጥቂቶቹን እናካፍላችሁ።

በሚካኤል ቤተክርስቲያን የመብት መደፈርን አስመልከቶ የተከፈተው ክስ ወደ ተከበሩት ዳኛ ስሚዝ መተለለፉን መናገራችን ይታወሳል። ስለሆነም ቦርዱ ለከሳሾች አልሰጥም ያለውን ፋይልና ግልጽ መረጃ አስመልክቶ ወሳኔ ለመስጠት በፊታችን ኖቬምበር 8 በዳኛ ማክፈርላንድ ችሎት እንደሚታይ ቀጠሮ መያዙን መረዳት መቻላችንን ልንነግራችሁ እንወዳለን። መረዋ በወቅቱ በፍርድ ቤት በመገኘት ስለፍርድ ቤቱ ሂደት ለአንባብያን እንደሚያቀርብ ካሁኑ ቃል እንገባለን።

በሁለተኛ ደረጃ  በቤተክርስቲያኑ ላይ የተጫነውን የዳኛ ትእዛዝ ማለትም

ፖሊስ ወደ መቅደስ አታስገቡ
አባላትን አታባሩ
ዶሴዎችን አታጥፉ የሚለውን የለም
ፖሊስ ማስገባት አለብን፡
አባላትን ማባረር መብታችን ነው፡
ዶሲዎችን ማጥፋት ይፈቀድልን። በማለት የቦርዱ ጠበቆች ይግባኝ ማለታቸው የሚታወስ ነው። በዚህም መሰረት ሁኔታውን ለማስረዳት በተያዘው የOCTOBER 29 ላይ ሁለቱም ጠበቆች በይግባኝ  ሰሚ ፍርድ ቤት ቀርበው ገለጻ ለመድረግ እየተዘጋጁ መሆኑን ለመረዳት ችለናል። አሁንም  በፊት እንዳደረግነው ሁሉ ከፍርድ ቤት ውሎ በኋላ መረዋ የሚደርሰውን ለአንባብያን እንደሚያቀርብ ቃል እንገባለን።

በመጨረሻም በወይዘሮ ሶፍያ  የተከፈተው የመብት መደፈር፡ የአካል መጎዳትና፡  ያለወንጀል መታሰር ክስ በ DISTRICT COURT 68 በተከበሩ ዳኛ ማርቲን ሆፍማን ችሎት እንደሚዳኝ ለመረዳት ችለናል። 

ውድ አንባብያን ድጋፋችሁን እያደነቅን ለምታደርጉት ሁሉ ዋጋችሁን ሚካኤል እንዲቆጥርላችሁ እየጸለይን፡ በሚደርስብን ዛቻ ማስፈራራትና  ስም ማጥፋት ተሸማቀን ሸብረክ እንደማንል በድጋሜ  ልናረጋግጥላችሁ  እንወዳለን። እስከዛሬ ግለሰብ ሲወነጀል እንሰማ የነበረው ለምን ህግ እያለ ህግን ጥሶ  እርምጃ ወሰደ  በሚል ነበር። ዛሬ  ከሳሾች መብታቸውን ለማስከበር ወደ ሕግ በመሄዳቸው እንደዚህ የሚሰደቡ ከሆነ ተሳዳቢዎቹ አንድም የአእምሮ ጨቅላዎች ናቸው። ካልሆነ ህክምና የሚሹ ህሙማን ናቸው። ባይሆንማ  ኖሮ በተሰባበረ "የምሁር"  ብእራቸው እንዲህ ሲዛለፉ ባልታዩ  ነበር።

እድሜ  ይስጠን ገና  ብዙ እናያለን።


ሰሞኑን እስክንገናኝ
ደህና  እደሩ

Thursday, October 7, 2010

የፍርድ ቤት ውሎ ልዩ እትም

አሸነፍን ብለው ለደስታ የከፈቱት የሻምፓኝ ቡሽ የወደቀበትን አቅጣጫ ባናውቅም ወደእኛ እንዳልደረሰ ግን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን። "የረጠበ ዝናብ አይፈራም" እንዲሉ ቀጠሮ በተቀየረ ቁጥር የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ እንደወረሱ፣ ሕንጻውን እንደተቆጣጠሩ፤ ምእመናንን አባረው እነሱ ብቻ ፈላጭ ቆራጭ የሆኑ የሚመስላቸው፣ ግለሰቦች ዛሬም የፖለቲካ  መሪዎቻቸውን አስቀድመው፡ እየጨፈሩ መሆኑን ሰምተናል። የሚያስጨፍረው  ምኑ እንደሆነ ባይገባንም መታለላቸው ግን ያሳዝነናል።

እኛ የምንጨፍረው የአባላት መብት ተከብሮ ሰው በዘሩ ሳይሆን በስብእናው፣ በፖለቲካ አቋሙ ሳይሆን በእምነቱ፣ በቡድን አባልነቱ ሳይሆን፣በክርስቲያን ወንድምነቱ፣ ሲከበር ስናይ ብቻ ነው።

የእኛ ጭፈራ አባላት ሲበረክቱ እንጂ ሲመነምኑ በማየት አይሆንም።

የእኛ ደስታ ፍቅር ሲነግስ እንጂ ጠብ ሲንሰራፋ  አይሆንም።

የእኛ ደስታ ጥቂቶች ሳይሆኑ ብዙሃን መወሰን ሲችሉ ብቻ ነው።

የእኛ ምኞት የማንም አባል መብት እኩል መሆኑን ማየት ነው።

የእኛ እውነታ የሚጠብቀን መልአክ እንጂ ቦርድ አይደለም ስንል ነው።

የእኛ ፍንጠዛ ልጆቻችን ተሰብስበው ሲጫወቱ ስናይ እንጂ ልጆች በሌሉበት ሕፃናት ባልተገኙበት መምህራን ሲንጎራደዱ በማስተዋል አይሆንም። ይህንን እስክናይ ድረስ ደግሞ መታገላችንን አናቆምም። ይህ የመብት ጉዳይ ነውና።

ወደተነሳንበት ለመመለስ የዛሬው ፍርድ ቤት እንዴት ዋለ? ለሚሉ የሰማንውን እናቅርብላችሁ።

በ 9:00 ሰዓት የተጀመረው ቀጠሮ  የፈጀው ጊዜ ከ30 ደቂቃ ያነሰ ነበር። በእለቱ የከሳሾች ጠበቃ የቦርድ አባላትን ለጠየቀው ጥያቄ  (DISCOVERY QUESTIONS) መልስ አንሰጥም በማለታቸው፣ ይህንኑ አስመልክቶ ዳኛው ትእዛዝ እንዲፈርምለት የማዘዣ ወረቀት አስገብቶ ነበር። ይህ ሲሆን የቦርዱ ጠበቆች  ሁለት የተቃውሞና የፍርድ ሃሳብ ለዳኛው በማስገባት በዚህ ላይ ውሳኔ  ሳትሰጥ ትእዛዙን አትፈርም ብለው በጠየቁት መሰረት የዛሬው ቀጠሮ ተቀጥሮ እንደ ነበር ይታወሳል። በወቅቱ የቦርዱ ጠበቆች ያቀረቡት የፍርድ ሃሳብ (MOTION)

1 ክሱ የተደጋገመ  ነውና ክሱን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገህ  በነጻ አሰናብተን።

2 ከዚህ በፊት በቦርዱ ላይ የጣልከውን እገዳ (INJECTION) ሙሉ ለሙሉ አንሳልን።

በተጨማሪ ያቀረቡትን መረጃ  የማሰባሰቢያ ጥያቄዎች ከልክልልን የሚልና ባለፈው እንደተስማማነው ጉዳዩን ከዚህ በፊት ያዩትና ለይግባኝ የተላለፈውን ክስ የወሰኑት ዳኛ ይህንንም እንዲያዩት አስተላልፍልን የሚሉ ክርክሮችና  ሃሳቦች ነበሩ።
ትላንት በወጣው መረዋ ልናስረዳችሁ እንደሞከርነው ዳኛው ይህ ክስ ከፊተኛው ክስ ጋር የማይዋሃድ መሆኑን ከመግለጻቸውም በላይ እስካሁን የቀድሞውን ዳኛ አናግራለሁ ባሉት መሰረት ባለማናገራቸው ሁለቱንም ወገን ይቅርታ ጠይቀው፣ በነገው እለት ፋይሉ እንዲዛወር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

የተከሳሾች ጠበቃ  የጠየቀውን በሙሉ አለመስማማታቸውን በመግለጽ እገዳውን እንደማያነሱ፣ ክሱ እንደማይሰረዝ፣ ሁለቱ ክስ ሊዋሃድ እንደማይችልና ወደ  ቀድሞው ዳኛ እንዲተላለፍ ሁለቱም ወገኖች የተሰማሙ ቢሆንም የቀድሞው ዳኛ ጋ ምንም ፋይል ስለሌለ ይህ እንዳዲስ የሚታይ መሆኑን አስረድተው ጉዳዩ ለቀድሞው ዳኛ ይተላለፍ ብለው ወስነዋል። የውሳኔውን ግልባጭ መረዋ ካስፈለገ  ላንባብያን እንዳለ  እንደሚያቀርበው እየተናገርን ሙሉውን የፍርድ ቤት ቃለ ጉባኤም እንደደረሰን ለማውጣት ቃል እንገባለን።
ቀን በመራዘሙ ብቻ የነገሩ ጭብጥ ሳይታይ ምስክር ሳይሰማ፣ መረጃ  ሳይቀርብ፣  ያሸነፉ የሚመስላቸው ካሉ አንድም ሁኔታው ያልገባቸው ካልሆነም ሆን ብለው ምእመኑን ለማደናገር የተነሱ ብቻ  ይሆናሉ እንላለን።

እኛ ፈሪሃ ሕግ ስላለን ዋሸተን አናሳምናችሁም። ሚስት በመደብደብ አልታሰርንም። የምንም ፖለቲካ ድርጅት መሪ ሆነን ገንዘብ አልዘረፍንም። አዲስ የመጡ ስደተኞችን የድርጅት አባሎቻችን ናችው የሚል ወረቀት ለመጻፍ የድሃ ገንዘባቸውን አልገፈፍንም። እኛ የታክሲ ማህበር መሪ ሆነን ሰንብተን ከስልጣን ሲያባርሩን ተናደን መሃበሩ የጠራውን የሥራ  ማቆም  አድማ ጥሰን ለብቻችን በአንድ ቀን ልንከብር አልተናሳንም። እየለፋን ልጆች የምናሳድግ እንጂ በስርቆት አልተተበተብንም። ለመብታችን ግን ትላንት እንደታገልንበት ዛሬም ነገም መታገላችንን አናቆምም።

ወድ አንባብያን ይህንን ጽሁፍ ስናዘጋጅ የደረሰን ሌላ አሳዛኝ ዜና ቢኖር በሚካኤል ቤተክርስቲያን የማርያም ጸበል ጸዲቅ ይጠጡ የነበሩ ማሕበርተኞች ካሁን በኋላ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ መሰብሰብና ማሕበር መጠጣት መከልከላቸውን  ከሊቀመንበሩ እንደተነገራቸው መስማታችን ነው። 

ባንድ የአካባቢያችን የፖለቲካ ባለስልጣን ነኝ ባይ የስልክ ጥሪ መሰብሰብ የሚችል ቦርድ፣ በመሃበር ለእምነታቸው የሚሰበሰቡትን አባቶችና  እናቶች ሲከለክሉ መመልከት  ምን ማለት እንደሆነ  የገባው ቢያስረዳን ደስ ይለን ነበር።

በአሜሪካ  "ፍትሕ ዘገየ  ማለት ፍትሕ ተከለከል"  እንደ ማለት ነው የሚለውን አባባል በመመርኮዝ ያሁኑ የጊዜ  መራዘም የሚያናድዳቸው ቢኖሩ ንዴታቸውን እንጋራለን። ነገር ግን የተረገዘ እስካልተወለደ  እርግዝና  ነውና ተረግዞ ይቀራል ብለን ካላመንን በስተቀር የሚወለደው ልጅ የሚያስፈነጥዘን ተወልዶ ስናየው መሆኑን በማሰብ፣ እስከዛው ለሚወለደው ልጅ እኛ መኝታና  ልብስ እንገዛለን እንጂ ይሞታል ብለን  የመቃብር ጉድጓድ አንቆፍርም። ለእውነት ስለቆምን ደግሞ እውነት እንደሚረታ  አንጠራጠርም።


መቼም ይሁን መቼ የተገፋ ያሸንፋል

እውነት ሁልጊዜ እውነት ነው።

የሳምንት ሰው ይበለን። 


Wednesday, October 6, 2010

ተከሳሽ የከሳሽን መልስ ቢያውቅ ኖሮ ፍርድቤት አይደርስም ነበር ቁጥር ፵፬

እንኴን አደረሳችሁ ውድ አንባቢዎቻችን።

መስቀል አለፈ፣ እኛን ገና አልሰቀሉንም።
ስም አጠፉ መሰላቸው እንጂ አልጎዱንም።
የስድብ ውርጅብኝ አወረዱብን ስንንበረከክ አላዩንም።
የከሳሾችን ጠበቃ ሳይቀር በማያውቀው ቋንቋ ተሳደቡ አዋረዱት ስሙን አጠፉ ከክሱ እራሱን ሲያገል አላስተዋልንም።
ከትላንት በስትያ በብሎጋቸው የሰደቡትን ባለፈው ሰንበት ተቀጠረ የተባለውን አስተማሪ እንዲሁ በብሎጋቸው ሲያወድሱት "ስንሰማ ባንድ አፍ ሁለት ምላስ" አልን እንጂ አልተገረምንም። {ትላንት በመረዳጃ  ማሕበሩ የተደረገውን የኢትዮጵያን ቀን አስመልክቶ የተረኩትን  መልሰው የሻርሩትን ባለፈው መረዋ አስነብበናችሁ ነበርና} የሚገርመን ምን እንደሚፈልጉ አለማወቃቸው ብቻ  ነው።
በፖሊስ ያሳሰሯትን ወጣት ለልጆቿ ምን? እንዴት እንንገራቸው?  ብሎ  እንደመጨነቅ በቁርባን ያገባችውን እናት ሃይማኖት የሌላት እያሉ ሲሳደቡ አነበብን።  ስለዘለፏት የምትሸማቀቅ ከመሰላቸው እምነታቸውን መጠየቅ ያለባቸው እነሱ መሆን አለባቸው እንላለን። ትላንት ዘሯን ቆጥረው የፖለቲካ  ሴት ናት እንዳላሉ ዛሬ ትክሰሳ የምትከሰው ኢንሹራንሱን ነው ብለው ቅራኔውን ለማስፋት ተራወጡ። ወንድሞችና እህቶች ባለፈው እንዳልነው ቤተክርስቲያን የአማንያን እንጂ የተወሰነ ዘር ንብረት ነው ማለት ወንጀል ባይሆን እንኴን ክርስቲያናዊ አይደለም። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ደግሞ የሃይማኖቱ የመጀመሪያ ተቀባይ የነበረው የትኛው ክፍል ነበር?

የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ  ልሳን የሆነው ብሎግ WWW.MELEKET4U.BLOGSPOT.COM ያወጣውን ኮሚቴው ከሽማግሌዎች ጋር አድርጎት የነበረውን ውይይት ሃሰት ነው ሲሉ አነበብን። ነገ ደግሞ  እነ አቶ በተሩ እነ ዶክተር ታየ እነ አቶ ጌታቸው እነ አቶ ኪዳኔ እነ አቶ  ግርማቸው እነ ሻለቃ ተፈራ እነ ወይዘሮ በየነች እነ አቶ ደም መላሽ የሚባሉ ሰዎች በዳላስ መኖራቸውን አልሰማንም ቢሉ አትገረሙ። ከመሰላቸው ይዋሹ መዋሸት ደግሞ በሽታ  ነው የሚላቸው ጓደኛ እንደሌላቸው ስናይ ማዘናችን ግን አይቀርም። ምንም ቢሆን ወንድሞቻችን ናቸውና።

በሌላ ወገን የምንነግራችሁ ነገር ቢኖር በነገው እለት ከጠዋቱ 9:00 ሰዓት ላይ የፍርድ ቤት ቀጠሮ እንዳለ  ነው።  የተያዘው ቀጠሮ  ቦርዱ ለከሳሽ ጠበቃ ተጠይቆ አልሰጥም ያለውን መጠይቅ ዳኛው ትእዛዝ እንዲሰጥበት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቀደም ባለው የመጀመሪያው ቀጠሮ ላይ የቦርዱ ጠበቃ የተነሳው ቪዲዮ በመረጃነት አይገባብኝም ምስክር አይሰማም ብሎ የተከራከሩት በዳኛው ውድቅ መደረጉ የሚታወስ ነው።ዳኛው ይህ ክስ የመብት እንጂ የሃይማኖት ጉዳይ ምንም እንደሌለው ከመናገራቸውም በላይ ቪዲዮውም እንደመረጃ እንዲገባ  ምስክርም እንዲሰማ ማድረጉ ግልጽ ነው። የተከሳሽ ጠበቃ ተቃውሟቸው እንዳልሰራ ሲረዱ ፍርድ ቤቱን ሌላውን የፍርድ ቤት ክስ ያየው ዳኛ ይህንንም በተጨማሪ ይመልከትልን ምክንያቱም ጉዳዩን በሌላ መልኩ አይቶታልና ብለው በጠየቁት መሰረት፣ ዳኛውም የቀድሞውን ዳኛ አነጋግረው ፈቃደኛ ከሆነ ቢዛወር እንደማይቃወሙ ቃል በገቡት መሰረት ምን አልባት የቀድሞው ዳኛ ይህንን ለማየት እፈልጋለሁ ካሉ ሊተላለፍ እንደሚችል ጉዳዩን ከተከታተሉት ግለሰቦች መረዳታችንን ልናሳውቃችሁ እንፈልጋለን።  ይህ ክስ አባላትን ማባረር ከጀመሩ በኋላ የተመሰረት መብትን ለማስከበር የተመሰረት ክስ መሆኑም ለሁላችንም ግልጽ ነ ው።
ስለሆነም በነገው እለት ምንም ተፈጠረ  ምን
መተዳደሪያ ደንቡ ወደነበረበት ካልተመለሰ 
የተባረሩ አባላት ካልተመለሱ
የአባላት ክፍያ  ወደነበረበት ካልተመለሰ
አንዱ ልጅ ሌላው እንጀራ ልጅ መሆኑ ካልቀረ
የአባላት መብት ካልተጠበቀ
ፖለቲከኞች ከቤተክርስቲያን ውስጥ ፖለቲካቸውን ካላቆሙ
የምእመናንን ጥቅም አስከባሪ ቦርድ እስካልተቋቋመ
ብሎም
ባለፈው እንዳደረጉት ቦርዱ በመሰብሰቢያ አዳራሻቸው እነ አቶ ሃይሉ እጅጉን ጠርተው እየተሳደቡት ክስ ከመሰረቱት ውስጥ ነህና ካላረፍክ እንከስሃለን የክስ አጋሮችህንም አብረን ለፍርድ እናቆማለን እንዳሉት በተናጠል ማስፈራራት እስካላቆሙ ድረስ 
በቦርዱ ብሎግ መሳደባቸውን እስካልገቱ ድረስ
መታገላችንን  አናቆምም

ዳላስ ለመኖር ደግሞ  የቦርድ ደጋፊዎች ነን ባዮችን ፈቃድ አንጠይቅም።
ሚካኤል ለተገፉ እንጂ ለገፊዎች ይቆማል ብለን አስበንም አናውቅ።
የነገ ሰው ይበለን።


   





Tuesday, October 5, 2010

ለሱ ብርታት ለእኔ ጽናት

ከደከምኩብህ አበራታኝ፣
ከተደናቀፍኩ ሳልወድቅ አንሳኝ።
        ሰው ነኝና ድኩም ፍጥረት፣
        ወድቄ  እንዳልቀር እንደኩበት፤
ምርኩዝ ሁነኝ ጠባቂ፣
እረዳት ሁነኝ ጠያቂ።
       ለጠሉኝ ልብ ስጣቸው፣
      ብርታቱን አትንፈጋቸው።
እኔ ባሪያህ ደካማ ነኝ፣
ለመጽናናቱ ጉልበት ስጠኝ።
     እንደሞትክልኝ ለሃጥያቴ፣
     ይቅር እንዳልከኝ በድክመቴ፣
     አበራታኝ ይቅር ልበላቸው ካንጀቴ።
እኔን እንደወደድከኝ፣
እንድወዳቸው ጽናቱን ስጠኝ።
   ቸር ነህና  ይቅር ባይ፣
   ዳግም ምሕረትህ   ይታይ።
ቢበትኑ ስብስቡን፣
በዘር በጎሳ ቢለዩን፣
በፖለቲካ ቢያበራዩን።
    አምባ ገነንም ቢሆኑ፣
    ምሕረቱን ስጣቸው ይዳኑ።
የእሳት አለንጋ ሳይገርፋቸው፣
ሰይጣን ሳያቀሳቸው፣
ዲያብሎስ ሳይሰርጋቸው፣
የክሕደት ማቅ ሳይወርሳቸው፣
እባክህ ፈጣሪ መልሳቸው፣
የፍቅርን መንገድ አሳያቸው፣
ግፉ በዛ  አሁንስ ይብቃ በላቸው።
      ለእኔም ብርታቱን አትንፈገኝ፣
      ከውዳሴ  ፖለቲካ  አድነኝ፣
      በይቅርታህ ጀቡነኝ፣
      ሰይፉን ሳይሆን ፍቅሩን ስጠኝ፣
      እንደ ሰብአ ሰገል የብርሃን ጮራ አሳየኝ፣
      በጥንካሬዬ እንጂ በድክመቴ አትዳኘኝ፣
      አምላኬ ለሱ ብርታት ለኔ ጽናቱን አከናንበኝ።

Saturday, September 18, 2010

በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው ቁጥር ፵፫

ይህንን የቅዱስ ያእቆብን ጥቅስ እንደ እርእስ የመረጥነው  ሰሞኑን እየተካሄደ  ያለውን የምሽት መንፈሳዊ ጉባኤ ተካፍለን ካዳመጥነው መንፈሳዊ ትምሕርት በመነሳት ነው። ጉባኤው ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ባሻገር ባለው የኬንዋውያን ቤተክርስቲያን እየተካሄደ ያለ ሲሆን፤ ቅዳሜ ማታና እሁድ ማታም እንደሚቀጥል ለመረዳት ችለናል። ከሁለት መቶ ምእመናን በላይ ተሳታፊ የነበሩበትን ይህንን ጉባኤ ስንካፈል የተሰማን ሐዘን የጠለቀ  ነበር። በፖለቲካው ብቻ  ሳይሆን በሃይማኖትም መለያየታችን የሚያሳዝን ሆኖ ስላገኘነው። "ፈተና የሚመጣው እኮ ሰይጣን ጥንካሪያችንን ሲያይ ነው" ብለው የሰበኩት መምህር በተለይ ሰይጣን እንደማንበገር ሲያውቅ የጭቅ ጅራፉን ያወርደዋል ሲሉ ብዙ ነገር ታወሰን። እዚህ አገር እርችት ሲተኮስ ድብልቅልቁ የሚወጣው እኮ መጨረሻው ላይ ነው ብለን አሰብን። ታዲያ በአሁኑ ሰዓት በአንድ ወገን  በጥቂት የቤተክርስቲያን አመራር ክፍልና በጣት በሚቆጠሩ ደጋፊዋቻቸው በአንጻሩ መብታችንን አናስደፍርም በካህን ታጅበን እንጂ በፖሊስ ተከበን አናመልክም በሚሉ ምእመናን መካከል የተጀመረውን መተናነቅ ስናስተውል  እውነትም ፈተናው አስከፊ እንደሆነ ታየን። ከግንድ የተገነጠለ  ቅርንጫፍ እንደሚደርቅ  አትጠራጠሩ ብለው ያስተማሩት አባት ደግሞ ለመለምለም የወይን ዛፉ አካል መሆን እንዳለብን በምሳሌ ከማስተማራቸውም በላይ፤ የማይሆን የዛፍ ተቀጽላም ከዚያም አልፎ ተገድራም መሆን እንደሌለብን ሲያስተምሩ የሚያስተምሩት የኛን  ችግር ተረድተው ይመስል ነበር። ቆይተን እንደተገነዘብነው ግን ተናጋሪው ያስተምሩ የነበረው ከሃይማኖት መራቅ እንደሌለብን ሆኖ አገኘነው። የወንጌል ትልቁ ጉልበቱ ደግሞ በተሰማ  ቁጥር ከራስ ችግር ጋር፤ ከምናየው ጋር ሁሉ መመሳሰሉና ለዛም መልስ ይዞ መገኘቱ ነው። ታዲያ ቤተክርስቲያን እንደሌለን ተከራይተን ክርስቲያን እንዳልሆንን ሁሉ ተለያይተን መገኘቱ ካስደሰተን ያስተማሩን አባት እንዳሉት እራሳችንን ዞረን መመልከት ሊኖርብን ነው። እኛ ይህንን ገምግመን መስቀል ካልገዛው ሕግ ይዳኘው ብለው የተነሱትን ደግፈናል። የለም ካህናት መሰደብ አለባቸው፤ ምእመናን መታሰር ይኖርባቸዋል፤ የተዋጣው ገንዘብ ካለ እስኪያልቅ እንዋጋለን ሲያልቅ ቤቱን እንሸጣለን ከሚሉት መወገን የምንል ካለን መወገን። ካልሆነ እንደ ክርስቲያንነታችን  ባመንበት ጸንተን በእምነታችን ሳንደራደር ለመብታችን ቆመን  የሕግን የበላይነት የተቀበልን መሆን ይኖርብናል ብለን የምናምን ተጠናክረን መነሳት ይኖርብናል እንላለን። የኛ ችግር በመብት እረገጣ ላይ ነውና ለዚህ ደግሞ ከሕግ ውጭ መፍትሄ ይኖራል ብለን አናምንም። የሃገራችን ልማድ ተከትለን  በሽማግሌ ለመፍታት ካንዴም ከአራት ከአምስት ጊዜ በላይ እንደተሞከረ ሁላችሁም የምታውቁት ጉዳይ ነው። ከሳሾቹ ችግሩን ለመፍታት ሽማግሌዎችን አክብረው ተቀምጠው ተወያዩ። የቤተክርስቲያን አንባገነን መሪዎች ግን ገደል ግቡ አሉ። ይባስ ብለው ፖሊስ ቀጥረው ውሻ አሳጅበው ሊያስፈራሩን ተነሱ። በብሎጋቸው ላይ የቤተክርስቲያኑን አንጋፋዎችና መስራቾች አንተ  እያሉ መዝለፍ ጀመሩ። ማ ከማ ጋር ወሲብ እንዳደረገ ማ እንዴት ልጅ እንደወለደ ማ ምን የፖለቲካ አመለካከት እንዳለው ዘገቡ። ካሕናቱን እንደ ሰፈር ዳንዴ ፈረጁ በወሲብ ከባለትዳር ግለሰብ ጋር በመጠርጠር ስም አጠፉ። ይህንን ሲያደርጉ ትዳር እያፈረሱ ቁርባንን እያረከሱ መሆኑ ግን አላስጨነቃቸውም። ዘር ቆጥረው የመንግስት ደጋፊ ናቸው ብለው ትላንት አብረዋቸው የነበሩትን እየተገባበዙ የበሉበትን ሳህን እየሰበሩ የጠጡበትን ጽዋ እየደፉ ታዩ። መንግስትን መደገፍ መብት መሆኑ ግን አልተገለጸላቸውም። ይህን ሁሉ አድርገው ታዲያ  ታዛቢያቸው በዛ እንጂ ደጋፊያቸው እንዳልጨመረ በሚካኤል ስም መመስከር ይቻላል። ያ  አልበቃቸውም

ካህናትን ሊያዋርዱ ተነሱ ከሸፈ።
በዘር መጡ ተመቱ።
በፖሊስ መጡ ተረቱ።
በፖለቲካ ተንቀሳቀሱ ፈራረሱ።
በገንዘብ ተመኩ ቋቱ እየደረቀ  መጣ።
በጉልበት መጡ ጉልበት የሚካኤል ሆነባቸው።
ዛሬ የቀራቸው ለቡድናቸው የሰጡት "የሚካኤል ሰይፍ" የሚለው ስም ብቻ ነው። ያ ደግሞ  የድሮውን የቻይና  ግሩፕን ያስታውሰናል። 
ወንድሞችና  እህቶች
"ከራበው ልጄ  ይልቅ ለጠገበው ልጄ  አስባለሁ"  ያሉት ዳላስ ነዋሪ የሆኑ ቤተሰቦች አልነበሩም። አባባሉ የቆየ  ነው ለማለት ነው።የራበው ልጅ እቤት ተኮራምቶ ይቀመጣል የጠገበው ግን ማን አለብኝ ብሎ ይደባደብና  ወይ ነፍስ ያጠፋና ቤተሰቡን ችግር ላይ ይጥላል ለማለት ነው። እዚህም በዳላስ አካባቢ ታዲያ ከላይ እንደጠቀስነው ሰላም ሲሰፍን እንቅልፍ የሚነሳቸው የሕዝቡ መፋቀር የሚያናድዳቸው፡ ከመጋረጃ ጀርባ ተደብቀው ሲናገሩ በድምጻቸው የማይታወቁ፤ በብእራቸው የማይለዩ፤ በተግባራቸው የማይፈረጁ የሚመስላቸው ግለሰቦች ከትላንትናው ቁጥራቸው እየመነመነ እርስ በርሳቸው እየተወነጃጀሉ ለመሆኑ ብዙ ፍንጭ እየየን ያለ  ይመስለናል።  በዚህ በከተማችን ለእምነታቸው የቆሙ ትክክል አይደለም ብለው ያመኑትን የተናገሩ ዲሞክራሲ በሰፈነበት አገር መብታችንን አናስደፍርም በጥቂት አንባገነኖች አንገታችንን አንደፋም መብታችንን  የሃገሩን ሕግ ተጠቅመን እናስከብራለን ባሉ "ቅዱሳን ነን"በሚሉ ተሰድበዋል "ከኛ ወዲያ ክርስቲያን የለም"  በሚሉ ተዘልፈዋል። ያም ሆኖ ግን የተዋረዱት ሰዳቢዎቹ እንጂ የተሰደቡት አልነበሩም።

ባለፈው እንደተናገርነው ሁሉ ማንነታቸውን እያወቅን ስም ጠርተን፤ ድክመታቸውን ፈልፍለን፤ የመኝታ ቤታቸውን ምስጢር አውጥተን ለአንባብያን አላቀረብንም። ያን ባለማድረጋችን ፈሪዎች ተብለን ይሆናል። እኛ ግን በደረቅ መሬት በመጓዛችን እንደነሱ በማጥ ውስጥ አልዳከርንም። ለቤተክርስቲያንናችን በ ሺህ የሚቆጠር ገንዘባቸውን ያፈሰሱ ምእመንን በስድብ ውርጅብኝ የገረፏቸው ግለሰቦች እነማን እንደሆኑ እናውቃለን። ግን ማንነታቸውን በመናገር እነሱን ማስተዋወቅ ደግሞ ለነሱ ክብር እንደሚሆን ስለተሰማን እንዳላወቅን አለፍናቸው። ባለፈ በመረዋ እትምታችን እንደተናገርነው ለአንባብያን ፍንጭ እንዲሆን የተሰደቡትን አባላት ስትለዩ የሚሳደቡት እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ደቂቃ አይፈጅባችሁም። እኛ መልእክቱ እንጂ መልእክተኛው ምን ያደርጋል በሚል እራሳችን ማስተዋወቅ አልወደድንም የመደበቅ ፍላጎት ኖሮን እንዳልሆነ ግን ምስክራችን ሚካኤል ነው። በምንም ሰዓት በሃሳብ ላይ በመታገል እንጂ በስድብ ለውጥ ተገኘ ሲባል ሰምተንም አይተንም  አናውቅምና መሳደብን እንደመሳሪያ መጠቀም አልፈለግንም። መኪናችን ቢሰበር የሚጎትትልን ሰው እናጣለን ብለን ሰግተንም አናውቅ። እንጀራ ንግድ ውስጥ ስለሌለንበት ደግሞ የደንበኛ ልምምጥ የለብንም። ገንዘቡና ጊዜው በተገኘ እንጂ አውሮፕላን ጣቢያ የሚያደርሰን ይጠፋል ብለን አንጨነቅም። ለቦርድ የመመረጥ ፍላጎት ስለሌለን ማን ይመርጠናል ብለን አንሰጋም። ሌሎች እንደሚያደርጉት የራሳችንን የቤተሰባችንን ገድል እያወራን ቅዱስነታችንን እየተናገርን ለምርጫ እንዳትረሱን አንልም። የቤተክርስቲያን ስራ በልመና ለብቁዎች የሚሰጥ እንጂ በቅስቀሳ ምረጡኝ ሲባል ጥቅም አለበት እንዴ? ሊያሰኝ ይችላልና።
አገር ቤት ያልተሳካ ፖለቲካ ዳላስ ያለውን ምእመን በማመስ በለስ ሊቀናን ይችል ይሆናል ብሎ  ማለም ደግሞ በፖለቲካ አለመብሰል ይመስለናል።

የሚያስጨንቀን ነገር ቢኖር ያልነበሩ ሲመሰክሩ ያልከፈሉ የከፈሉትን አባቶች ሲያዋርዱ ያደጉበት አስነዋሪ ጠባያቸው በስተርጅና  ሲያገረሽባቸው ስናስተውል ነው። 

የሚያስጨንቀን "ክርስቲያን ነን" እያሉ አዛውንቶችን፤ መንፈሳውያን ነን እያሉ ወንድም እህቶችን የመንደር ዱርዬ እንኳን በማይጠቀምበት አስነዋሪ ቃላት ሲሳደቡ መስማታችን ነው።
እኛ የሚያስጨንቀን በሕዝብ ገንዘብ ንጉሥ ሆነው ባልከፈሉበት አዛዥ ባላጠራቀሙት በታኝ ባልሰበሰቡት ወሳኝ መሆናቸው ነው።የሚያስጨንቀን ክርስቲያንን አባረን የክርስቲያን ስብስብ  ነን ሲሉ ስንሰማ ነው።

የሚያስጨንቀን በሬ  ወለደ  ብለው ሲያወሩ ነው።

ትላንት ለኢትዮጵያ  ቀን እንዳትሄዱ ሲሉ ከርመው፤ የኢትዮጵያ  ቀን ሳይሳካ  ቀረ  ሲሉ ሰንብተው፤ መረዋ የነበረውን ለአንባብያን ሲተነትን ገንዘብ ያዋጡትን ግለሰቦች ስም ሳይቀር ሲናገር ውሸታቸው መጋለጡን ሲገነዘቡ አቶ ሰይፉ ካሉበት አቶ  መደቅሳ ከገቡበት ችግር የለብንም ብለው መናገር ጀመሩ። ባንድ አፍ ሁለት ምላስ ይሏችኌል ይህ ነው። የወያኔ ቀን ነውና እንዳትሄዱ ብለው በጻፉት ብእራቸው፤የቅዳሜው እለት አልተሳካም እሁድም የተገኙት የእድር ሰዎችና ቤተሰቦች ብቻ ናቸው እንዳላሉ መረዋ ገንዘብ ያዋጡትን ከፊል ስሞች አውጥተው ሲያዩ ተደናገጡ። ግለሰቦቹን እንዳይሳደቡ ደግሞ ገንዘብ አዋጡ ተብለው ስማቸው ከተጠቀሰው አንዳንዶቹ በቤተክርስቲያኑ ጉዳይ ቢያግዟቸውም በመረዳጃ መሃበሩ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አመለካከት እንደማይጋሩ የተገነዘቡት ሆነ። ታዲያ እነሱን ቢሳደቡ ጸሐፊዎቹ እነማን እንደሆኑ ስለሚያውቌቸው የሚመጣባቸው ችግር ስለታያቸው ሕዝቡም እየሸሻቸው መምጣቱን ሲገነዘቡ ተገልብጠው መልካም ጅምር ነው ማለት ጀመሩ። ሃሌ ሉያ። የሚደገፍ አቋም ነው። ይህንን ስላደረጉ ደግሞ  እኛ እነሱ በሄዱበት ጎዳና በምንም አይነት አንደማንጔዝ ቃል እንገባላችኋለን። የኛን መንገድ ሲቀላቀሉ ደግሞ ደስተኛ እንሆናለን እንጂ ለምን አጣበባችሁን ብለን አንከፋም። በብሎጋቸው የጻፉትን አንስማማበትም አቶ ዮሴፍ ላይ የተጻፈው የኛ አቌም አይደለም አሉና አረፉት። አሁንም ግን ስለ ጋሼ ሃይሉ የተጻፈውን አልኮነኑም። ስለፍቅረማርያም ያወሩትን አልኮነኑም፤ ስለ  አዜብ የተሳደቡትን ይቅርታ  አልጠየቁበትም፤ ስለብዙአየሁ ያወሩትን አላፈሩበትም፤ ስለ አቶ ጌታቸው ትርፌ በተደጋጋሚ ያወጡትን እንደኮሩበት ነው። ስለፈትለወርቅ  የተናገሩት አላሳፈራቸውም። ስለ ተፈራወርቅ የጻፉትን ይኮሩበታል ማለት ነው። ስለአቶ  ተኮላ የዋሹትን አልተሸማቀቁበትም። ጥሩአየር ሲዘልፉ ምን ማለታቸው እንደሆነ እራሳቸውም ግራ የተጋቡ ለመሆኑ ያወቁት አይመስለም።  አቶ ግርማቸውን በመሳደባቸው አሁንም ትልቅ የሆኑ እንደመሰላቸው ነው። ስለሙላው ሲዘባርቁ ያሸነፉ እንደመሰላቸው ነው። ስለ  ጸሃይ ጽድቅ ወንጀል ሲያወሩ የሚያስከትለው  ምን ይሆን? ብለው አልነበረም። ከሁሉም የሚገርመው ዳዊት አለማየሁን በዘሩ ሳይቀር ተሳድበው እንቅልፍ ወስዷቸው ካደረ ወንድሞቼ  እነዚህ ሰዎች ወንጀለኞች ናቸው። ብዙ መጥቀስ ይቻላል። ስለተሳደቡ ግን አላሸነፉም እንደምታዩት እየተሸነፉ መጡ እንጂ። ከሁሉ የገረመን ለቤተክርስቲያኑ ገነዘባቸውን ያፈሰሱት አቶ  ሃይሉና  አቶ  ምናሴ የስድብ ውርጅብኝ ሲያወርዱባቸው ተዋቸው እንሱን በፍቅር መዋጋት ብቻ ነው ያለብን ብለው ሲናገሩ ስንሰማ ነው። ያንዳንዱን የመንፈስ ደካማነት በማየት የሚያዝን ሰው በሌላው ጥናት ይጽናናል ማለታችን ነው።
ዛሬ እርስ በራሳቸው እየተላተሙ ነው። ነገ አቀርቅረው እንደሚቀሩ ደግሞ ምንም ጥርጥር የለንም።
የሳምንት ሰው ይበለን 

Saturday, September 11, 2010

መልካም አዲስ ዓመት

መልካም አዲስ ዓመት
                              ዘመነ ማርቆስ ተሻረ፤
ዘመነ ሉቃስ ተሾመ።    

አዲሱ ዘመን ሐሰት የሚጨነግፍበት
እውነት የሚለመልምበት ዘመን እንዲሆንላችሁ መርዋ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።

Wednesday, September 8, 2010

ያያችሁት ሰው ሳይሆን ጥላ ነው ለሚል ሰው መድሃኒቱ የምን ጥላ? ብሎ መጠየቅ ብቻ ነው። ቁጥር ፵፪

በስደት ላይ 30 ዓመት እየሞላን ነው ብሎ  መናገር የሚያስደነግጠው አዳማጩን ሳይሆን ተናጋሪውን ለመሆኑ ቋሚ ምስክር ነን። ምን ስትሰሩ ከረማችሁ ለሚሉት አጥጋቢ መልስ መስጠት ያስቸግራልና። ስለ እውነት ለመናገር እንደ ቀልድ ያለፈው የስደት ዘመን የራሱ የሆነ  ውጣ ውረድ ነበረበት። ዛሬ እንደቀልድ የምናየው ነገር ትላንት የተራራ ያክል አስቸጋሪ እንደነበር ሲነገር ቀልድ ሊመስል ይችላል። ዛሬ የምንምነሸነሽበት ነፃነትና የግለሰብ መብት ትላንት በነበሩ የአሜሪካውያን ታጋዬች ደም የተገነባ መሆኑን መቀበል የሚከብደን ብዙዎች ብንኖር አይገርምም። በወቅቱ የነበረውን ዘረኝነት በምስክርነት የሚናገሩ ሰዎችን ስንሰማ እንኳን ድግግሞሽ ነው በማለት ማዳመጡ ሁሉ የሚያስጠላን  ልንኖርም እንችል ይሆናል።  የራሳችንን ጉብዝና እያጎላን የሌላውን ስንፍና መናገራችንም ያለ እውነታ  ነው። በዚህ በምንኖርበት አገር ዘረኝነት መኖሩን ለመቀበል ደግሞ  እራሳችን ችግር ውስጥ ገብተን መገኘትን አለብን። ካልሆነ የሌላው ስንፍና  እንጂ ለምን እኛ ከባሕር ማዶ  መጥተን ከነዋሪው መሰላችን የተሻለ  ኑሮ እንኖራለን ብለን የምንከራከር እንዳለን መካድ የሚያስገምተው እራሳችንን ብቻ ነው።

ዛሬ ይህንን ለማንሳት ያነሳሳን ሁሉም ነገር ጊዜውን እየጠበቀ ትላንት ሌላው እደረሰበት ዛሬ እኛም ለመድረሳችን ብልጭታ  እያየን በመምጣታችን ነው። የጽሑፋችን መነሻ  የሆነን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ  ተደርጎ  የነበረው ፱ኛው የኢትዮጵያ ቀን ላይ ያየነው ቅንነት የተሞላበት መሰባሰብ ነበር። በዓሉን ለማክበር የመጡት በሞላ አንድ ዓይነት አመለካከት አንድ ዓይነት የፖለቲካ አቋም ነበራቸው  ለማለት  ባንደፍርም መደረግ አለበት በሚባለው እቅድ ላይ ግን ምንም ልዩነት እንዳልነበረ በስፍራው ነበርንና ምስክርነት መስጠት እንችላለን።

ባለፈው በመረዋ እትምታችን ስለ ቅዳሜው የዘገብነው  እንዳለ ሆኖ እሑድ እለት የተገኘው ሕዝብ ቁጥር ከቅዳሜው የላቀ  ከመሆኑም በላይ በሁለቱ ቀን ጊዜ  ውስጥ $78,000  ለማዋጣት ቃል መገባቱን ግማሾቹም መክፈል መጀመራቸውን ስናይ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበር አዳራሽ እውን እንደሚሆን ለመቀበል ጊዜ አልወሰደብንም።

ከሁሉም በላይ የሚካኤል ቤተክርስቲያን ሲገዛ በግንባር ቀደምትነት ያስተባበሩትና እዳው በጥቂት ዓመታት ተከፍሎ እንዲያልቅ ያስደረጉት አቶ ሰይፉ ይገዙ በፈቃደኝነት የዚህም የመረዳጃ ማህበር የሕንፃ ኮሚቴ አባል መሆናቸውን ስናይና በእለቱ ይህ ትላንት መደረግ የነበረበትን ሕልም ዛሬ እውነት ለማድረግ የተቻላቸውን ለማድረግ ቆርጠው መነሳታቸውን ቃል ሲገቡ ስንሰማ ይቻላል የሚለው መፈክር በጆሮአችን መደወል ጀምሮ ነበር። የኮሚቴው አባላት ስም ሲጠራም የጅምሩ እውነተኛነት የባሰውን እየጎላ  መጣ። እንዴው የመሃበሩን ሥራ  መጋፋት ነው ባትሉን ለአንባብያን ማንነታቸውን እናስተዋውቃችሁ።

1  አቶ  ሰሎሞን  ሐመልማል (የቦርዱ ተወካይ)
2  አቶ ሰይፉ ይገዙ
3  አቶ  በትሩ ገብረእግዚአብሔር
4  አቶ  ግርማቸው አድማሴ
5  ወይዘሮ ተዋበች
6  አቶ ሚደቅሳ በየነ
7  አቶ  መላኩ አቦዝን
8  አቶ ዳንኤል ግዛው   እንደሆኑ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን።

በዚህም እለት በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ቃል የገቡትንና  የከፈሉትን ሥም ዝርዝር ከምናስታውሰው  ብንጠቅስ ስብስቡ የተለያየ  ክፍልን ያቀፈ  ለመሆኑ ግንዛቤ  የሚሰጥ መሰለን።

አቶ ብርሃን መኮንን እና ባላቤታቸው ወይዘሮ ተዋበች   $10,000
አቶ ኤልያስ                                                       $6,000
አቶ  ሃይሉ እጅጉ                                                $5,000
አቶ  ብዙአየሁ      (በ city shuttle )                     $5,000
አቶ ሙላው ወራሽ                                              $5,000
ዶክተር ስዩም                                                                               $1,000
አቶ ሃብቴ                    (በማሩ ግሮሰሪ ስም)               $1,000
አቶ መንግስቱ ሙሴ   (በአበባ  ግሮሰሪ ስም)              $1,000
አቶ  ሰይፉ ይገዙ                                                $1,000
አቶ ግርማቸው አድማሴ                                       $1,000
አቶ አበበ ጤፉ                                                   $1,000
አቶ መላኩ አቦዝን                                               $1,000 ለማዋጣት ቃል መግባታቸውን ስንነግራችሁ በርካታ ግለሰቦች በነፍስ ወከፍ $500 - 100  መለገሳቸውንና ቃል መግባታቸውን ለማየት ችለናል። በአጠቃላይ በበዓሉ ላይ በድምሩ $78,000   ቃል እንደተገባ ገሚሱም ገቢ እንደሆነ ከኮሚቴው በተሰጠው ገለጻ ለመረዳት ችለናል።
ታዲያ  እነዚህ ግለሰቦች በሙሉ የፖለቲካ ሰዎች ወይም ስብስቡን  እንደሚቃወሙት  ግለሰቦች አባባል አገር ቤት ካለው መንግስት ድርጎ ፈላጊዎች ናቸው ብሎ መወንጀል ከተቻለ  ፍርዱን ለአንባብያን እንተዋለን::

በወቅቱ ለበዓሉ ድምቀት የሰጡት የጋርላንዱ ከንቲባ የመረዳጃ መሃበሩ ያዘጋጀውን ሽልማት ለተሸላሚዎች ከመስጠታቸውም በላይ በግላቸው መዋጮ ማድረጋቸውን ሳንናገር አናልፍም። አርክቴክ የሆኑትና  መሃበሩን በቦርድ ተመራጭነት የሚያገለግሉት  አቶ አብርሃም ተሰማም ለዚህ ሕንጻ መሳካት ይረዳ ዘንድ የሕንጻውን ንድፍ በነጻ እሰራለሁ በማለት በሺህ የሚቆጠረውን ወጪ ገምድለው ጥለውታል። ሁኔታውን የታዘቡት የእለቱ የኪነት አቀንቃኝ አቶ ይሁኔ በላይም ለሚመጣው የገንዘብ መዋጮ ስብስብ ቀን በነጻ እንደሚዘፍኑ ለተሰበሰበው ሕዝብ ቃል ገብተዋል።

በማጠቃለያ እንደቆየው የቻይኖች አባባል "የሺ ማይል ጉዞ  በእርምጃ  ይጀመራል" ነውና ባለፈው በታዘብነው ግን ከማይል በላይ መጓዝ እንደተቻለ  ለመመስከር ችለናል።

ሰው አልነበረም ለሚሉት ታዲያ እንደ አርእስቱ ሁሉ ይህ ታዲያ ከየት መጣ? ልንልላቸው እንወዳለን

በዚህ አጋጣሚ ለመላው የስልምና ተከታዬች መልካም የረመዳን በዓል በመረዋና  ባንባቢዎቻችን ስም እንመኝላቸዋለን::

የታሰበውን  ለማስፈጸም ይርዳን እያለ መረዋ ለዛሬ በዚህ ይሰናበታል።

Sunday, September 5, 2010

ከማያዳምጥ ጋር መወያየት ትርፉ የእራስን ቃል መልሶ ማዳመጥ ብቻ ነው። ቁጥር ፵፩

ደህና  አደራችሁ ሳይሆን "ደህና ያደራችሁ አላችሁ?" ብለው ይጠይቁ የነበሩ ግለሰብ እንደነበሩ ያወጉኝ አዛውንት በገበያ መሃል ቀን በቀን ፋኖስ ይዞ ሲጓዝ የነበረን የድሮ ፈላስፋ ምን እየሰራህ ነው? ተብሎ ሲጠየቅ  ሰው እየፈለግሁ ነው ማለቱንም እያስታወሱ ነበር። እንዴው ለልማዱ እንዴት ከረማችሁ?እንበል እንጂ ያለፉት ሳምንታት እንዲሁ ሕብረተሰባችን እየታመሰ ተሳዳቢዎቹ ስድባቸው አልቆ እባካችሁ የምንዘልፈው አልቆብናልና ያላችሁን ላኩልን እያሉ ሲማጸኑ የሰማንበት ወቅት እንደነበረ ሁላችሁም የታዘባችሁት ጉዳይ ነው።

በሌላ ወገን ደግሞ ይሳደቡ የነበሩት ስድቡ ማንንም እንዳልሳበላቸው ሲረዱ አሁንም ከመንበሩ ሆነው ከደሙ ንጹሕ ነን ማለታቸውን ስንሰማ፡ አልተደነቅንም። ይህ እንደሚሆን እናውቅ ነበርና። ሰዳቢዎቹን ይደግፉ የነበሩት ሁኔታው መስመር ማለፉን ሲገነዘቡ ይህ መቆም አለበት በማለታቸው እነሱም የስድቡ ጅራፍ እየደረሳቸው ለመሆኑ በአካል ቀርበው ያነጋገሩን እንዳሉ ስንነግራችሁ እሰየው ብለን አልነበረም። ስንሰደብ የተሰማንን እያስታወስን ድጋፍ ሰጠናቸው እንጂ። እኛ ደስተኛ የምንሆነው አሁንም የስድብ ሙዚቃ የሚማርካቸው ዘላፊዎች በተራቸው አሁንስ በቃን ሰውም አልወደደልን ፈጣሪንም አስቀየምን የሚሉበት ቀን ሲመጣ ብቻ  ነው። ያ ደግሞ እሩቅ እንዳልሆነ  ብዙ ፍንጭ እያየን ይመስለናል።

ሁላችሁንም ልንጠይቅ የምንወደው ለስድባቸው ጆሮ በመንፈግ የሚሉትን ባለማራባት አዳማጭ እንዲያጡ ለማድረግ እንድትተባበሩን ሲሆን፤ አድማጭ ሲያጡ እርስ በርሳቸው እየተሰዳደቡ እንደሚለያየዩ እርግጠኛ በመሆን ነው። ገበያተኛ የሌለበት ጠጅ ቤት ሰካራሙ ሰራተኛው ብቻ ይሆናል ይባላልና። 

በቤተክርስቲያናችን የስደት ሲኖዶስን ለማስገባት የሚደረገው ጥድፊያ እየታየ  ሲሆን፤ ባለፈው እንደነገርናችሁ ድቁና ለማግኘት ወደ ሂውስተን ተልከው የነበሩትን ሕጻናት ለድቁና መብቃታቸውን በደብዳቤና በስልክ ያረጋገጡት የሚካኤል ካህን ይህንን ሲያደርጉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ለናንተ  መንገር አይኖርብንም። መልሱ ለሁላችሁም ግልጽ ነውና። በደብዳቤ  እውቅና  ሰጥቶ እከሌን ሹምልኝ እያሉ እኔ ገለልተኛ ነኝ ማለት ደግሞ  "አጨስኩ እንጂ አልዋጥኩትም"  የሚለውን  ያለፈ የአሜሪካ ባለስልጣን አባባል ያስታውሰናል። ይህ ቤተክርስቲያን በሬሳችን ላይ እንጂ በሕይወት እያለን ለስደት ሲኖዶስ አይሰጥም ይሉ የነበሩትን አዛውንቶች በሉ መሞቻችሁ ይኸው ተቃረበ ለማለት አንወድም፡ መሞታቸውን አንፈልግምና። ይልቁንስ ድቁና የሚሰጡት የስደቱ ሲኖዶሶች ከሆኑ ልጆቻችንን አንልክም ብለው አቋም የወሰዱትን ቤተሰቦች መረዋ በዚህ አጋጣሚ  ስም ሳይጠራ አድናቆቱን ሊገልጽ ይወዳል።    

በሌላ መንገድ ተሳዳቢዎቹ የመሳደብ መብት እንዳላቸው የአሜሪካን አገርን ሕገ መንግስትን በመጥቀስ በተደጋጋሚ ሲናገሩ አድምጠናል። እንዴው አተካሬ  ላለማብዛት ልንተወው ፈለግንና አላስችል አለን። አንድ ሰው በሕግ እራስን ለመከላከል መግደል እንደሚችል ተደንግጓል ያ ማለት ግን ሰው መግደል ይቻላል ማለት አለመሆኑን ቢገነዘቡ መልካም ነው። 

ስለፍቅር የሚሰብኩ ቤተክርስቲያን ለምን ይከሰሳል የሚሉ የስደት ሲኖዶስም ደጋፊ አለውና ስለነሱ ባትናገሩ ጥሩ ነው ብለው የድርጅታቸውን ኦፊሻላዊ የአቋም መግለጫ የሚያስተጋቡ አሁንም ነገሮች በውይይት መፈታት አለባቸው የሚሉ መጣጥፎችንም ተመልክተናል። "በፍርድ ቤት ሰላም አይመጣም ማንም ቢያሸንፍ ሁላችንም ተሸናፊዎች ነን"  ብለን በመረዋ ተከታታይ እትምቶቻችን የምንናገረው ስለነበረ  እንኳን ለዚህ አበቃችሁ  እንኳን እውነታው ተገለጸላችሁ ከማለት በስተቀር አባላችንን ኮረጁት  ብለን አልተናደድንም።

ለናሙና ያክል ካለፈ መረዋ  እናካፍላቸው።

........አሁንም ለማንም ይፈረድ ለማንም ሁላችንም ተሸናፎዎች ነን ብለን እናምናለን። ፍርድ ቤት ይፈርዳል ግን ለማንም ይፍረድ ለማን አንድ እንሆናለን ወይ?ነው ጥያቄው። የተፈረደለት ይፈነጥዝ ይሆናል፤ ሰላም ፍቅር መጣ ማለት ግን አይደለም። ሰላም የሚፈጠረው፤ አንድነት የሚመጣው መነጋገር ሲቻልና ልዩነቶችን በጋራ ተወያይተን መፍትሄ ስናገኝላቸው ብቻ ነው።

ሴትዬዋ እርጉዝ ነች እሚለው ላይ ከተስማማን፤ መውለዷ የግድ ነው እዛ ላይ መከራከር አያስፈልግም የሚያዋልዳት ዶክተር የሚረዳት፤ ሆስፒታል እስካለች ጊዜ ብቻ ይሆናል። ወልዳ እንዴት ማሳደግ ትችላለች እሚለው ላይ ግን የዶክተሩ ሚና አይኖርም ለማለት ነው። በዛ ላይ ሚና መጫወት የሚችሉት ቤተሰብና ዘመድ ጔደኛና የሰፈር አዛውንቶች መሆናቸውን መካድ እንዴት ይቻላል? ካልተግባባን ሌላ ችግር አለ ማለት ነው። ስለሆነም በቤተክርስቲያናችን ሰላም መውረድ የሚችለው ሁላችንም ከልህና ከቁጭት ወጥተን በመነጋገርና በመመካከር ብቻ ነው። ወንድሞችና እህቶች ይህ የእምነት ስብስብ መሆኑንም አንዘንጋ።

በሌላ እትምታችን ደግሞ በመረዋ ቁጥር  ፲፫ ።

1 ሕጉ ወደ ነበረበት መመለስ አለበት
2 አባላት ያለምንም ጥያቄ መክፈል የሚችሉትን እየከፈሉ መመዝገብ አለባቸው።
3 የቦርድ አባላት ነን ባይ አንባገነኖች ሕዝቡ ለመረጣቸው ጊዜአዊ ኮሚቴ አስርክበው መውረድ አለባቸው።
4 የሚደረገው ስብሰባ በገለልተኛ ምእመናን መመራት ይኖ ርበታል ብለን እናምናለን።

በተጨማሪም በመረዋ ቁጥር ፲ " ዝምታ በራሱ ተቃውሞ ነው" የሚለውን በከፊል እንጥቀስ።

ቤተክርስቲያናችን ወደ መፍረሱ እየተቃረበ ለመሆኑ ሁሉም የተስማማበት ጉዳይ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት። ይህንን መጥፎ ሂደት ለመግታተ የሚቻለው የሚከተሉት ማረሚያውች ባፋጣኝ ሲደረጉ ብቻ ነው ብሎ ያምናል።
1 ቦርዱ በጊዚያዊ ኮሚቴ ሲተካ
2 የቀድሞ አባላት ወደ አባልነታቸው እንዲመለሱ ሲፈቀድ
3 ተቀየረ የተባለው የአንባገነን ሕግ ተሽሮ ወደ ድሮው ሕግ ስንመለስ
4 ቤተክርስቲያኑ የአምልኮ እንጂ የፖለቲካ ስፍራ መሆኑ ሲቆም
5 የእምነትን ጉዳይ ካህናቱ ብቻ መምራት ሲችሉ
6 የቤተክርስቲያን ገንዘብ የሰረቁ ምህረት ሲደረግላቸው ብቻ ነው ብለን እናምናለን።
ይህ ካልሆነ ቀጣዩ ትግል በዝምታ መሆን አይችልምና ዝምታ በራሱ ተቃውሞ መሆኑ ቢገባንም ተሰብስበን በመነጋገር መፍትሄ መፍጠር አለብን በማለት ጥሪ ማድረግ እንወዳለን። "  የጥቅሱ መጨረሻ 

ይህ ታዲያ የመረዋ የቆየ  አቋም ብቻ  ሳይሆን አሁንም የምንታገልበት መርህ መሆኑን በ ድጋሜ ማስረገጥ  እንወዳለን።

ከቤተክርስቲያን ባሻገር በትላንትናው እለት 9ኛውን የኢትዮጵያ ቀን ለማክበር ሄደን ጥሩ ምሽት ማሳለፋችንን ስንመሰክር፤ የዳላስ ፎትዎርዝ አካባቢ ፍልሰታቸው ከኢትዮጵያ  የሆነ ሁሉ የሚገናኙበት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለመገንባት የተጀመረው ሥራ ግቡን እንደሚመታ ከኮሚቴው አባላቱ ገለጻና  በወቅቱ ከነበረው የሕዝብ የገንዘብ ችሮታ እሽቅድምድሚያ በመነሳት ድምዳሜ ላይ ደርሰናል። መረዋም የኮሚቴው ጥረት ግቡን  ይመታ  ዘንድ ሁላችንም መተባበር እንዳለብን ሊያሳስብ ይወዳል። ባንሳሳት በውቅቱ ቃል የተገባው ከ $50000 በላይ ገንዘብ በጥቂት ጊዜ ውስጥ የእጥፍ እጥፍ እንደሚሆን  ጥርጥር የለንም።

እንዲሁ ካካባቢው ሳንወጣ በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በምእመናን የተቋቋመው የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ልሳን የሆነ  ብሎግ መፈጠሩንና  ብሎጉም በጅምር ላይ መሆኑን የደረሰን ዜና ያረጋግጣል። ለብሎጉ እድገት ኮሚቴው ትብብራችሁን እንደሚጠብቅም ተነግሯል። 
 http://www.meleket4u.blogspot.com/

 እውነትን የያዘ ማሸነፉ የግድ ነው
መልካም ሳምንት።

  

Wednesday, August 25, 2010

ትልቅ ሰው በምሳሌ ያስተምራል ቀላል ሰው በስድብ ያርቃል። ቁጥር ፵

መጽሐፍ ቅዱስ አገላበጥንና "የሚሳደቡ ብጹአን ናቸው መንገስተ ሰማያትን ይወርሳሉና "የሚል ጥቅስ ማግኘት ግን ተሳነን። የሚሳደብ ሰው የሃሳብ ድሃ የሆነ ብቻ ነው።  ባለጌ ባለጌ መሆኑን የምታውቀው በግብሩና በምላሱ ነው ይባል ነበርና። ግለሰብን በማዋረድ እናቶችን በመዝለፍ፤ በታመሙ በመቀለድ፤ በሙት ላይ በማፌዝ:የግለሰብን ስም እየጠቀሱ በማስፈራራት ትልቅነት አለ ከተባለ ትልቆቹ እነማን እንደሆኑ ደግሞ እያወቅን እየመጣን ያለን ይመስለናል። ዝም ያለ ሁሉ የፈራ የሚመስላቸው፤ የመናገር እንጂ የማዳመጥ ባህሉም ልማዱም እውቀቱም የሌላቸው ግለሰቦች ብቻ ናቸው። የሚጽፉትን በማየት ደረጃቸውን ለመለየት ደግሞበነሱ አባባል " የመንኮራኩር ፈላስፋ"መሆንን አይጠየቀምና።

ውድ አንባብያን

በፍርድ ቤት የተያዘው የይግባኝ ጉዳይ የመልስ መልስ ተሰጥቶት በቅርቡ ውሳኔውን  እየተጠበቀ መሆኑን የተቆርቌሪዎች ቡድን አባላት አብስረውናል። በስድብ የተካነውና ግለሰቦችን እያዋረደ፡ ያለው የቦርዱ ደጋፊ ነን ባዮች ድሕረ ገጽ ለከሳሾቹ ክስ መልካም መረጃን እያቀበለ ለመሆኑ በቅርቡ የምናየው ታላቅ የምስራች እንደሚኖር መረዋ ለአንባብያን መናገር ይወዳል። የማስፈራሪያና የስድብ ምንጭ የሆነው ይህ ድሕረ ገጽ የመናገር መብትን የጣሰ፤ የግለሰብን መብት የተጋፋ፤ ከመጋረጃ ኋላ  ተደብቆ ግለሰቦችን የሚያስፈራራና የብዙዎችን የመሥራት፤ የመንቀሳቀስ መብት የሚጋፋ ከመሆን አልፎ የሰው ሕይወት እንዲጠፋ  ቅስቀሳ  የሚያደርግ ለመሆኑ በተደጋጋሚ ያወጣቸው ጽሁፎችን ተንተርሶ ለፍርድ የሚቀርቡበት ሰዓት መቃረቡን ስንናገር፤ ለመብት የታገለ  ማንኛቸውም ግለሰብ ይህንንም የመታገል ግዴታ  እንዳለበት በማሳሰብ ጭምር ነው።

ማንም ግለሰብ ቤተሰቡንና ንብረቱን ብሎም እራሱን የመከላከል ሙሉ መብት እንዳለው ሁሉ፤ መንግሥትም የግለሰቦች ሕይወት አስጊ ደረጃ ላይ ሆኖ  ሲያገኘው የመከላለልና የዜጎችን መብታቸውን የመጠበቅ ሃላፊነት አለበት። በደል ሲደርስ ወደ ሕግ መሄድ አዋቂነት እንጂ የሚያሰድብ ብሎም ያልተደረገ ፈጥሮ  ስም የሚያስጠፋ  መሆን አይኖርበትም።  ማንም ከሕግ በላይ መሆን አይቻለውም። የግለሰብ መብት የሚከበረው የሌላውን መብት እስካልተጣሰ  ድረስ ብቻ ነው።  ስለሆነም በሚጻፈው የተደናገጣችሁ የቤተሰቦቻችሁና የራሳችሁ ሕይወት አስጊ ደረጃ ላይ ነው ብላችሁ የምታስቡ ሁሉ፡ ድርጊቱ ከመፈጸሙ በፊት ወደ ሕግ እየሄዳችሁ ለሕግ አስከባሪዎች ማሳወቁ ለተጀመረው እንቅስቃሴ እነደሚረዳ ልናሳስባችሁ እንወዳለን። የሕግ የበላይነት እንደሚያሸንፍ ደግሞ ምንም ጥርጥር የለንም።  

ይህንን በዚህ እናቁምና ባለፈው እሑድ የቤተክርስቲያኑን መኪና አሽከርክሮ ወደ ሂውስተን ሄዶ የነበረው የቦርዱ ተወካዮችና የእናቶች የዘማሪ ቡድን አባላት እንደተጠበቀው ከስደት ሲኖዶስ ከመጡት አራት ተወካዮች ጋር ተገናኝቶ መምጣቱንና 5 ልጆችም ከዚሁ ከስደቱ ሲኖዶስ የድቁና ማእረግ ተቀብለው መምጣታቸውን የደረሰን ዜና ያረጋግጣል። ድቁና ከተቀበሉት መሃል ሁለቱ የቦርድ አባላት ልጆች አንደኛው ለቦርዱ የመከላከያ ምስክር የነበሩት "ሕፃናትን ከፎቅ ሊወረውሩ ሲማከሩ ሰምቻለሁ" ብለው የመሰከሩት ግለሰብ ልጅ መሆናቸውን ሁኔታውን የተከታተሉት ምእመናን አውስተውናል። "የስደት ሲኖዶስን ለማምጣት የተጀመረው ትግል ፍሬ እያገኘልን ነው" የሚሉ የስደት ሲኖዶስ አላሚዎች የፖለቲካ  ድርጅቶችና ግለሰቦች ፈገግታ ቢያሳዩ እውነታ አላቸው። መረዋ  የተጻራሪዎች ትግላቸው ይህን እቅድ በሥራ ለመተግበር እንደሆነ የተናገረበት ሰዓት ውሎ ስላደረ ነግረናል ከማለት በስተቀር አልተገረምንም።

ባለፈው እሁድ በቤተክርስቲያኑ የሰበካ  ሰዓት ከባለቤቷ የተጣላች እናት ወደ ሃገር ቤት ለመላኪያ ገንዘብ አዋጡ ተብሎ ገንዘብ በመዋጣት ላይ እንዳለ ከመሃል ተነስተው "ቤተክርስቲያን አስታራቂ እንጂ አፋቺ የሆነችው መቼ ነው?" ብለው የጠየቁት እናት ጥያቄአቸው ትክክል እንደነበረ ብንገነዘብም ወዲያው የዘር ግንዳቸውን ዳሰው የተለመደ የስድብ ውርጅብኝ እንዳያወርዱባቸው ፈርተንላቸው ነበር። ነገር ግን ያካባቢው ሰፈርና የቤተክርስቲያኑ መብራት በመጥፋቱ በቶሎ ለመበተን ችለናል።መብራቱን ያጠፉት ደግሞ የከሳሽ ቡድኖች ናቸው ተብሎ መወንጀሉንም በብሎጋቸው ላይ ያነበባችሁት ጉዳይ ነው።  "የመቀበር መብታችንን የሚገፍ መንግስት ባገራችን ጣለብን" ያሉት የእለቱ አስተማሪ ካህን ከፖለቲካው ውስጥ ባይገቡ ኖሮ ትምህርታቸው መልካም ነበር። ነገር ግን የከበቧቸውን ፖለቲከኞች አስደስታለሁ ብለው ያልሆነ ስህተት ፈጸሙ ብሎ መናገር  ለወደፊቱ ትምህርት ይሆናቸዋል ብለን እናምናለን።

ውድ ወንድሞችና እህቶች

ክርስቲያን በእምነት ላይ የተመረኮዘ እንጂ በዘር የተገነባ ከሆነ መጥፎ ለመሆኑ መስካሪ አያስፈልግም።

በአንድ ወቅት ሁለት አፍሪካ አሜሪካውያንን ያየ የአራት አመት ልጅ ለእናቱ  "mommy look this N......"
ሲል እናትየዋ የተሰበሰበውን ሰው ተመልክታ   " I am sorry" ብላ መለሰች።
ይህንን የሰማ አንደኛው አፍሪካ አሜሪካዊ  "don't worry we will credit  it to the source" 
ያለውን ያጫወተን ቀልደኛው ጔደኛችን ነበር።
አይዞሽ አትጨነቂ ለህፃኑ ይህንን ማን እንደነገረው እናውቀዋለን ማለቱ ነው። በሌላ  አባባል የተማረው ካንቺ ነው ብሎ ለማለት ነው።

ልጆቹን  የሚበላ ለድሮ ድመት ወይም ውሻ ብቻ ነበር ዛሬ ግን ክርስቲያን ነን የሚሉ ሲያደርጉት ስናይ አዘንን። በውሸት ፍቅር ይመጣ ይመስል የስድብ ውርጅብኝ እያወረዱ መደምደሚያው ላይ "ወደ ክርስቶስ ቤት ተቀላቀሉ" የሚሉ ያስቁናል። እራሳቸውን እንዳታለሉ ሁሉ ፈጣሪንም ያታለሉ እንደሚመስላቸው ግብዝነታቸውን በማየታችን።

ሌላው ሳናነሳው የማናልፈው ባለፈው በምእመናን የተቌቌመውን የምእመናን እንባ አስጠባቂ ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር እንዲሁ በድሕረ ገጽ ላይ ወጥቶ ተመልክተናል። ለነገሩ ይህ ባደባባይ ሕዝብ ተሰብስቦ የተቌቌመ  ኮሚቴ እንጂ የሕቡእ ኮሚቴ ባለመሆኑ የስም ዝርዝሩም እንዲሁ ያደባባይ ሚስጥር ነው። ኮሚቴዎቹ በሥራ  እየተፈተኑ ለመሄድ የተዋቀሩ መሆናቸውን እንደ እንጉዳይ የሚጠፉ ሳይሆን እንደድር የተሳሰሩ መንፈሰ ጠንካሮች መሆናቸውን ከተመለከነው መናገር እንወዳለን። "ለደህና እቃ ማስታወቂያ  አያስፈልገውም" እንዲሉ በሥራችን እንጂ በስማችን መኩራራት አይኖርብንም ብለው ያለፉትን እናንተ መተዋወቅ አለባችሁ ካላችኋቸው ለጥረታችሁ እናመሰግናለን ብለው ያመሰብኑ ካልሆነ በስተቀር "ውይ ሥማችን ወጣ ብለው እንደማያፍሩ: አንጠራጠርም። በሚሰሩትየስራ ውጤት ደግሞ  እንደምታፍሩ ቃል  ብንገባ ካየነው በመነሳት ነውና ውሸት አይሆንም።
በሚቀጥለው እትምታችን በትልቅ ዜና እንደምንገናኝ በቅድሚያ ቃል እየገባን ለዛሬው በዚሁ እንሰናበታለን።

በነገራችን ላይ ለማንኛውም በ E MAIL ልትገናኙን ለምትፈልጉ ሁሉ አድራሻችን

yetayalewnetu@gmail.com   ነው


የከርሞ  ሰው ይበለን

ቸር ወሬ ያሰማን።

Monday, August 9, 2010

ከምእመናን የደረሰን ዜና ቁጥር ፴፱

ላለፉት ወራቶች በቤተክርስቲያናችን የተፈጠረው ችግር አሳስቦአቸው መፍትሄ  ማግኘት አለብን ብለው የተነሱት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አባላት በቤተክርስቲያኑ አዳራሽ ለመሰብሰብ መከልከላቸው ሳያናድዳቸው የሆቴል አዳራሽ ተከራይተው "የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመፍትሄ ኮሚቴ"  ማቌቋማቸው የሚታወስ ነው። ይህ በጅምሩ የ200 አባላትን የሥም ዝርዝር ይዞ የተዋቀረው ኮሚቴ የደጋፊዎቹ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሄዱን በመግለጽ በሃላፊነት የተቀበለውን ሥራ ለማቀላጠፍ ይረዳ ዘንድ በትላንትናው ስብሰባው የተለያየ ኮሜቴ ማዋቀር አስፈላጊ ሆኖ  ስላገኘው  9 ኙ የኮሚቴ አባላት በተዋረድ የሚሳተፉበት 4 ኮሚቴዎች ማቌቌማቸውን ከስፍራው የተገኙ ምእመናን ገልጸውልናል።

በእለቱ በተደረገው የኮሚቴ ማዋቀር ስብሰባ ላይ እንደተነገረው አባላት ምነው ዘገያችሁ? ማለታቸው የተገባ  ጥያቄ  መሆኑን የዘገቡት የኮሚቴው ሰብሳቢ "ጥልን ለማፋፋም እንጂ ሰላምን ለመፍጠር  ጊዜ  እንደሚፈጅ መታወቅ እንዳለበት ጠቅሰው በተለያየ መልኩ ግን ብዙ በይፋ ያልወጡ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንና በተለይም ባለፈው ወር በግለሰብ ተጠርቶ በነበረ ውይይት ላይ በመገኘት ከተላያዩ ጉዳዩ ይመለከተናል ከሚሉ የቤተክርስቲያን  አባላት ጋር ውይይት ኮሚቴው ማድረጉን " ለተሰብሳቢዎቹ ገለጻ አድርገዋል"። ይህ ዛሬ የተቋቋመው ኮሚቴ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አለመሆኑን የተናገሩት ሰብሳቢ በኮሚቴው ውስጥ ገብቼ  ለማገልገል እፈልጋለሁ ለሚል ለማንም ኢትዮጵያዊ በሩ ክፍት መሆኑን ጠቅሰው፡ አሁንም መፍትሄ የምናመጣው ተሰብሰቦ በመነጋገርና በመወያየት  መሆን አለበት ብሎ ስብስቡ  እንደሚያምንና በዚህም መርህ እንደሚመራ ጠቅሰዋል። በአሁኑ ወቅት የሰላም መንገዱ የተዘጋ በመሆኑ ደግሞ የሕግን የበላይነት በሕግ ማስከበረ አማራጭ የሌለው መንገድ ሆኖ መገኘቱን ለተሰብሳቢው አስረድተዋል።

በእለቱ የተሰበሰቡት የኮሚቴ ተመራጮች ስራቸውን ለማከናወን እንዲራዳቸው በጸሎት የከፈቱት የመንፈሳዊ አባቶች የራሳቸው ችግር ሳይሆን የምእመናን መበታተን እያስፈራቸው እንደሆነ  ጠቅሰው ክርስቲያን ሽንፈትን የሚቀበል ሳይሆን ጥንካሬን የሚያስተምር መሆን አለበት ብለው ለተሰብሳቢዎቹ ተናግረዋል። በነሱ ላይ ያለው የፈቃድና የኢኮኖሚ ችግር የሚቀረፍበትን መንገድ ተሰብሳቢዎቹ እንዲያስቡበትም ለተሰብሳቢዎቹ ማሳሰቢያ አቅርበዋል። ከሁሉም በላይ ግን የክርስቲያኖቹ መበታተን አሁንም እያሳሰባቸው በመሆኑ ከቤተክርስቲያን በኩርፊያ መቅረት እንደማይገባ አስተምረው  ከጸለይን ከተማጸንን የማይሆን  ነገር እንደማይኖር መቀበል ደግሞ ክርስቲያናዊ እምነታችን ነው ብለዋል።
  
በእለቱ

፩   የሕግ ክፍል 
፪   የአባላት ጉዳይ ክፍል
፫   የሕዝብ ግንኙነት ክፍል
፬   የመንፈሳዊ ክፍል

ኮሚቴዎች መዋቀራቸውንና የሥራ መመሪያ መንደርደሪያ ለያንዳንዱ ኮሚቴ መሰጠቱን ዘጋቢዎቻችን ጠቅሰውልናል።   በቅርቡም ኮሚቴው የራሱ የሆኑ መጽሔት እንደሚያዘጋጅ የሕዝብ ግንኙነቱ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተናገሩ ሲሆን በስድብ ሳይሆን እውነትን በመዘገብ ደጋፊን ማበርከት እንደሚቻል በግብር እየታየ መሆኑን ጭምር ተናግረዋል። የእለቱ ስብሰባ በጸሎት ተጀምሮ  በጸሎት መገባደዱን ምእመናኑ ጨምረው እንዳወሱን ልንነግራችሁ እንወዳለን።

መረዋ በዚህ አጋጣሚ ይህንን ስብስብ እዚህ እንዲደርስ ለማድረግ ለጣሩ ሁሉ በተገፉትና  በተሰደቡት ምእመና ሥም ምስጋና  እያቀረበ። መሳደብን እንደበትር፤ አሉባልታን እንደ እምነት፤ ትልቅ ሰውን ማዋረድን እንደ ጀግንነት፤ የሚወስዱትን ልቦ ናቸውን ያራራው ዓይናቸውን ይክፈትላቸው እያለ፡ ትዳር ለማፍረስ፤ ግለሰብ ለማዋረድ ፤ የተነሱትን ከመናቅ በስተቀር፡ የነሱን መንገድ መከተል ግን የድክመትም ድክመት እንደሚሆን ያምናል።  አዛውንቶችን በመሳደባቸው  አሸነፍን የሚሉ የፖለቲካ  ድርጅቶች ካሉ እየከሰሩ መሄዳቸውን እንጂ ማሸነፋቸውን እንደማያሳይ ማረጋገጥም ይወዳል ። ሳይሰደቡ ትዳራቸው የፈረሰው የተሳዳቢዎቹ እንጂ የተሰዳቢዎቹ አለመሆኑንም መጥቀስ አስፈላጊ ይመስለናል። ለልጆቻችን ምን እያስተማርን ነው?  ብለን መጠየቅ ያለብን ደግሞ  ሁላችንም ነን። እከሌ  ዘሩ እንደዚህ ነው ብሎ በዘር ግለሰብን መፈረጅ ደግሞ አዋቂነት ከመሰላቸው መቀጠል ይችላሉ። እስከዛሬ የተሰደቡትን ግለሰቦች በማየት ሰዳቢዎቹ እነማን እንደሆኑ ለመገመት በመቻሉ የከተማው ነዋሪ ጥሩ ግንዛቤ  እንያገኘ መሆኑንም መናገር የተገባ ይመስለናል። ይህ ስድብ ደግሞ  ኢትዮጵያዊ ባህላችን አለመሆኑን የሚቀበል ማናቸውም የክርስቲያን አባል ይህንን የተቌቌመውን ኮሚቴ እንዲቀላቀል መረዋ ጥሪውን ያቀርባል።

ከቁልቌል ዛፍ እንጆሪ ይበቅላል፤ ከዶሮ ጅማት ማሲንቆ ይሰራል፤ ማለት ደናክል በረሃ ጤፍ ለማምረት እንደመጣር ያክል ነውና፡ ተሳዳቢዎቹም ይቀየራሉ ብሎ ማለም እንዲሁ ውሃ እየናጡ ቅቤ እንደ መጠበቅ ነው እንላለን።

ለኮሚቴው መልካሙን እየተመኘን የኮሚቴው ልሳን የሆነው መጽሔት ሥራውን ሲጀምር መረዋ የአባላትን የበላይነት በመቀበል የብሎግ እትምቱን እንደሚያበቃ ለአንባብያን በቅድሚያ  ልናሳውቅ እንወዳለን።

እስከዚያው በሰላም ያድርሰን።