Thursday, July 4, 2013

ቀጥተኛ መስመር አቋራጭ የማይሆንበት ወቅት አለ

ለዚህ ያደረሰን አምላክ ክብር ይግባው እንደምንል ሁሉ መጭውንም ያሳምርልን ብሎ መለመን ደግሞ የተገባ  ነው። እንደኛ ሐጥያት ቢሆን ኖሮ ብዙ ቅጣት፣ ብዙ ግርፋት፣ ይገባን ነበር።  አምላክ ግን የምሕረትና የፍቅር አምላክ በመሆኑ ለሐጥያታችን ይቅርታን ብቻ  ሳይሆን ሕይወቱንም ከፍሎልናልና እነሆኝ አሁንም በምህረቱ እየዳሰሰን ነው። ለዚህም አምላክ ምስጋና ይድረሰው።

የቤተክርስቲያኑን ክስ አስመልክቶ ሰሞኑን የሰማንው ዜና አለ። ታዲያ “የዋሸን እለት ሞትን ማለት ነው፡ እውነቱን ነግረናችሁ እበረንዳ ማደሩን እንመርጣለን” ብለናችሁ ነበርና ዛሬም ቃላችንን አናጥፍም። ከናንተ የተደበቀ ምንም ነገር የለንም እስካሁን የሰነበትነው የናንተን አመኔታ በማካበታችን ለመሆኑ ሌላ ምስክር መጥርት አያስፈልግም። በመሆኑም በርእሱ እንደገለጽነው The shortest distance between two points is a  straight  line የሚለው የሂሳብ ሕግ አንዳንዴ  እንደማይሰራ መቀበል የግድ ይሏል። ስለሆነም ባለፈው ነግረናችሁ የነበረው የቤተክርስቲያን ክስ ክሱን መስርተውት የነበሩት ጠበቃ በነደፉት መልኩ መቀጠል ይሻላል አይሻልም በሚል ሰፊ ውይይት ተካሂዶ ሁኔታውን እንደገና በመዳሰስ ክሱን የተረከቡት ጠበቆች (THE LAW FIRM)  ባቀረቡት ምክር ብሎም የሽምግልና ሂደትን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ብዙሃኑን ለማሳተፍ በሚልና ሌሎች አማራጮችንም በመዳሰስ የተጀመረ ሂደት ክስ እንዲሰረዝ ለዳኛው ማመልከቻ መግባቱን መስማታችንን ልንነግራችሁ እንወዳለን። ይህንን በአባላት ላይ የደረሰውን የቤተክርስቲያን አባላት ችግር ለመፍታት በዋናነት የመልአኩ ፈቃድ እንዲታከልበት ጸሎታችሁ አይለይ እያልን፣ ስለሁኔታው በሰፊው ዝርዝሩ እንደደረሰን እንደምናሳውቃችሁ ቃል እንገባለን።

በተሳፋሪነት የሚበሩ ሁሉ አብራሪው እኛ ነን ብለው ቢናገሩ ውሸት እንደሚሆን ሁሉ ጫፍ ይዘን ማሳረጊያ ልናወጋችሁ አንፈልግምና እስከዚያው ጆሯችሁን ሰጥታችሁ ጠብቁን።

የሳምንት ሰው ይበለን። 

Saturday, June 1, 2013

በትንሳኤ የሚያምን ሰው በሞት አይደናገጥም

ውድ ምእመናን


እንደኛ ክፋት፣ እንደኛ ተንኮል ቢሆን እስካሁን መሰንበት አልነበረብንም። ምህረት መደሰቻው የሆነ ፈጣሪ አምላክ ሁሉን ቻይ ነውና ከሐጥያታችን እንድንድን ተሰቃይቶ ሞትን እንደሞተልን ሁሉ ዛሬም በምህረቱ እየዳሰሰን ነው። እራስን ማታለል ይቻል ይሆናል ፈጣሪን ለመሸንገል መሞከር ግን ግብዝነት ነው። በሚያምኑ ላይ ማላገጥ ቀላል ነው ብሎ ማመን ይቻል ይሆናል። በእምነት ጸንቶ መቆየት ግን ብርታትን የእግዚአብሔርን እርዳታ ይጠይቃል። በዳላስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በመብት ጥያቄ አኳያ በተነሱ አለመግባባቶች፣ አባላትን በማባረር ሰላም አይፈጠርም ብለን ስንናገር ሰንብተናል። የተወለዱ ጨቅላ ሕጻናትን በመግደል የክርስቶስን ማደግ መግታት እንደማይቻል ሄሮዶቱስ ቢያውቅ ኖሮ ያንን ሁሉ በደል ባልፈጸመ  ነበር። ለእምነት የተሰበሰበ ክርስቲያን በእምነት አይጣላም ከሚል አመለካከት በመነሳት ሁሉን አደላዳይ አምላክ የተለያየነውን እንዲሰበስበን፣ የተቀያየምነውን እንዲያስታርቀን፣ ያራራቀንን እንዲያቀራርበን በማሰብ፣ ለሰደቧችሁ ይቅርታን፣ ላዋረዷችሁ ምሕረትን፣ ላባረሯችሁ እርሕራሔን እንዲሰጣቸው ፀልዩ ብለን መናገራችንን አሁንም አንዘነጋም። ይህንን ስንል ከፍርሃት በመነሳት አልነበረም።  በእምነታችሁ ተደራደሩ፣ ተረገጡ፣ መብታችሁን ተገፈፉ፣ ንብረታችሁን ተነጠቁ፣ ማለታችንም እንዳልነመረ ሁላችሁም የምታውቁት ይመስለናልና መደጋገም አንፈልግም። ቀደም ሲል ተነስተው የነበሩትን የመብት እረገጣን፣ የአባላትን ማባረርና የቦርድ አባላት የሆኑት መሪዎች የግለሰብን የአባልነት ማመልከቻ በፖለቲካ መነጽር እያዩ ደጋፊዎቻቸውን ሕጉን እየለጠጡ፣ ተቃዋሚዎቻችን ናቸው የሚሏቸውን ሕጉን እያጎበጡ ሲያስገቡና ሲያባርሩ ተመስርቶ የነበረውን ክስ ከጅምሩ ደግፈን በጽናት መቆየታችን ያደባባይ ሚስጥር ነው። ይህንን ስናደርግ እንዳወሩት ገንዘብ ተልኮልን፣ ድርጎ ተወስኖልን ሳይሆን ለራሱ መብት ያልቆመ ግለሰብ ለሌላው መብት መቆም አይችልም ከሚል መርህ በመነሳት ነበር። ባደረግነው አሁንም እንኮራለን። እንዳልነው ቤተክርስቲያኑ ያባላት ድሃ እስኪሆን ድረስ መንምኖ የተሰበሰበው ገንዘብ ሲቀንስ እንጂ ሲጨምር አለመታየቱ ለተናገርነው ማረጋገጫ መረጃ  ነው።

ባለፈው በመብት እረገጣ ክስ ላይ ተሰልፈው የነበሩ ግለሰቦች በአዲስ ዓመት አዲስ መንፈስ ብለው ላስቀየሟቸውና ለተቀየሙ ይቅርታን ባደባባይ ሲያሰሙ ሰምተን ብስለታቸውን አድንቀናል ከጥንካሪያቸው ተምረናል። በተደጋጋሚ እንዳልነው በዝሙት ዓለም እየታዩ ሌሎችን ዝሙተኛ፣ በየመጠጡ ቤት ሰክረው እየተወላገዱ ሌሎችን የአልኮል ሱሰኛ፣ በእጅ አመል እየተዳደሩ ሌላውን ዘራፊ ወንጀለኛ ለሚሉ አጸፋዊ መልስ መስጠት አቅቶ እንዳልነበረ ደግሞ መናገር እነሱ እንደሚሉት "መሃይምነት" እንዳልሆነ ዛሬም ቢነገራቸው አይከፋም። ለሚሳደብ መሳደብ ቀላል ነው መሳደብ ግን አለመብሰል ነው ብለን እናምናለን።

ውድ የቤተክርስቲያን ምእመናን አንድን ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ቤት ከማባረር  የከፋ ነገር ያለ አይመስለንም። ይህ ደግሞ በምድር መቅሰፍትን በሰማይ አባታዊ ግሳጼንና  ፍርድን እንደሚያስከተል ዛሬም መናገር እንወዳለን። ሌላው ሲባረር የሚደሰቱ ካሉ ጸሎት ያስፈልጋቸዋል። የተረከቡ የመሰላቸው ተሳስተዋል። "በእንግድነት የሚያድሩበት ቤት ማረፊያ  እንጂ መኖሪያ  አይሆንምና"

ታዲያ ትላንት የተጀመረው የአባላት ትግል ዛሬም ቀጥሎ በያዝነው ሳምንት በተለየ መንገድ አዲስ ክስ መመስረቱን ሰምተናል። የተጀመረው ክስ እንዳየነው የአስተዳደር ቦርድ አባላት "ቤተክርስቲያናችንን ከገለልተኛ አመለካከታችን አውጥተው፣ ከሃገራችን ሲኖዶስ ነጥለው፣ የፖለቲካ መስመር ለማራመድ ወደ ስደተኛ ሲኖዶስ ንብረታችንን አሳልፈው በመስጠታቸው የተናደዱ ግለሰቦች "ዛሬስ ያበጠው ይፈንዳ ሳንሞት አትቀብሩንም፣ ሳንታወር አትመሩንም፣ ያዋጣንውን ድርሻችንን እንካፈላን ብለው እንደሆነም ለማወቅ ችለናል። ትላንት የንብረት ጥያቄ  ይነሳ  ሲባል የቀድሞ ከሳሾችም ሆኑ መረዋዎች ተቃውመውት ነበር። ለምን ቢሉ የንብረት ክሱ መበታተንን ያመጣል ከሚልና  ችግራችንን በውይይት መፍታት ከተቻለ መሰነጣጠቁን ማቆም ይገባል ከሚል እምነት ነበር። ይህ በእውነትም አድማጭና ሰሚ ቢያገኝ ኖር መልካም አመለካከት ነበር። ሊሆን ግን አልቻለም። ለምን ቢሉ እየታረቁ የሚክዱ እየተወያዩ  የሚያሴሩ የቦርድ አባላት አሻፈረን በማለታቸው ነበር። አሁን ግን መረዋ ከሳሾች የጀመሩት የንብረት ክፍያ ጥያቄ ወቅታዊና አማራጭ የሌለው ነው ብሎ በመቀበል መጨረሻውን ያሳምረው ማለት ይወዳል። 

የአሁኑ ከሳሾች ለምነን ሰሚ አጣን፣ ተናግረን ተዘጋን፣ በእምነታችን ተቀጣን፣ በመውደዳችን ተገፋን፣ለዚህ ቤተክርስቲያን ደግሞ ላደረግነው አስተዋጽኦ መስካሪያችን አንድ አምላክ፣ ብሎም በመቀመጫውና  በግድግዳው ላይ ያለው አሻራችን በእጃችን የሚገኘው የቤተክርስቲያን ደረሰኝ መረጃችን ነው ይላሉ። ውሸትን መድገም ያሽቸግራልና ዛሬ ያስተዳደር ቦርድ መሪዎች ነን ባዮች የሚሉትን ለመስማት እንወዳለን። ምስክር ሆነው በመሃላ ሲመሰክሩ ማየትን እንናፍቃለን። አሁን ደግሞ  ምን ብለው እንደሚያወሩም መስማት እንጓጓለን። 

መረዋ በመደጋገም እንደ ጻፈው አሁንም ሰላም ማምጣት ካስፈለገ  ምርጫው አንድ ነው ብሎ ያምናል። ምላሹ የምእመናንን መብት ማክበር ብቻ  መሆን ይኖርበታል። የንብረት መካፈል ክስ የመሰረቱት ግለሰቦች ገንዘብ ወስደው ለመክበር አስበው እንዳልሆነ እናውቅላቸዋለን።  ትርፍ አትራፊ ካልሆነ ድርጅት የሚገኝ ገንዘብ በሕግ ትርፍ አትራፊ ላልሆነ ተግባር የሚውል ብቻ እንደሚሆን እናውቃለንና። ለስም እንዳልተነሱ እናውቃለን በፊትም ስማቸው ታዋቂ ነውና። በፖለቲካ እንዳልሆነ እናውቃለን አቋማቸውን ደብቀው አያውቁምና። ለመብት መሆኑን ግን አልደበቁም ትላንትም ካገር ያስወጣቸው እምነት ነውና።

መረዋ በሃይማኖት ጥያቄ መግባት አይይፈልግም ብሎ በተደጋጋሚ ለአንባብያን ቢናገርም የስደት ሲኖዶስ መኖሩን ግን አይቀበልም። የኢትዮጵያ ሲኖዶስ መንበሩ ቅድስት ማርያም እንጂ ሰሜን አሜሪካ አይደለም ብሎ ያምናልና። ከሃገራችን ተሰዶ  የነበረ ቢኖር የመድሃኒ ዓለም ጽላት በጣልያን ወረራ ከንጉሰ ነገሥቱ ጋር ወደ  ሎንዶን  እንደ ነበረ እናስታውሳለን። እሱም ንጉሱ ሲመለሱ ተመልሶ አገር ቤት ገብቷል። የኃይማኖት መሪዎችና እምነቱ ግን ከሃገራችን ተሰዶ  አያውቅም።

ስልጣን አለን ለሚሉ የተሰበሰበው ገንዘብ እስኪያልቅ እንፋለማለን ብለው ለሚፎክሩ የፖለቲካ ሰዎች መረዋ የሚለው ነገር ቢኖር "ደጀሰላም ያደገ፣ ምግብ ቤት ሁሉ ደጀሰላም ይመሰለዋል" እንዲሉ የተሰበሰበ  ስብስብ ሁሉ የፖለቲካ ደጋፊ አለመሆኑን እንዲረዱት ነው።

 ዛሬ የተጀመረው ክስ እንደ ትላንቱ ሳይሆን መፋታት ካለብን ድርሻችንን መካፈል መብታች ነው የሚል ስለሆነ መፍትሔው በሰላም መካፈል ብቻ  ይሆናል። አብረን መኖር አንችልም ብሎ ገንዘብንም ንብረትንም ነጥቆ መቅረት አለመቻሉን ደግሞ በፍርድ ቤት የቀረበ  ጉዳይ ነውና  መጨረሻውን በፍርድ ቤት የምናየው ይሆናል።

መሪ መሆን ጥሩ ነው ያሉበትን አለመገንዘብ ደግሞ "ግቻ ያሰረ እረኛ ዘውድ የጫነ  ይመስለዋል"  የሚለውን የድሮ  አባባል ያስታውሰናል። መረዋ በፊት እንዳለው አሁንም ማለት የሚወደው መፋታቱ ካልቀረ አሁንም ፍችው በበሰለ መንፈስ መመራት እንዳለበት ነው። ካልሆነ " የበሰለ ዳቦ መብሰሉ የሚታወቀው መሃከሉን በመንካት ነውና" ሊጥና  ብስሉን ለማየት እድሜ  ይስጠን።

በሰላም ዋሉ

Wednesday, March 27, 2013

ማገርና ወራጅ የሌለው ቤት ጣራው መደርመሱ የግድ ነው።

እስከዛሬ የምናውቀው ለተሰደደ የሚጸልይ መንፈሳዊ አባት እንጂ የሚሰደድ አባት አልነበረምና ለተሰደዱት ጸልዩላቸው። የፈጣሪን ዘላለማዊ ግዛት ለማየት የሚጓጓ እንጂ ዙፋነ ሲመትን ካልያዝኩ ሃይማኖቱ ይፍረስ የሚል አባት ካያችሁ ይቅር በላቸው ብላችሁ ለምኑላቸው። "የመምጫዬ ቀን አይታወቅም ብሏልና  ንስሃ ግቡ" ብለው በሚያስተምሩበት ልሳናቸው፣ ካልገዛን ይዝጋን፣ የሚሉ ስታዩ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱላቸው። እኛ ፭ ኪሎ  እስክንደርስ ቤተክርስቲያኑ ይፍረስ፡ የሚሉ ከሰማችሁ ተዝካር በቁም አውጡላቸው።

ውድ የመረዋ እድምተኞች፣ የመብት መጣስን ተቃውማችሁ በሰለጠነው ዓለም ተቀምጠን መረገጥን፣ በሰላማዊ አገር እየኖርን መታፈንን፣ ገዴታ  እንጂ መብት የሌለበትን አባልነት ላለመቀበል አሻፈረን ብላችሁ እስካሁን የታገላችሁትን ሁሉ ዛሬ መረዋ እንኳን ደስ ያላችሁ ሊል ይወዳል። የዛሬ ፭ ዓመት ይህ ይሆናል ስትሉ፣ ስንል የሚሰማው ጥቂት ነበርና። ተጀምሮ  እስኪያልቅ ግን ያላችሁት፣ የተናገርነው፡ መሬት ላይ ጠብ አላለም። ዛሬ ይዋሹ የነበሩት የተጋለጡበት፡ ለመብት የቆሙት ደግሞ በኩራት የሚንቀሳቀሱበት ወቅት ሆኗል። ባለፈው ቅዳሜ የሚካኤል  ቤተክርስቲያ አባላት የስደት ሲኖዶስን መረጡ ሲባል ሰምተው የተናደዱ ቢኖሩ ትላንት ስንናገር አይሆንም፣ አይደረግም፣ ይሉ የነበሩ ግለሰቦች ብቻ ናቸው። ይህ ከሆነ "ቤቴን ወለድ አግድ አሲዤም ቢሆን ወደ  ሕግ እሄዳለሁ" ያሉት ግለሰብ ደላላ ሲያጠያይቁም አላየንም። ይልቅስ ያስተዋልንውን ሌላ ቁም ነገር እናጫውታችሁ። እነዳዊት አለማየሁን አናስገባም እያሉ ያኮረፉ ጓዶቻቸውን የስድስት ወር የአባልነት ጊዜ  እያራዘሙ ሲመልሱ ማየታችን ነው። ነገሩ የፖለቲካ ነው ካሉም ወሳኞቹ ባለስልጣናት እነዳዊትም እነሱ የማይደርሱበት የትግል ገድል እንደ ነበራቸው መናገር የግድ ይሏል። ሃይማኖተኛ የሆኑትን እየመረጥን ነው ካሉም መስፈርቱ ሌላ ካልሆነ ዳዊትን በዚህ የሚፈትኑት አልመሰለንም። ልንል የፈለግነው እምነትና ውሸት እየተጠላለፈ  መጣ ለማለት ነው። ሌሎች ስሞች መደርደር ቀላል ነው። የዛሬ ፬ ዓመት  የመሃበረ ቅዱሳን አባል ነህ ብለው የወነጀሉት ግለሰብ ምን ማለታቸው እንደሆነ ተጨንቆ እኔ ነኝ ቅዱሱ? ኧረ ባባቶች መሳለቅ ነው ማለቱን ሰምተን ነበር። በወቅቱ ውሸት መጥፎ  ነው በተለይ ውሸቱ ከቤተክርስቲያን ሲሆን እጅጉን ይዘገንናል ብለን መጻፋችንም ትዝ ይለናል።


እስቲ ዛሬ ልብ በሉ  ከ 4 ዓመት በፊት ስለባለስልጣኖቹ እቅድ ስንናገር ትንቢት ተናጋሪዎች ሆነን ሳይሆን አካሄዶችን በመመልከት የደረስንበት የግምጋሜ ውጤት ነበር። ያልነው ባይደርስ ለቤተክርስቲያን መልካም ነበር የፈራነው ግን ሆነ። እነሆኝ የስደት ሲኖዶስ ቤተክርስቲያኑን ለመረከብ ቻለ። እንዴው ለምስክርነት December 18 2009 መረዋ ቁጥር ፭ የጻፈውን ቀንጨብ አድርገን በድጋሜ ዛሬ እናስነብባችሁ። እንዲህ ይል ነበር...........

በግል እንደታዘብነውና ሂደቱን እንደተከታተልነው። ሕጉን ለምን በክስ መሃል ለመቀየር አስፈለገ ለሚለው? የራሳችን መልስ የሚከተለው ይሆናል።
1 የማይፈልጉትን አባላት ለማባረር።
2 አዲስ የሚገቡ አባላትን ለማጣራት ለማበጠር።
3 አባላት ተቀበሉትም አልተቀበሉት የራሳቸውን ውሳኔ በመሰላቸውና ከቦርዱ ጥቅም በመነሳት ለመወሰን።
4 የእምነትን ጉዳይ አስመልክቶ ቄሱ ምን መሰበክ እንዳለበትና እንደሌለበት ለመንገር።
5 አባላት ለመመዝገብ ሲመጡ እንደ አፓርትመንት የማመልከቻ ማስከፈል። አባልነታቸውን ተቀባይነት አገኘም አላገኘ የከፈሉት እንዳይመለስ ማድረግ።
6 ገለልተኛነትን በመስበክ የሲኖዶስን ቦታ መተካት። ነው ብሎ ለማለት ብዙ ጊዜ አልፈጀብንም።

አሁንም ያላችሁት አልተፈጸመም የሚሉ ካሉ የምንጨምረው ይኖረናል። ዛሬ አንጋፋ  የቤተክርስቲያን አባቶች ተባረዋል ከ 1150 አባላት በላይ የነበረው ቤተክርስቲያን ዛሬ 279 አባላት ብቻ እንዳለው የሚሰማ  ሰው ቤተክርስቲያኑ አይወድቁ አወዳደቅ እየወደቀ  እንዳለ  የሚስማማ  ይመስለናል። ቀሳውስት እውነትን ስለሰበኩ ሲባረሩ ስናይ እግዚኦ ብለን ነበር። አባቶች ካገር እንዲባረሩ ለኢምግሬሽን ደብዳቤ  ሲጻፍ ስናይ ኧረ  በክርስቶስ ብለን ነበር። ደብዳቤውን የሚጽፉት ደግሞ  የቤተክርስቲያን ባለስልጣናት ብሎም እራሳቸው በስደተኝነት መኖሪያ  ፈቃድ ያገኙ መሆናቸውን ስናስብ የበለጠ አዝነን ነበር፡፡ አባላት ለአባልነትም ከባላቸው ከሚስቶቻቸው እንዲለዩና እንዲመዘገቡ ሲደረግ እግዚኦ ብለናል። የከፈሉበት ሳይሆኑ የተሾሙበት ፈላጭ ቆራጭ ሲሆኑም አስተውለናል። ይህ የትላንት ሂደት ነበር። ዛሬ ጨዋታው መቀየሩን አይታችኋል።
የእምነቱን መንገድ ወደ  ፖለቲካ  የወሰዱት የመንግስት ተቃዋሚ ነን ባዮች ትልቅ ስህተት እየሰሩ ነው።
የቆሰለ  ዝንጀሮ ወደ መንጋው ሲጠጋ የሚድን ይመስለዋል ሲቀርብ ግን ቁስሉን ሁሉም እየላሱበት ይብስና  ይሞታል እንዲሉ ፣ የባሌ  መንገድ በጋርላንድ በኩል  የሚመሰላቸው ፖለቲከኞች  ካሉ ጊዜ  ይስጠን እንጂ  መንገድ መሪ አጥተው በጎዳና ሲንገላጀጁ ለማየት ጊዜ  እንደማይወስጅብን እርግጠኛ ሆነን እንናገራለን። ትላንት እንዳልነው ጆሮ ቆራጭ መጣብህ እየተባለ ያደገ  ሕፃን አድጎ ቀልዳችሁን ተው እንደሚል ሁሉ አሁንም ቤተክርስቲያንህን ኢሕአደግ ሊወስድብህ ነው ያሉት ምእመን የወሰደበት ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ነኝ ባዩ እንጂ ኢህአደግ አለመሆኑን እያየው ነው። በሬ ያረደ ሰው በጎረቤት ሙዳ ስጋ  ሲጣላ  አላየንምና። ዱላ  ያለው ጠመንጃ ይመኛል ሲባል እንጂ ጠመንጃ  ያለው ዱላ  ይመኛል ሲባልም አልሰማንም ለማለት ነው።

ዛሬ ምእረፉ ተዘጋ  ለሚሉ የምስራች ወሬ አለን። ባለፉት ዓመታት የንብረት ጥያቄ  ክስ ይደረግ ሲባል ስንቃወም መቆየታችን እውነት ነው። ይህ ደግሞ መለያየትን እንዳያመጣ በመፍራት ነበር። የከሳሾችም ሆነ  የኛ  ፍላጎት መብትና እምነትን ከመለየቱ ላይ ነበርና። ዛሬ  ግን የእምነት ውሳኔ  መወሰን ተችሎ  ይሆናል፣ ንብረትን መንጠቅ ግን አይቻልም። አባላትን ማባረር ካህንን ማስጠንቀቂያ  መስጠት ከስራ  ማገድ ችለው ይሆናል በሌላው ገንዘብ መወሰን ግን አይቻልም። በእምነት አንግባ ያለው ዳኛም ከንብረት ጥያቄ  ሊሸሽ አይችልም። ከዳኛው ለመጥቀስ "በመጨረሻ ተከፋፍላችሁ እንደምትበተኑ ይታነኛል" ሲል የቤተክርስቲያኑ ጠበቃ  እሱን እኔም እላለሁ ብሎ  ነበር። ያ ቀን እንዲመጣ የጣሩት ባለስልጣናት ምኞታቸው ሊፈጸም መቃረቡን ታዲያ  ቀስ ብለን ሹክ እንበላቸው።
ክርስቶስ የቄሳርን ለቄሳር አለ እንጂ የቄሳርን ለመቅደስ አላለም። የተገፉትና  የተወረወሩት ምእመናን ወደ  ባህር ተወርውሮ ካሳነባሪ አፍ ገብቶ  እንደወጣው.................... ተመልሰው ነፍስ እንደሚዘሩ እርግጠኞች ነን።
የኛ ትግል ለምእመን መብት ነበር እንጂ ለግንብና  ለገንዘብ አልነበረም። አታመልኩም ካሉ: አትናገሩም ካሉ በጉልበት እንነጥቃለን ካሉ፣ እነሱ ያልከፈሉበት ገንዘብ ይዘው ቢከራከሩም ሕዝብ የለፋበትን፣ እናባርራለን ያሏቸውን፣ ያባረሯቸውን አባላት ድርሻ  የመስጠት ግን ግድ ይላል። እዚህ መድረሱ ያሳዝነናል። ይህ ደግሞ  በኛ ፍላጎት የተደረገ  እንዳልሆነ  ይታወቅ። ትንቢት መናገር ባትሉን ይህ እንደሚሆን ግን መተንበይ እንወዳለን። "ሲመሽ ስገዱልኝ ያለ  ሽፍታ ወጋጋን ሲቀድ  ይደበቃል።"

የሚካኤል ፈቃድ ይታከልበት

መልካሙን ለሁላችን።
  























































Saturday, March 9, 2013

ጉቦ የተቀበለ ዳኛ የሚፈርደውን መረጃውን ሳያገናዝብ አስቀድሞ ያውቀዋል።

"ዝምታ  ወርቅ ነው" "ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባበትም" ሲባል እንሰማና "ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል" "በሽታውን ያልተናገረ መድኃኒት አይገኝለትም" የሚለውን አባባል ስናዳምጥ ደግሞ ግራ እንጋባ ነበር። አሁን ግን ተረት አይደለም ምንም ነገር አያታልለንም። በመቆየት አረጀንና ከእድሜ ጋር ትእግስትም መጣ ቢባል እውነት መሆኑ እኮ ነው። አይገርምም? አገር ቤት ቢሆን ኖሮ አባባ፣ እማማ፣ ተብለን ወንበር የሚለቀቅልን፣ ስንገባ ነወር የሚባልልን፣ ሽማግሌዎች፣ ላስታራቂነት የምንፈለግ፣ የሰፈር ሕጻናት የሚፈሩን፣ የሚያከብሩን፣ አዛውንቶች እንሆን የነበርን ዛሬ እዚህ ባለንበት ሃገር፡ በስድብ ይወርዱብናል፣ የምናየው ደስ አይልም። ለምስክርነት የተቃወሟቸውን ግለሰቦች በሞት የተለዩ ወንድማቸውን እንኳን ባደባባይ እንዳይሰናበቱ፣ እንዳያለቅሱ ሲከለክሉ አስተውለናል። ሊደባደቡም ይቃጣቸዋል፣ ያስፈራራሉ። በደፈናው እዚህ ዳላስ ያልደረሰ ውርጅብኝ ምን አለ? ያም ሆኖ ግን ይህንን መላና  ዘይቤ  ብለው የተነሱ እየተጋለጡ መጡ እንጂ፣ የሚናገሩት እስኪጠፋቸው ድረስ ያልሆነ ያልተደረገ አወሩ እንጂ፣ በቤተክርስቲያን ሽፋን የፖለቲካ አጀንዳ ይዘው በፖለቲካ የራቃቸውን በእምነት ሽፋን ገቡበት እንጂ፣ አባላቱን በተኑት እንጂ፣ ምንም ያተረፉት ነገር እንደሌለ ምስክሩ ምእመኑ ነው። የምናወራው ስለ ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የችግር ጉዞ  ነው።

የቤተክርስቲያኑ ተመራጮች፣ ካህናትን አባረሩ፣ የሚሰበከውን እኛ አስቀድመን ማወቅ አለብን አሉ፣ ችግራቸው ግን  አልተፈታም።
እንዴት ቤተክርስቲያን ይከሰሳል እኛ እንደልባችን ፈልጠን ቆርጠን እንግዛችሁ አሉ። ሕዝቡ ግን መክሰስ የሚያውቅ ሰው እኮ የሕግን የበላይነት የተቀበለ ነው አላቸው። አትናገሩ ብላችሁ ስታፍኗቸው፣ በፖሊስ መቅደሱን ስታስደፍሩ፣ ምን ማድረግ ነበረባቸው? ብሎም ጠየቃቸው። መልስ አልነበራቸውም። ያም ሆኖ  ሕዝቡ ግን ምን መአት ወረደብን ብሎ ወደ  ፈጣሪው እግዚኦ ማለቱን አላቆመም። በወንጀል ባደባባይ እየተከሰሱ እንኳን አበስ ገበርኩ ሳይሉ አሁንም የመንፈሳዊ ቤት መሪዎች  ነን ሲሉ ቅር አላላቸውም። ስለ ልጆቻቸው ሳይናገሩ ስለ ልጆቻችን ሊነግሩን ይፈልጋሉ። ስለ ባለቤቶቻቸው ሳያወሩ ባለቤቶቻችንን ሊወርፉ ይነሳሉ። የብዙውን ግለሰብ ሥም በየብሎጉ በውሸት እያብጠለጠሉ፣ ትዳር ሊያፋቱ፣ ጎጆ ሊያፈርሱ፣ ተነስተው ያሰቡት ሳይሆን ቀርቶ የተገላቢጦሽ ችግሩ በራሳቸው ላይ ሲመጣ እንደ ምልክት ቆጥረው አምላክን ሲማለዱ ግን አላስተዋልንም።

አንድ ነገር ግን እውነት እየሆነ  መጣ። በሕግ አምላክ ያሉት ግለሰቦች የተናገሩት አንዱም ከመሬት ጠብ አላለም። የዛሬ 4 ዓመት የጻፉት በቅደም ተከተል እየደረሰ  ነው። አሁንም እኛ ያስተዋልነውን እንንገራችሁ። የምናስበውን ካላደረግን ከሥልጣን አንወርድም የሚሉት ባለስልጣናት ይህን ማድረጋቸው መብታቸው ነው ለማለት ግን ጊዜ  አይወስድብንም። ሕጉን እንደፈለጋቸው መቀየር ይችላሉና። የዛሬ  ሳምንት ባዋጅ  ያራዘሙትን የምርጫ ጊዜ እስከ ማርች አይደለም እስከ ኦሜጋ ማድረግ ይቻላቸዋል። መንግሥት እነሱ ናቸውና። ማርች ያሉት ደግሞ ጾም ይገባልና  በጾም መሰብሰብ አይቻልም ብሎ ቀኑን ለማራዘም እንደሆነ  የሚጠፋው ሰው ይኖራል ብለው ያስቡ ይሆን? እንደዚህ ካሰቡ ተሳስተዋል። ትላንት ሲያደርጉት በማየታቸን ለኛ አዲስ አይደለምና?። የአባልነት ክፍያ ከስድስት ወር በላይ ያዘገዩትን በመሃል ተናደውባቸው የነበሩትን ጓዶቻቸውን ለመመለሰ የመክፈያውን ጊዜ አንድ ዓመት እንዳደረጉት ሁሉ ሌላም የመቀልበሻ  አዋጅ ማወጅ ይችላሉ። ሕግ እነሱ ናቸውና። የሚነዳቸው ነገር ቢኖር የመንግስተሰማያት ቁልፍ በእጃቸው አለመኖሩ ብቻ  ይመስለናል። ያ ስልጣን  እነሱ ጋ ባለመኖሩ  ፈጣሪ ምስጋና ይግባው እንላለን።  ከዛሬ  ጀምሮ  የቦርድ አባል መሆን የሚችለው ከደብረታቦር  አውራጃ ከፋርጣ ወረዳ  የመጣ ብቻ  ነው ማለት ይችላሉ። ትግሬ  ከሆንክ የሸዋ ሰው የደቡብ ከሆንክ እኛ የምንለውን የምትቀበል ከሆነ  መልካም ካልሆነ ግቢያችንን ልቀቅ ማለት መብታቸው ነው። ሕግ በእጃቸው ነውና።  የምእመናን ግዴታ ደግሞ እነሱ ያሉትን መቀበል ብቻ ነው። እምቢ አሻፈረኝ የሚል ካለ ከቤተክርስቲያኑ ይባረራል፣ ተባሯልም። ይህ አልሆነም? አይደረግም? የሚል ካለ ለቤተክርስቲያኑ የለፉ እምነት ያላቸው ፈሪሃ  እግዚአብሔር ያደረባቸው ምእመናን ሰላም ባሉ ፍቅር በመናገራቸው የእምነትና የትግል የመደብ ጀርባቸው ተመርምሮ ከአባልነት የተከለከሉ የመስራች አባላት ስም መደርደር ይቻላል። የሚያሳፍረው ግን የሚያባርሩትንና የተባረሩትን ማመዛዘን  ሲጀመር ነው።

የቀድሞ  የቦርድ አባላት ሕጉን ከአባላት ፈቃድ ውጭ  መቀየር እንችላለን ሲሉ እግዚኦ  የመብት ያለህ የተባለው "ዛሬ ሕጉን የቀየሩ የቦርድ ባለስልጣናት ነገ  ሕጉ በነሱ ላይ እንደሚያነጣጥር ይወቁ ብለን የጮህነው፣ ይህ እንዳይከሰት ነበር።" "ገንዘብ በሰላሳ  እውቀት በስልሳ " ይሏል ይህ ነው።

አባቶችን እየተጋፋ ቀሳውስቶችን እያስፈራሩ እንግሊዝኛ የማይናገር ሁሉ መሃይም ነው ሲሉ ከረሙ። ባለፈው እሑድ በሰላም ያረፉትን መንፈሳዊ አባት አቡነ  ይስሐቅን ጭምር ሳይቀር ሲዘልፍ የነበረው የቤተክርስቲያናችን ዲያቆን ጸሎትና ምህላ  የሚያስፈልገው ሆኖ  ታይቶናል። በነገራችን ላይ ጳጳሳት ከግብጽ በሚመጡበት ሰዓት አረብኛ ተናጋሪ እንዳልነበሩ ሁሉ፣ በአገራችን ያሉ የመንፈሳዊ አባቶች በግእዝ የተካኑ እንጂ ብዙዎቹ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንደማይናገሩ እየታወቀ ዛሬ እኔ እንግሊዘኛ በመናገሬ  ብቸኛ አዋቂ ነኝ ብሎ ሲዝናና ያየነው ዲያቆን ለድፍረቱ እግዚኦታ የሚያስፈልገው ነው። የስደት ሲኖዶስ እደግፋለሁ እያለ የአስታራቂ ለምድ ለብሶ የነበረው ይህ ዲያቆን ማንነቱን ለማወቅ ለብዙሃኑ ጊዜ  ፈጅቶ እንደሆን እንጂ እኛስ ቀደም ብለን አውቀነው ነበር። አገር ቤት ያሉ አባቶችም እያወቁ በምህረት ሲያልፉት ከርመው ሲበዛባቸው የወሰዱትን እርምጃ  ሁላችንም ያየነው ነው። ከእንግዲህ ለሰማይ ቤታችን እንጂ አላፊ ለሆነው ለአንድ ዓለም ባንጨነቅ መልካም ነው እንላለን።

ይህንን ካልን ዘንዳ በማጠቃለያው የምንናገረው አለን።

በስልጣን ላይ ያሉትን የቦርድ ባለስልጣናት የምንላቸው ነገር ቢኖር፣ ከወረዳችሁ ላትመለሱ ስለምትችሉ ሕጉን በመቀየር እራሳችሁን እድሜ ልክ ተመራጭ አድርጋችሁ እንድታስቀምጡ ነው።

ከውጭ ሲኖዶስ ጋር ከመቀላቀላችሁ በፊት የናንተን ዘላለማዊ ስልጣን እንዲቀበሉና  እንዲያጸድቁ በጽሁፍ ማረጋገጫ ብትጠይቁ መልካም ነው።

ከቤተክርስቲያኑ ስም ላይ የኢትዮጵያ የሚለውን ወደፊት ጭቅጭቅ እንዳይፈጥር አንስታችሁ በምትኩ ጁፒተር ወይም ጋርላንድ በሚል ብትቀይሩት የተሻለ  ነው። 

የእናንተን ስም  በመቅደስ የማያነሳ ካህን ካለ ማባረርን አትርሱ።

በስማችሁ ስለት የማያስገባ አባል ካጋጠመ አስወገዱ።

እናንተን የሚረዳ ከሆነ  በውስጥ ጠንካራ  ደጋፊ የሆነውን ጵጵስና አሰጡ።

የተረፈ  ገንዘብ ካለ የሚመጡት እንጋራ  እንዳይሉ በስማችሁ ሞግዚትነት ተከፋፍላችሁ አስቀምጡ።

በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እምነት፣ መብት፣ ፍቅር፣ መከባበር የሚሉ አባባሎችን በድንጋጌ አዋጅ አግዱ።

ገንዘብ የሚከፍል ከጠፋ ከበር ላይ ደህና  ጎበዝ በማስቆም የመግቢያ ዋጋ ማሰባሰብ ጀምሩ።

የዛሬ  3  ዓመት እንደጠቆምነው ገቢው ካነሰ  ቅዳሴ  ጠበል በገንዘብ መሸጥን እንደ  ገንዘብ ማሰባሰቢያ  ተጠቀሙበት። 

የፖለቲካ አባላትን በማሰባሰብ እራሳችሁን አጠናክሩ።

ይህ ብዙውን "ችግራችሁን ይቀርፈዋል" ብለን እናምናለን።

ለሰማዩ ሳይሆን ለዚች አንድ ዓለም ምኞትም የሚያሟላ ይመስለናል። ይስመርላችሁ 11.2 ውሎ ይደር! አሜን።

ከዚህ በመቀጠል ካንባቢ የተጠቆምነውን ጽሑፍ ለእናንተ ለማዳረስ የድህረ ገጽ አድራሻውን ቀጥለን አስቀምጠንዋልና  በመጫን እንድታነቡ እንጋብዛችኋለን።

የሲኖዶስ የፈተና ጉዞ
https://docs.google.com/file/d/0B5ikXekolDC4TWplNG1yZEVUZzg/edit?usp=sharing

Tuesday, December 11, 2012

ሰላም የሚፈጠረው ሰላም ብሎ በመነሳት ብቻ ነው።


                    ሁሉንም ቻይ አምላክ እንደየሥራችን የእጃችንን ይከፍለናል ማለት እውነት መሆኑ ባይካድም ምሕረቱ  የማያልቅበት እየሱስ ክርስቶስ አብሮት የተሰቀለውን ነፍሰ ገዳይ እንደማረ ሁሉ እኛንም በምሕረቱ ይዳስሰናል ብለን እናምናለን። ደካሞች ነንና ጥንካሬን፣ ፈሪዎች ነንና ድፍረትን፣ ንፉግ ነንና ቸርነትን፣ ቂመኞች ነንና ይቅርታን፣ ከሀዲዎች ነንና እምነትን፣ እንደሚቸረን ደግሞ ደጋግሞ የተነገር በመሆኑ የቃሉ ፍጻሜ ላይ መጠራጠር ከሌለ በስተቀር ይሆናል ያለው እንደሚሆን  በሙሉ እምነት መናገር ይቻላል። 
            አዞ አፉን ከፍቶ በመተኛቱ የሞተ እየመሰላቸው የሚጠጉትን  እንደሚያድን ሁሉ የፈጣሪን አምላክነት የሚፈታተኑትን በመንግሥቱ ቀናዊ ነውና እንደሚገስጻቸው ደግሞ ለዘመናት ያየነው ያስተዋልነው በመጽሐፍ ያነበብነው ነው። 
             ይህንን ካልን በኋላ ሰሞኑን በዚህ በዳላስ የተደረገውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን የሰላም ጉባኤ  በጉጉት ከጠበቁትና በመጨረሻም በውጤቱ ከተበሳጩት መሃል እራሳቻንን እንደምራለን። ሰላም ወረደ ማለት የሁሉም ጊዜ እምነትን በማስፋፋትና በማጠናከር ላይ እንጂ በማፍረስ ላይ አይሆንም ከሚል አመለካከት። የመንፈሳዊ አባቶች ሱባኤና ጸሎት፣ የምእመናን ለቅሶና እግዚኦታ ምላሽ ያገኝ ይሆናል ከሚልም መንደርደሪያ  በመነሳት ነበር።   
       ለምን አልሆነም ለሚለው የበኩላችንን መናገር እንችላለን። ዋንኛውና  የማንጣላበት ግን እሱ ስላልፈቀደ ብቻ  ነው። ከሃገር ቤት የመጡ አባቶች ግዝትን አንስተው እዚህ ያሉትን መንፈሳዊ አባቶች ስልጣን ተቀብለው ከነክብራቸውና ከነማእረጋቸው እንዲገቡ መስማማታቸውን ሲቀበሉ፣ በስደት ያሉ መንፈሳዊ አባቶች  ግን ለ 20 ዓመት ሲያነሱት የኖሩትን የመንበረ  ስልጣን ጥያቄ አሁንም የሙጥኝ  ማለታቸው ግን ሁላችንንም አሳዝኖናል።
                    ክርስቶስ እንደሚገደል እያወቀ  ወደ  መሰቀያው የሄደው እኮ መሰወር አቅቶት አልነበረም። የሰቀሉትን ግፈኞች የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ያለው መቅጣት ተስኖት አልነበረም። የተሰቀለው በደሙ ከሃጥያታችን ሊያነጻን ይቅር ያለው ምህረትን ሊያስተምረን ነው እንጂ። ለሐዋርያት ስልጣን የሰጠውም እንደኔ ሆናችሁ አስተምሩ በስሜ  ወንጌልን ስበኩ ህሙማንን ፈውሱ አርአያም ሁኑ በማለት ነው። ታዲያ አባቶች ለዚህ መንፈሳዊ ስልጣን ያበቃቸውን አምላክ በተሰበጣጠረው ምእመን ችግር መፍትሄ  እንጂ መለያያ ባይሆኑ እንዴት መልካም ነበር። መቼም እድሜ የማይደበቅ ስጦታ ነውና ለመጠራት የቀረን ስንት ጊዜ  ይሆን  ብሎ መጠየቅም መልካም ነው። ሰላምን ለሚፈልግ ምእመን ሰላም ለክሙ ማለት እንጂ መለያየትን እንዴት ለማሳለፍ ይፈለጋል። ተአምር የሚገለጽባቸው ገዳማት ደግሞ ያሉት ሃገር ቤት ነው ብለን እንቀበላለን። ያ የሆነው በየጥሻው በየዋሻው፣ በየሰቀላው፣ በየዱር ገደሉ ተጠልለው በሚጸልዩ መነኮሳትና አበው እንደሆነ እናምናለን።
              ስለሆነም ዛላለማዊ ስፍራን እንጂ ጊዚያዊ ወንበርን በመተው ለሰላም እንዲነሱ እንለምናለን። ፈጣሪያችን የኢትዮጵያን ለቅሶ ሰምቶ ምህረቱን ይላክ።




Thursday, May 10, 2012

ማን አሸነፈ?

በቤተክርስቲያን አሸናፊ አይኖርም ብሎ  መረዋ የጻፈው ከ ፫ ዓመት በፊት ነበር። መረዋ ዛሬም ማንም አሸናፊ አይደለም ብሎ ያምናል። እንዴውም የገደለው ባሌ  የሞተው ወንድሜ የሚለውንም እንደ ምሳሌ መጠቀሙን ያስታውሳል። እንሆኝ የቤተክርስቲያናችን ውጣ ውረድ ከተጀመረ ከ ፬ ዓመት በላይ ሆኗል።
ይህ ሁሉ ውጣ ውረድ ይህ ሁሉ ክስ የመጣው ደግሞ ከሳሾች ገንዘብ ፈልገው አልነበረም።
ቢሆንማ  ኖሮ ካሳ በጠየቁ ነበር።
ለስልጣን ብለውም አልነበረም።
ቢሆንማ  ኖሮ ምእመን ሳይወያዩበት በቦርዱ "ጸደቀ"  የተባለው መተዳደሪያ ደንብ ለተመራጭ አስተዳዳሪዎች የፈላጭ ቆራጭ ስልጣን የሚሰጥ ነበር።
ለንብረትም አልነበረም።
ቢሆንማ  ኖሮ የንብረት ክስ ከተመሰረተ  ፍርድ ቤቱ ያገባዋልና ይወስንላችኋል ሲባል የንብረት ክስ አንመሰርትም ባላሉ ነበር።

ነገሩ የመብት ጉዳይ ሆነና ይኸው እስካሁን እያወዛገበ ይገኛል። ለስለሰብአዊ መብት እንከራከራለን የሚሉ ግለሰቦችና  ድርጅቶች መብት እንንፈግ ብለው ሲዶልቱ መክረማቸውን ያያችሁት ጉዳይ ነው ። በመብቴ  አልደራደርም ያለው አባል ከአባልነት እራሱን እያሸሸ ለመምጣቱ ደግሞ ምስክር መጥራት የሚያስፈልግ አልመሰለንም። ምስክሩ እናንተ ናችሁና።

፴ ብር ለይሁዳም አልበጀምና  ተው ሲባል ሰሚ አልነበረም። ይህ ግን ቤተክርስቲያኑን አደኸየ  እንጂ አልጠቀመም።
አቶ  ኃይሉ እጅጉ በመሰረቱት ቤተክርስቲያን አዳራሽ ለመብት ቆመሃልና  አትገባም ሲባሉ የዓይን ምስክር ነበርን። ነበራችሁ።
አቶ ሙላው ወራሽ እንደ ወረደባቸው አሉባልታና የስም ማጥፋት ዘመቻ  አገር ለቀው ይወጣሉ ብለው የጠበቁ ቢኖሩ የሚያስገርም አልነበረም።ያ ግን አልሆነም።

ደጋፊም ተቃዋሚም አሁንም አንድላይ ነን። አሁንም አንድ ላይ እያስቀደስን ነው ማለት እውነት ነው። ጸሎታችንን እኩል ይሰማል ማለት ግን አጠያያቂ ይሆናል። ትላንት ከአዳራሽ ያስወጡ የነበሩ እራሳቸው እንደወጡ ያያችሁት ነውና  መድገም አያስፈልግም።

ሰባት ጊዜ ሽማግሌ አናግረናል የሚሉት የመብት ተከራካሪዎች፡ ሰባቱንም ጊዜ ከሽማግሌዎች ጋር በአክብሮት ተወያይተን ተለያይተናል ብለው በልበ ሙሉነት ይናገራሉ። በምስጋና የተለያዩት የመብት ተከራካሪዎች፣ የሚኮሩበት ጉዳይ ቢኖር ሽማግሌዎቹን ማሳመን መቻላቸው ብቻ  ሳይሆን ከመሃከላቸው ደጋፊና አብሯቸው የሚታገል ማትረፋቸው ነው። የዛሬ ሳምንት በቤተክርስቲያን የቦርድ መሰብሰቢያ  አዳራሽ በመገኘት ሁለቱም ወገኖች ታረቁ ተብሎ ሲነገር ሕዝቡ እልል ሲል ያየ ቢያለቅስ ምን ይፈረድበታል? ሁኔታው ግን ሰዓታትም ሳይቆይ  እርቅ ፈርሷል ተባለና ተቀየረ። ማን እንዳፈረሰው ደግሞ  ሽማግሌዎቹን መጠየቅ ይሻላል እንላለን።

የመብት ታጋዮቹን ደገፋችሁ በሚል የወሲብ አሉባልታ የተነዛባቸው ጠነከሩ እንጂ ሸብረክ ሲሉ አላየንም። ባልሰሩት የነፍስ ግዳይ የተወነጀሉት አሁንም እስር ቤት ገብተው አላየንም። ከመብት ተከራካሪዎቹ ቃለ አባባል እንውሰድ " እኛ የእምነትና የእውነት ድሃ  አይደለንም" የሚል ነው። ፍርድ ቤት ይለየን እንደተባለው እነሆ ፍርድ ቤት እየለየው ነው። ማሸነፍን ግን አላየንም።

 ውድ አንባብያን ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት የቦርድ አባላት ከሳሾችን ከዓመት በፊት ከቤተክርስቲያን እናባራችሁ ብለው በወሰኑባቸው ማግስት አታባርሩንም በሚል ስማቸው ተካቶ ከነበረው 28 ተባራሪዎች ውስጥ የሆኑ ምእመናን ክስ መመስረታቸው ይታወሳል። በመሆኑም የነበረውን በየጊዜው የፍርድ ቤት ውሎ መረዋ በወቅቱ የዘገበው ጉዳይ ነበርና ዛሬ ወደ ኋላ ተመልሶ ሁኔታውን በመተንተን ጊዜአችሁን ከመሻማት ይቆጠባል። ነገር ግን የዛሬ ዓመት ክሱን እናቁም በማለት ከሳሾች ከደጋፊዎቻቻው ጋር በመስማማት ክሱን ቢያቆሙም ቦርዱ እስከዛሬዋ የፍርድ ሰዓት  ድረስ ለጠበቃ ያወጣንውን 89,000 ብር ይክፈሉን ሳይከፍሉን ክስ አናነሳም ብለው ሲከራረሩ ቆይ ተው ነበር። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ዳኛው የዚህን ክርክር የመጨረሻ ውሳኔ በመስጠት ገንዘብ መጠየቅ አትችሉም  ብለው ብይናቸውን ሰጥተዋል። ይልቅስ ይላሉ ዳኛው ይህንን የእምነት ጉዳይ በቤተክርስቲያን ደንብ በውስጥ ለመፍታት ብትሞክሩ መልካም ነው። በማለት ምክራዊ ብይንም ሰጥተዋል። ከሳሾች ለቦርድ አባላት ፩ ብር (አንድ ብር) እንዲከፍሉ እንደተወሰነባቸው ደግሞ የነገሩን የመብት ተከራካሪው ቡድን አባል ለዚህ ምእመናንን እርዳታ  አንጠይቅም በማለት እየሳቁ ነበር።

ይህ ቦርዶቹ የሚጠይቁት የጠበቃ  ገንዘብ  ባለፈው አወጣን የሚሉትን ከ140,00 ብር በላይ የሆነውን አያጠቃልልም። በቅርቡ መረዋ የደረሰውን የቦርድ አባላት ባለፈው ፩ ዓመት ተኩል ለጠበቃ ከፈልን ብለው ፍርድ ቤት ያቀረቡትን የ 89,000 የወጭ ሰንጠረዥና ከሳሾች በሁለት ዓመት ለጠበቃ  ከፈልን የሚሉትን 21,593 ብር  የወጭ ሰንጠረዥ  ያጠቃለለ  በገጹ ላይ እንደሚያትም ቃል ይገባል። ከየትም ይሁን  ከየት ማንም ከፈለው ማ ከፋዩ የቤተክርስቲያናችን አባላት ያዋጡት ገንዘብ ነውና።  ለአባላት ይጠቅም ዘንድ በእጃችን ያለውን ማናቸውንም መረጃ እንዳስፈላጊነቱ ለማሳወቅም እንደምንጥር ሰንናገር በእርግጠኝነት ነው።

ለመንፈሳዊ አባቶች ያለንን አድናቆትና አክብሮት እየገለጽን የኛን ወገን ዜና ማሰራጫ ሌላ መድረክ ስለሌለን ይህንን የመተንፈሻ ገጽ መጠቀማችንን እንዲረዱልን እንወዳለን።

ውድ ምእመናን ከኛ ወገን የሚተላለፍ መልእክት አለን 

ከጎናችን ሆናችሁ ለከረማችሁ፣  ለእውነት ስለቆማችሁ፣ ለተሰደባችሁ፣ ለተባረራችሁ፣ ሁሉ ሚካኤል ዋጋችሁን ይክፈላችሁ እንላለን። እኛና  እናንተ  እንቅልፍ ተኝተን እናድራለን እንቅልፍ ያጡ ሌሎች ናቸው።
እኛና እናንተ  በእሳት ተፈትነን የሕይወት ጓደኛ ሆነናል።
በየወንዙ የሚማማሉት ሌሎች ናቸው።
እኛ ትናንትናም ዛሬም ትክክል ነበርን፣ ለሰላምና ለአንድነት ታግለናል።
አቋማቸውን እንደጥላ  የማያምኑት ሌሎች ናቸው። 

ሚካኤል ፍርድ እየሰጠ ነው። ለክፋት በቆመው ላይ የዘላለም ፍርድ ይስጥ። 

እኛ ማንንም አንጠላም ለሚጠሉን እንጸልያለን።
በማንም ላይ አንፈርድም፣ በሚፈርዱ እናዝናለን።
ማንም ከስራ  እንዲወጣ አንፈልግም፣ ይህን ለሚያስቡ ሱባኤ  እንገባለን።
በማስፈራራት አንፈራም ከጥል ይልቅ ለፍቅር እንሰግዳለን።
ቤተክርስቲያናችን እንደሚኖር እኛ ግን እንደምናልፍ እናምናለን።
ቤተክርስቲያን የአባቶችና የክርስቲያን ስብስብ እንጂ ሕንጻና ገንዘቡ ነው ብለን ለደቂቃም አናምንም።  

ለሰላም እንጸልይ።

እንኳን ደስ አለን።

Saturday, May 5, 2012

ለሁሉም ነገር መጨረሻ አለው

ውድ የመረዋ ታዳሚዎች። ለረጅም ጊዜ በዝምታ በመሰንበታችን የት ደረሱ? ብላችሁ ለጠየቃችሁ ሁሉ አለን ከማለት ውጭ ሌላ የምንጨምረው የለንም። ስለሆነም ሰሞኑን የከረምንበትን ሁሉ በቅደም ተከተል ለናንተ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናችንን ስንነግራችሁ በደስታ ነው። ችግራችን ትላንት እንደ ነበረው ሳይቀየር ያለ  ሲሆን መለስተኛ ለውጦች የሉም ብለን መናገር ግን ይከብደናል። ከሶስት ዓመት በፊት የተናገርነው አሁን እየተፈጸመ ያለው ትንቢት ሆኖ  ሳይሆን እውነታ  ስለነበረ ብቻ  ነው። ሰሞኑን ያመታት ቅምራችንን እናቀርባለን። እስከዛው ደህና ሁኑ።

Thursday, July 14, 2011

የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ

ውድ ምእመናን እንደምን ከረማችሁ እኛ በፈጣሪ ቸርነት እስካሁን አለን። ምነው ጠፋችሁ?  ብላችሁ ለጠየቃችሁን መልእክት ለጻፋችሁልን ሁሉ አለን ክብሩ ይስፋ ለመድኅኒዓለም  እንላለን። ከ ሁለት ቀን በፊት የ5ኛው districte ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በወይዘሮ  ጥሩአየርና  በአቶ ዳግም በተመሰረተው የቦርድ አባላት ያለአግባብ የስልጣን አጠቃቀም ክስ ላይ ብይን መስጠቱን ለአንባብያን መናገር እንወዳለን። መረዋ  ብይኑን ሙሉ ለሙሉ አንባብያን እንድታነቡት ሲያቀርብላችሁ እራሳችሁ አንብባችሁ ግንዛቤ  እንድትወስዱ በማሰብ ነው። በተከበሩት ዳኛ ኤልዛቤት ሜየር የተጻፈው የብያኔ  ትችት እንደሚያስረዳው፣ ይግባኝ ባዮቹ ከሳሾች የቤተክርስቲያኑ የቦርድ አባላት አላግባብ ስልጣናቸውን ተጠቅመው መተዳዳሪያ  ደንቡን መቀየራቸው አግባብ አለመሆኑን ጠቅሰው መክሰሳቸውን ተነተርሶ የቀረበ  ክስ መሆኑን አስታውሶ ክሱ በመብት መደፈር አኳያና የቤተ ክርስቲያኑ ንብረት ይገባኛል ጥያቄ አንስቶ ቢሆን ኖሮ ፍርድ ቤቱ መግባትና መወሰን ይችል እንደነበር አውስቶ ነገር ግን በመተዳደሪያ  ደንቡ ላይ ብቻ ያተኮረ ስለሆነ ይህ ደግሞ በውስጥ መፈታት ያለበት እንጂ ፍርድ ቤት በእምነት ውስጥ ጣልቃ  መግባት የለበትም የሚል ብዙ ተመሳሳይ የቆዩ ውሳኔዎችን በመጥቀስ የበታች ፍርድ ቤት ቦርዱ የመተዳደሪያ  ደንቡን መቀየር ይችላል ብሎ  የበየነውን ውሳኔ አጽንቶ ወስኗል። የቤተክርስቲያን ቦርድ አባላት ክሱ በውሸት የተመሰረተ  የቦርድ አባላትን ስራ ለማስፈታት የተመሰረተ  መሆኑን የይግባኝ ፍርድ ቤቱ እንዲወስንላቸውና  ካሳ  እንዲጥልላቸው ያቀረቡትን ሳይቀበለው ቀርቷል።

ለምን ታዲያ የንብረት ይገባኛል ጥያቄውን ከመጀመሪያው አላነሳችሁም ብለን ያነጋገርናቸው ለጉዳዩ  ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች የነገሩን ቢኖር ከመጀመሪያው ይህ  ሃሳብ ቀርቦ የከሳሾች ፍላጎት የቤተክርስቲያኑን አባላት መብት ለማስጠበቅ እንጂ ለመበታተን ስላልነበር ሃሳቡ ተነስቶ  ውድቅ እንደተደረገ ለመገንዘብ ችለናል።

ባሁኑ ሰዓት ግን የንብረት ይገባኛል ክስ ቢመሰረት ማንም ምእመን ሊቀበለው የሚችል ለመሆኑ በሂደት በቤተክርስቲያኑ አባላት ላይ የደረሰው በደልና  አሁን ቤተክርስቲያኑ ያለበትን  በማሰብ መናገር ይቻላል ብለው እንደሚያምኑም ለመረዳት ችለናል።

መረዋ  በእትምት ጅምሩ ላይ የጠቆማቸው ሁሉ ተራ  በተራ ተፈጻሚ ሆነዋል።

ካህናት ተባረዋል
አባላት ተበትነዋል
የስደት ሲኖዶስ ከበራፍ ቆሞ እየጠበቅ ነው
እምነት ሳይሆን ስልጣን፣ አባላት ሳይሆኑ ተመራጮች ፈላጭ ቆራጭ ሆነዋል።
የነበረው ገንዘብ መንምኗል፥
ፖለቲከኞች መሰባሰቢያ  ሲያገኙ አማንያን ከስብሰባ  ታግደዋል
በእምነት ሳይሆን በፖሊስ ለማስፈራራት ተሞክሯል
የቦርድ አባላት ወንጀል በይቅርታ  ሲታለፍ ግለሰቦች ወደፍርድ ቤት በመሄዳቸው ወይም ቦርዱ የሚደረገውን በመቃወማቸው ነፍሰገዳይ ዝሙተኛ ሌባ ሴሰኛ እየተባሉ ከእግዜር በተላከ ቁጣ የሞት ፍርድ ሳይቅር እንደተፈረደ  ሁሉ ተጽፏል።
በአባላት ላይ የክፍያ  ጫና  ተጥሏል።
በዘር እንዲከፋፈል ተደርጓል
የስደት ሲኖዶስ አባላት ሰፈር ተወለጆች እንዲጠናከሩ ሲደረግ ሌሎች በዘራቸው ተወንጅለዋል።
ሲፈርዱ የነበሩ ፈራጆች ዛሬ ተፈርዶባቸዋል።
የቤተክርስቲያን መስራቾች በመመስረታቸው ተነቅፈዋል ወዘተ

ልንል የፈለግነው ያላሰብነው አዲስ ክስተት አልተፈጠረም ለማለት ነው
ባጋጣሚ ትላንትና የደረሰን ዜና  ደግሞ  ወጣት የቤተክርስቲያን ልጆች ጥያቄ  አቀረባችሁ ተብለው መባረራቸውን መስማታችን ነው። ጥያቄው ምን ነበር ስንል
ለምን የረባ  ምሳ አትሰጡንም?
ገንዘብ የለንም ካላችሁ ለምን መብራትና ቴሌቪዥን ግዢ ሄዳችሁ?
በእኛ ስም ከበጎ አድራጊዎች የተገኘ ገንዘብ የት ገባ?
ሳንማር የምንመረቀው እንዴት ነው? የሚሉ እንደ ነበሩ ለመረዳት ችለናል።

እነዚህ  እዚህ የተወለዱና  ያደጉ ሕጻናት ደግሞ ፖለቲካውም አይገባቸው ውሸትም አይዋጥላቸው፥

መረዋ ላለፉት 5 ዓመት ከልባቸው ለእውነት ለፍትህ ለመብት ለታገሉ ምእመናን በሙሉ ያለውን አክብሮትና አድናቆት እየገለጸ ወደፊትም በዚህ መልክ ለሚነሱና ካሁን በኋላ  የንብረት ጥያቄ  ለሚያነሱ  ሁሉ ድጋፉን ለመለገስ ወደ ኋላ  እንደማይል ካሁኑ ቃል ይገባል።

የማንም መብት ሲጣሰ የግል መብት እንደተጣሰ  መቁጠር ትክክለኛ  ውሳኔ  ነው።

የሚሸነፍ ሰው ለመብቱ የማይነሳ ብቻ  ነው።

ሰላምና ፍቅር ለሁላችሁ ይሁን፥

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንዳለ  ለማንበብ የምትፈልጉ ከዚህ በታች ያለውን በመጫን ያንብቡ

http://www.5thcoa.courts.state.tx.us/cgi-bin/as_web.exe?c05topin.ask+D+510527

Thursday, May 19, 2011

አትደግ ያለው ልጅ በእሳት ይጫወታል።

ወንድሞችና እህቶች እንደምን ከረማችሁ። ካነበባችሁን ውሎ አደረ። በየሳምንቱ በሬ  ወለደ ብለን መጻፍ አልለመደብንምና ወይንም እኛ ስንፈልግ እንጂ ከሌሎች ፉክክር በመግባት እንካ ስላንቲያ ማለት ባለመፍቀዳችን   ለናንተ የሚሆን ዜና አግኝተን እስክናዘጋጅ ድረስ ቆየን። ከወዲያኛው ጎራ የሴት ዘጋቢ የፍርድ ቤት ውሎ እንድትዘግብ ተለምና ከምትጓዝበት እንደቀረችና ፍርድ ቤት እንደዋለች ስናነብ ከምር ከልባችን ሳቅን። መሳቅ ብቻ አይደለም የቆየ የአለቃ ገብረሃናን ቀልድ አስታወሰን። ቀልዱ እንዲህ ነው። አለቃ ገብረሃና ከሸንጎ ላይ እንዳሉ አሽከራቸውን ይጠሩና በጆሮው ያችን ሴት ሂድና ማታ  አለቃ ይፈልጉሻል በልና  ጠይቀህ መልሱን ሰው እንዳይጠረጥር በወንድ ጾታ ቀይርና ንገረኝ ብለው ይልኩታል ሲመለስ ምን አለ? ብለው አሽከራቸውን ሲጠይቁት አሽከራቸው አልችልም ነፍሰ ጡር ነኝ ብሏል አለ ይባል ነበር። አባባሉ ፍርድ ቤት የነበረ ሴት አለማየታችንን ለመናገር ያክል ነው። የነበሩትን በመመልከት ደግሞ ጸሃፊዎቹን ማወቅ ብዙም የተወሳሰበ አልነበረም።

በእለቱ የከሳሽና  የተከሳሽ ጠበቆች ከዳኞቹ ለቀረበላቸው ጥያቄ  መልስ የሰጡ ሲሆን የከሳሽ ጠበቃ ክርክር አጭርና የማያሻማ ነበር። ይኽውም ክሱ የመብት እንጂ የኃይማኖት እንዳልሆነና ቦርዱ ካለ አባላት ፈቃድ በክርክር መሃከል ሕግ መቀየሩ አግባብ አይደለም የሚል ነው።

የቦርዱ ጠበቆች ክርክሩ የኃይማኖት መሆኑን በተለይም መሃበረ ቅዱሳን የተባለ  እምነት በመላው አሜሪካ እየረበሸን ነው ይህም የዳላስ ክስ የዛ ተቀጥላ ነው የሚል እረጅም ገለጻ ማድረጋቸውን ለመረዳት ችለናል። ጠበቆቹ ደግሞ ነገሮች በተራዘሙ ቁጥር ተጠቃሚዎች ናቸውና ለምን የቃል ክርክሩን መረጡ ማለት የዋህነት ነው። የከሳሾች ጠበቃ የቃል ክርክሩን ጊዜ ለመቆጠብና የጠበቃን ወጪ ለመቀነስ እንደማይፈልግ በይግባኝ ወረቀቱ ላይ መጥቀሱ ይታወሳል። የቦርዱ ጠበቆች ግን ገቢያችንን አትቀንስብንም እኛ እንፈልጋለን ብለው ቀጠሮው ተያዘ ክርክሩም ተደረገ። አሁን ዳኞቹ ምንም ይፍረዱ ምን ክርክሩ ይቀጥላል። ምን አልባትም የፌድራል ፍርድ ቤት ሊያየው የሚገባ  አቤቱታም እንደሚኖር ከምንጫችን የደረሰን ዜና ይጠቁማል። 

የሰው ስም ሲያጠፉ ግለሰብን ሲዘልፉ ቤተስብን ሲወነጅሉ የነበሩት የማዶ ጸሃፊዎች መከሰሳቸውን የሰማነው ከነሱ ብሎግ ላይ አልነበረም። በስድባቸው እንደሚቀጥሉና እንደማይፈሩ ያነበብነው ግን በብሎጋቸው ላይ ነው። እንደማይፈሩ እኛም እናውቃለን የሚፈራ ሰው ክፉና ደጉን የሚለይ ብሎም የሚመጣበትን ነገር አመዛዝኖ  የሚለይ ብቻ ነውና።  በፈንጂ የሚጫወት የማያውቅ ሰው ብቻ ነው ይባል የለ። 

ከሳምንት በፊት ቀደም ሲል በድንገት ከመከላችን በሞት የተለየች እህታችንን አርባ ለመደገስ የቤተክርስቲያኑን አዳራሽ $500 ከፍለው ሃዘንተኞቻቸውን የጋበዙት ቤተሰቦች በእለቱ ሊያሳዩት የነበረውን የሟችቷን የሕይወት ታሪክ ያዘለ የ 7 ደቂቃ ፊልም ለማሳየት የማሳያ ፕሮጀክተሩን በመልከላቸው ሲያዝኑ በአካል ታዝበናል። ቦርዱ አይቻልም ብሎ ሲነግራቸው ያዳመጡት ከሐዘንተኞቹ አንዱ ግለሰብ እኛ እኮ ቤተክርስቲያን አጥተን አይደለም እዚህ የመጣነው አልገባቸውም አሁን ግን እስከመጨረሻው አጡን ሲሉ አዳምጠናል። በመንፈሳዊ ጉዳይ ዘር ቦታ ሲኖረው ከማየት ይሰውረን ወንድሞችና እህቶች።  ይህንን የወሰኑት የቦርድ  አባላት የገደለ ጥይት ድምጹ ከሩቅ አይሰማም ብለው ከሆነ ተሳስተዋል። የግፍ  እንባ መጥፎ  መሆኑን ከመጽሐፍ እንረዳለንና። እዚህ ደግሞ ዜና ማሰራጫው ዘዴ ብዙ ነው። ካልሰማው ይልቅ የሰማው ብዙ ነው። ሰምቶ ምን አደረገ? ማለት ግን ትክክለኛ ጥያቄ  ነው።
ሌላው ዜና የቤተክርስቲያኑ የቦርድ አባላት ባለፈው ቅዳሜ አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ ጠርተው እንደ ነበረ የሰማችሁት ጉዳይ ነው። በእለቱ ዙፋነ ወንበር የጨበጡ የመሰላቸው አዲስ ተመራጭ አቶ ሰሎሞን ከጎናቸው ከነበሩት ከአቶ ከተማ ጋር በመሆን።

አቶ  ሃይሉ እጅጉን   
ወይዘሮ ገነት ከበደን
ዲያቆን አርአያ  ኃይለመስቀልን ከስብሰባ  እንዳይገቡ መከልከላቸውን ስንሰማ  አዘንን። ለምን ቢሉ ቤተክርስቲያናችን መልሶ ከመሰባሰብ ወደ መፈራረስ መሄዱ ስለታየን ነው።አቶ ሰሎሞን አባራሪ አቶ ሃይሉ እጅጉ ተባራሪ ------- ወገኖቼ የሆነ ነገር የጎደለ  አይመስላችሁም።
አቶ ከተማ  ቤተኛ ዲያቆን አርአያ ባይተዋር -------- እግዚኦ ማለት አሁን መሰለን።
ወይዘሮ ገነት ተባራሪ ቀሪው አባራሪና አጋፋሪ------- ነገ  በኔ ማለት ይገባል።
የንብረት ጥያቄ  ቢመጣ እኮ ድርሻህን አሳየኝ ማለት እንደሚጀመር አንርሳ። የአቶ ኃይሉ እጅጉ በሺህ የሚቆጠር ችሮታ ቤተክርስቲያኑን እንደ ገነባው የምንጣላ  አይመስለንም። የአቶ  ከተማና የአቶ  ሰሎሞን ፉከራ  ግን  ቤተክርስቲያኑን  እያፈረሰው እንደሆነ አከራከሪያ ሆኗል። 
የዲያቆን አርአያ ለዚህ ቤተክርስቲያን ያበረከቱት አስተዋጽ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። የአሁኑ የቦርድ አባላት ውሳኔ  ግን የቤተክርስቲያኑን ውድቀት እንደሚያጣድፈው እድሜ  ሰጥቶን የምንመለከተው ይሆናል።
የወይዘሮ ገነት ከበደ ለዚህ ቤተክርስቲያን ያደረጉትን እርዳታ ለማወቅ ምስክር ፍለጋ መሄድ የሚያስፈልግ አይመስለንም ። ምስክር የሚያስፈልገውስ የዛሬዎቹ ፍርድ ሰጪዎች አስተዋጽኦ ጉዳይ ነው። 

ግለሰቦቹ መዋጮ ሲከፍሉ እንቢ አልተባሉም። እምቢ የተባሉት ገብተው የሚያቀርቡት ጥያቄ ስላስፈራ ብቻ ነው።  የሕግ ሰዎች ይህንን
taxtion without reperesentation  ይሉታል።

ዛሬ የተባረሩትን አይተናል ነገ ደግሞ ሽማግሌ ነን ብለው የተቀመጡት አዛውንቶች ተራቸው ይደርሳል። ያኔ እነሱ ዛሬ ተነሰተው እንዳልቆሙ ሁሉ ለነሱም የሚቆም ይጠፋል። ትላንት ሕጉን ያጸደቁ ዛሬ ያሳለፉት ሕግ እነሱን እየጎዳቸው እያስተዋልን ነውና።

የድሮ ታሪክ ታስታውሳላችሁ ሁለት ሴቶች አንድ ሕጻን የእኔ ነው በማለት ተካሰው ቀርበው ዳኛው የማንኛችሁ እንደሆነ ማወቅ ስለማይቻል ሕጻኑ በቢለዋ ለሁለት ተሰንጥቆ ተካፈሉት ብለው ሲፈርዱ እናት ያልሆነችው በፍርዱ ስትስማማ እውነተኛዋ  እናት ግን እኔ ይቅርብኝ ሕጻኑን እሷ ትውሰደውና ታሳድገው  ያለችው። እኛም ያለውን ሁኔታ ስናስተውለው ከሳሾች ቤተክርስቲያኑን ለማዳን ቦርድ ነን ባዮች ደግሞ ፍርስርሱን ለማውጣት እየተጣደፉ ያለ ይመስለናል።

የቅዳሜው ስብሰባ  ምልዓተ ጉባኤው  አልሞላም ተብሎ  መበተኑን ስንታዘብ ሊቀመንበሩ አቶ  ሙሉጌታ  እንዳሉት ሁለተኛ ስብሰባ  በ 4  ይጠራና አሁንም በቂ ሰው ካልተገኘ በሕጉ መሰረት የቦርዱ ውሳኔ  ተፈጻሚነት ይኖረዋል። ብለዋል ይህ ደግሞ መጀመሪያ ሕጉን ቀየርን ሲሉ የተነሳውን  ተቃውሞ ያጠናክረዋል። ቦርዱ መተዳደሪያ ደንብ እንደ ፈለገው ከቀየረ፡ኮረም አልሞላም ብሎ  የ$10000 የእደሳ ባጀት ካጸደቀ፣ የማይፈልጋቸውን ማባረር ከቻለ አባል የሚኮነው ለምን ይሆን?

አንድ የገረመን ነገር ቢኖር የተባረሩትን ግለሰቦችና ያባራሪዎቹን የክርስትና እምነት ጥንካሬ ስናሰላስል የተሰማን ሃዘን ነው። እስቲ እያንዳንዳችሁ በግላችሁ ታዘቡ ፍርዱን እናንተው ለናንተው ስጡ።
 
ማን ነበር ተከራይና አከራይ እኩል ለቤቱ ጣራ አይጨነቁም ያለው? እየቆየ አባባሉ እየታወሰን  ተናጋሪው እየጠፋን ነው።
 
ይልቅስ አንድ የታወቀ ባንክ ዘራፊ ተይዞ ለምን ባንክ ዘረፍክ?ተብሎ ሲጠየቅ የመለሰውን እናስታውሳችሁና  እንሰናበታችሁ "ገንዘቡ ያለው እዛ ስለሆነ  ነው" ብሎ  ነበር። ቦርዱ የላከው 2009 የሂሳብ ሰንጠረዥ $ 75000 ለጠበቃ እንደዋጣ ያሳያል 2010 ስንት እንደሆነ አልነገሩንም ምናልባትም አይነግሩንም ይህ ገንዘብ የወጣው  እነ አቶ ሃይሉ እጅጉን ለማባረር፣ እናቶ ከተማን ለመሾም መሆኑ ነው። የፖለቲካ  ፍልሚያ  ነው ስንል ያልሰሙን ሰዎች ዛሬ እውነት አላችሁ ይሉናል ብለን እናምናለን።
 
በጉልበትና በፍርድ ቤት ፍቅር አይመሰረትም እውነትን የያዘ  ያለጥርጥር ያሸንፋል።

በእሳት የሚጫወት ግን አትደግ የተባለ ብቻ  ነው።

Wednesday, April 27, 2011

እሱ ከመቃብር ተነስቷል እኛስ?

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ። ለመጭው ዓመት በሰላም አቅፎ  ደግፎ  እንዲያደርስን እየጸለይን ሰላምና  ፍቅሩን እንዲያድለን አጥብቀን እንለምነዋለን።
መረዋ ከብዙ ዓመታት ጋብቻ በኋላ ልጆቻቸውን አስተምረው አስመርቀው የልፋታቸውን ውጤት እያስተዋሉ አሁንስ ለራሳችን እናስብ ብለው ባለፈው ቅዳሜ ሥጋወደሙ የተቀበሉትን የቤተክርስቲያናችን አንጋፋ ሽማግሌ የነበሩትንና የሚካኤል ቤተክርስቲያን የቦርድ አባል፡ የሽማግሌ  ኮሚቴ  አባል ሆነው ለዘመናት ያገለገሉን አቶ  ዳኜንና  ባለቤታቸውን እንኳን ደስ አላችሁ ሊል ይወዳል። በሚካኤል ቤተክርስቲያን የፋሲካ ዋዜማ  ቅዳሜ በመሃከላችን ባለመኖራቸው ያዘነው ብዙ እንደ ነበርን ለማወቅም ችለናል። ሐዘኑ የተፈጠረው ለምን ወደ ሌላ  ቤተክርስቲያን  ሄደው ሥጋወደሙ ተቀበሉ በማለት ሳይሆን ይህ እንዲሆን ምን ሚና ተጫወተን ይሆን? የሚለውን ወደኋላ መለስ በማለት የችግሮቹን ሂደት በመቃኘት ጭምር እንደሆነም ለማወቅ ችለናል። ስለሆነም የትም ቤተክርስቲያን ይሁን የት ዋናው የነሱ ምኞት መፈጸሙ ነውና መረዋ  በድጋሜ እንኳን ደስ ያላችሁ እያለ ለአቶ  ዳኘ ቤተሰብ በመላ ስሜቱን  ሲገልጽ ለደረሱበት መንፈሳዊ ድል ደግሞ መንፈሳዊ ቅናት እያደረበት ነው።

ከዚህ በፊት በነበረው እትምታችን ጠቅሰንላችሁ እንደነበረው ባለፈው ሳምንት በነበረው ቀጠሮ የከሳሽና  የተከሳሽ ጠበቆች የመከራረሪያ  ነጥባቸውንና የፍርድ ሃሳባቸውን አጠናቅረው ማቅረባቸውን ልንነግራችሁ እንወዳለን። የከሳሾች ጠበቃ ፋይሉን ያስገባው የስቅለት እለት ዓርብ እንደ ነበረ ስንረዳ ይህ ባጋጣሚ የሆነ  እንጂ ሆን ተብሎ የተደረገ  እንዳልነበረም ለማረጋገጥ ችለናል። ካሁን በኋላ ዳኛው ስሚዝ  ጉዳዩን እልባት ለመስጠት የግድ መወሰን ስላለባቸው በሳምንት ውስጥ ብይን ይሰጣሉ ብለን እንጠብቃለን። መረዋዎችም ውሳኔአቸው እንደደረሰን ለአንባብያን ለማቅረብ አሁንም ቃል እንገባለን።

በሚካኤል ቤተክርስቲያን በአቶ  ጸሐይ ጽድቅ ተገዝቶ ከ 5 ዓመት በላይ ሲያበራ የነበረው የቤተክርስቲያን መብራት እሳቸውን ለመጉዳት በሚል እንዲወርድ መደረጉን ስንሰማ  እጅጉን አዘንን። መብራቱን ለግሰው የነበሩት አቶ ጸሐይ ጽድቅ ቡራኬውን በወቅቱ የተቀበሉ ስለሆነ  ብሎም ለሚካኤል ካበረከቱ በኋላ  የሳቸው ንብረት ሊሆን እንደማይችል እየታወቀ ይህ መደረጉ ደግሞ የሚደንቅ ነው። የአቶ ሙላው ወራሽ ስጦታ የነበረው ቴሌቪዥንም እንደዚሁ ከደጀሰላም መነሳቱን ሰምተናል። የመብራቱን መነሳት ለመመስከር ስንችል የቴሌቪዥኑን መነሳት ግን ከመስማት ባሻገር መደረጉን ለማረጋገጥ ገና እድል እንዳላገኘን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። ያም ሆነ ይህ በቂም ላይ የተመረኮዘ ማናቸውም ውሳኔ ትክክል እንዳልሆነ ከመናገር ግን ወደ  ኋላ አንልም። በዚህ መንገድ ከተቀጠለ  ደግሞ ቦርዱ የማይወዳቸውን ግለሰቦች የመዋጮ ስጦታና የስለት ገንዘብ ከባንክ እያወጣ እንዳይበትነው እንሰጋለን ቢባል ትክክለኛ ጥርጣሬ ይመስለናል። የስደት ሲኖዶስ ለጊዜው ይቆይ የተባለው የምእመናንን ተቃውሞ  በመፍራት እንደሆነም መስማታችንን ስንነግራችሁ የመብት ትግል መቼም ይሁን በማ እየቀጠለ  እንደሚሄድ አሁንም ቃል እንገባላችኋለን። በሚመጣው ሳምንት ቀደም ባለው ጊዜ በወይዘሮ ጥሩዓየርና  በአቶ  ዳግም ተመስርቶ የነበረው ክስ ይግባኝ የቃላት ክርክር እንደሚኖር ባለፈው የጠቀስን በመሆኑ መደጋገም አስፈላጊ አልመሰለንም። ይህ የቤተክርስቲያን የመብት ጥያቄ  ክርክር ከተጀመረ ከሁለት ዓመት በላይ እየሆነ  ነው። ሳምንት ይቆያሉ ብለው ያላሰቡን የቦርድ ዓባላት በጥንካሬአችን መገረማቸውን እራሳቸው እየመሰከሩ ነው። ዛሬ መስራች አባላት በቦርዱ ውስጥ የሉም ዛሬ ትላንት የቦርድ አባላት ሆነው ሲወሰኑ የነበሩት እንደባይተዋር እየተባረሩ ነው ።  እንዳልወሰኑ እየተወሰነባቸው ወዳጅ እንዳልተባሉ ጠላትነታቸው እየተነገራቸው፡ ሕግ አስፈጻሚ እንዳልነበሩ ሕግ እየተፈጸመባቸው። ደንብ እንዳልጠቀሱ ደንብ እየተጠቀሰባቸው ነው።

ብዙዎች ከቤታቸው ገሚሶች ወደሌላ  ቤተክርስቲያን መበተናቸውን በደስታ  የሚመለከተው ቦርድ ጥቂት ሆነን ፈላጭ ቆራጭ ሆነን እንከርማለን ብለው አስበው ከሆነ አሁንም ተሳስተዋል እንላለን። ያላካበቱትን፡ ያልለፉበትን ገንዘብ መበተን፣ ያልሰበሰቡትን ምእመን አበሳጭቶ ማስኮረፍና  ከቤተክርስቲያን ማስቀረት ቀለላል ሊሆን ይችላል መገንባት ግን የዘመናት የሥራ  ውጤት መሆኑን መረዳት ቢችሉ ግን ትልቅነት ይመስለናል። ኩርፊያ  ያለበት ቤተመቅደስ ደግሞ ቁጣን እንጂ ሰላምን ያመጣል ማለት አይቻልም። ምእመናንን  ብቻ  ሳይሆን ካህናትንም የሚከለክል ደግሞ ትልቅ ድክመት ያለው ነው እንላለን።
 እሱ ከመቃብር እንደተነሳ  እኛስ ብለን ብንጠይቅ መልካም ነው።
ቸር ወሬ  ያሰማን

Wednesday, March 23, 2011

የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ

እንደምን ከረማችሁ ምእመናን

የተለየ ነገር ሳይኖር በተደጋጋሚ እናደርገው እንደ ነበረው በተከታታይ ባለመውጣታችን ምን ነካችሁ?  ላላችሁን። መረዋን አትግደሉብን ብላችሁ ለጠየቃችሁን። መረዋ ላይ ካልወጣ እውነት አይደለም ላላችሁና እምነት ለጣላችሁብን ሁሉ ምስጋናችን ወሰን የለውም። ዋሽተን ከምንከበር ይልቅ እውነቱን ተናግረን ብንወገር እንደምንመርጥ መናገር ደግሞ እውነትነቱ አንደማያጠራጥር ምስክሮቻችን እናንተ  ናችሁ።  በመሆኑም እንደ ተለመደው የዛሬን  የፍርድ ቤት   ውሎ እናካፍላችሁ። 

ባለፈው እትምታችን እንደ ነገርናችሁ  የዛሬው ቀጠሮ በ 192 የካውንቲ ችሎት በዳኛ ስሚዝ ፊት የተደረገ ክርከር ነበር። ባለፈው እረዳት ዳኛ የቦርዱ ሹማምንት ከከሳሾች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን የመመለስ ብሎም የቤተክርስቲያኑን ዶሴዎች የማሳየት ግዴታ አለባችሁ ብለው የወሰኑትን ውሳኔ በመቃወም የቦርዶቹ ጠበቃ  ለዋናው ዳኛ ስሚዝ ይግባኝ ማለታቸው ይታወሳል። የዛሬው ቀጠሮ ከመድረሱ በፊት ባለፈው በቦርዱ ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እንዳነሳላቸው የዘገብነው ጉዳይ ነው።

በዛሬው  እለት የተከሳሾች ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ በ march 21st ያስገቡት  ማመልከቻ ለከሳሾች ጠበቃ እንዳልደረሳቸው ለፍርድ  ቤቱ ሲናገሩ ፍርድ ቤቱ ለምን? ብሎ  የተከሳሾችን ጠበቃ  ሲጠይቅ መልሳቸው በfax ልከናል የሚል  ነበር። ፋክስም እንዳልደረሳቸው የተናገሩት የከሳሾች ጠበቃ ባላዩት ማመልከቻ  ላይ ምንም ውሳኔ  ሊሰጥ  እንደማይቻል ተናግረው ዳኛው ተስማምተዋል። ዳኛው የይግባኝ  ሰሚ ፍርድ ቤት በሃይማኖት ጣልቃ  አትግቡ ብሏልና ለምን ጉዳዩን አየዋለሁ? ብለው ለጠየቁት ጥያቄ የተከሳሾች ጠበቃ  እኛም የምንለው እሱን ነው ብለው ሲመልሱ፣ የከሳሾች ጠበቅ ግን የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የወሰነው በእገዳው ላይ እንጂ በክሱ ይዘት ላይ አይደለም በማለት ተከረክረው ለዚህም በውሳኔው መደምደሚያ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን 
ፍሬ ሃሳብ ሳይተችበት ለዳኛ ስሚዝ ማስተላለፉን ጠቅሰዋል። የከሳሾች ጠበቃ  አያይዘውም አሁንም ቢሆን በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ አልስማማም ያ  እንዳለ  ሆኖ ለክቡር ፍርድ ቤቱ ልጠይቅ የምፈልገው እነዚህ የቦርድ አባላት እንደ ፈለጉ ሕግ መቀየር ከቻሉ ነገ  አዲስ ሕግ አውጥተው ንብረቱን ወስደው ቤተክርስቲያኑን ሸጠው ወደ ጃማይካ  ቢሄዱ ምን የሚያግዳቸው ነገር አለ። እዚህ ቤተክርስቲያን አባል መሆን ለምን ያስፈልጋል?  ፈላጭ ቆራጩ ቦርድ እንጂ አባላት ምንም መብት የላቸውም። የከሰሰ  ከአባልነት ይባረራል ካሉ። አባል ለመሆን ማመልከቻ  አስገብቶ  የቦርዱን ፈቃድ መጠየቅ ካለበት ስልጣኑ የምእመናን ሳይሆን የቦርዱ ነው ብለዋል። ስለሆነም ቦርዱ ነገ  ሕጉን  ቀይሮ ምንም ማድረግ ይችላል አባል ምንም መብት የለውም ብለው ለፍርድ ቤቱ አሳስበዋል። በተጨማሪም ይህ ቤተክርስቲያን የ  501 C ፈቃድ ያለው እስከ ሆነ ድረስ  የፌድራልና የስቴት ሕግ የመከተል ግዴታ  አለበት በሃይማኖት ሽፋን ወንጀል መስራት አይችሉም ብለዋል። የተከሰሱት የቦርድ አባላት የራሳቸውን ሕግ እንኳን የማያከብሩ ናቸው ለዚህም የምርጫቸውን ሁኔታ መመልከት ይቻላል በማለት ተከራክረዋል። የተከሳሾች ጠበቃ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ከወሰነው ውጭ ፍርድ ቤቱ ምንም ማድረግ አይችልም ብለው ዛሬውኑ ክሱ ተሰርዞልን እንሰናበት ብለው ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ነበር።

በመጨረሻም ዳኛው ሁለቱ ጠበቆች ተስማምተው የመከራከሪያና  የፍርድ ሃሳባቸውን ከዚህ በፊት ከነበሩ ተመሳሳይ  የተለያዩ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች ጋር እንዲያቀርቡላቸው ሁለት ሳምንት ሲሰጡ ስምምነቱን አስመልክቶ የተከሳሽ ጠበቃ ጽፈውና ፈርመው ለከሳች ጠበቃ እንዲያሳልፉ የከሳሽ ጠበቃ ደግሞ ፈርመው ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀረቡ ነግረዋቸዋል።

ዳኛው የሁለቱን መከራከሪያ ነጥብና የፍርድ ሃሳብ ካዩ በኋላ ማስረጃ መስማት እንደሚያስፈልግም ሆነ ክርክሩን ለመክፈት ወይንም ለመዝጋት ውሳኔ  ለመስጠት ለ APRIL 15 ቀጠሮ  ሰጥተው የእለቱ ችሎት  ተፈጽሟል።

በተጨማሪም በወይዘሮ ጥሩአየር እና  በአቶ  ዳግም ከሳሽነት ተመስርቶ በዳኛ  እስሚዝ የቦርዱ አባላት ካለ አባላት ፈቃድ ሕጉን መቀየር ይችላሉ ብለው የበየኑት ብያኔ  የሚታወስ ነው። ውሳኔውን በመቃወም ከሳሾቹ ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ  ማለታቸው ይታወሳል። ስለሆነም ጉዳዩን በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እያለ ከሳሾች ፍርድ ቤቱ ያለውን መረጃ ተመልክቶ  ውሳኔ  ይስጠን ቢሉም የቦርዱ ጠበቆች የለም የቃል ክርክር እንፈልጋለን በማለታቸው የቃል ክርክሩን ለማዳመጥ ጉዳዩ ለመጭው MAY 4, 2011 
ሰዓት 1:00PM  
ላይ መቀጠሩን ልንነግራችሁ እንወዳለን።
ቦታው 600 COMMERCE # 200
COURT OF APILE
FIFTH DISTRICT OF TEXAS


ማንኛውም የቤተክርስቲያን ምእመን በፍርድ ቤት በመገኘት ክርክሩን ማዳመጥ  እንደሚችል ስንነግራችሁ በደሰታ  ነው።
የቦርድ አባላት የማያልቅ ገንዘብ ስላላቸው ብዙ የማቆያ ዘዴዎችን እንደሚጠቀሙ ትላንት ፍርድ ቤት የተነገረ ሲሆን፣ መብታቸው የተደፈረው ምእመናን ደግሞ  ፈጣሪንና ደጋፊዎቻቸውን ይዘው መታገላቸውን እንደማያቆሙ ከሂደቱ መገንዘብ ይቻላል።

መረዋ ለምእመናን የሚጠይቀው ነገር ቢኖር መብት የሌለው አባልነት ምንድነው? የሚል ይሆናል።

መረዋም የዛሬውን ዘገባ  በዚሁ ያበቃል።

Friday, March 4, 2011

ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጠ

ውድ አንባብያን እንደምን ከረማችሁ

ባለፈው የቦርድ አባላት ግለሰቦችን ከቤተክርስቲያን እንዳያባርሩ ዶሴዎችን እንዳያጠፉ ተጥሎባቸው የነበረውን እገዳ በመቃወም ይግባኝ  ማለታቸው የሚታወስ ነው። በትላንትናው እለት ጉዳዩን የሰማው ፍርድ ቤት ዳኛው አስቀምጦት የነበረውን እገዳ  በማንሳት ክርክሩን ወደሚያዳምጡት ዳኛ መልሶ  መላኩን ለመረዳት ችለናል።   

በዳኞቹ አባባል የመታደደሪያ  ደንቡ ማንንም ሰው ቤተክርስቲያን እንዳይመጣ ቁርባን እንዳይቀበል ቦርዱ መከልከል አይችልም የሚለውን ይህ በውሰጥ ሊፈታ የሚችል በመሆኑ ፍርድ ቤት ማዘዝ አይችልም ብለው  ሲወስኑ የጉዳዩን ጭብጥ ክርክር ግን አናይም በማለት ውሳኔው እገዳውን በተመለከት ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰው ሁኔታውን እንዲያዩትና ክርክሩን እንዲሰሙ ለዳኛ ስሚዝ ዶሴውን መልሰው መላካቸውን ጠቅሰዋል።

ገንዘብ እንዳያባክኑ  ዶሴዎችን እንዳያጠፉ ተጥሎ  የነበረውን እገዳ ዳኞቹ ቦርዱ ገንዘብ ለማባከኑና  ዶሴዎችን ለማጥፋቱ የቀረበ  መረጃ ባለመኖሩ እገዳውን አንስተንዋል ሲሉ  ወደፊት ግን ይህ ለመደረጉ መረጃ  መስማት እንዲችሉ ለዳኛ ስሚዝ ጉዳዩን ክፍት በማድረግ ትተውታል።

ይህንን  አስመልክቶ  ሊቀርብ የሚችል ብዙ መረጃ  መኖሩን ስለምናውቅ የሚያስጨንቅ አለመሆኑን ለአንባብያን መናገር እንወዳለን። እስካሁን ምንም ክርክር ሳይጀመር ምስክር መስማት ሳይቻል  በአሰራር ብቻ  እየተወሰነ  ያለውን ጉዳይ አለቀ የሚሉ ካሉ ትልቅ ስህተተ  እየተሳሳቱ እንደሆነም መናገር እውነት ይሆናል።

የይግባኝ ፍርድ ቤቱ በእገዳው ላይ ብቻ ውሳኔ መስጠታቸውን ተናግረው ክሱን አስመልክቶ ምንም ውሳኔ አለመስጠታቸውን አስፍረዋል። ይህንን  ማድረግ የሚችሉት ዳኛ ስሚዝ እንደሆኑም ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።  ለዚህም ነው ዶሴው ወደሳቸው ፍርድ ቤቱ የተመለሰው።

በ3/23/2011 9:15 AM

በዳኛ ስሚዝ ችሎት እንድንገናኝ ጥሪ እያቀረብን  ለዛሬው በዚሁ እንሰናበታችኋለን።

ክርክሩ ተጀመረ  እንጂ አላለቀም። 

Tuesday, February 22, 2011

የፍርድ ቤቱ ቀጠሮ

ውድ አንባብያን እንዴት ከረማች? እኛ አሁንም የጀመርነውን ለመጨረስ ከመታገል ወደ ኋላ አላልንም። የተፈጠረ ብዙ ነገር ብንታዘብም የፍርድ ቤት ዜና ከማግኘታችን በፊት ለእትምት ላለመውጣት ወስነን ነበርና ይህንኑ ስንጠብቅ ሰነበትን። እነሆኝ በዛሬው እለት የደረሰን ዜና እንደሚጠቁመው ባለፈው ተላልፎ  የነበረው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለ March 23, 2011 9:30 AM መቀጠሩንና ሁላችሁም መጋበዛችሁን መረዋ ማሳሰብ ይወዳል። ስለሆነም በተባለው ቀን ፍርድ ቤት ለመገኘት ካሁኑ የስራ እቅዳችሁን  እንድታስተካክሉ በድጋሜ  እናሳስባችኋለን። 

በተጨማሪ ከማንም ያልወገነ ገለልተኛ የተባለው ቤተክርስቲያናችን የአመራር አባላትና ካህናት ባለፈው ሳምንት ወደ ሂውስተን በመጓዝ ከስደት ሲኖዶስ አባቶች ጋር መገናኘታቸውን የደረሰን ዜና  ይጠቁማል። በወቅቱ በስፍራው  ተገኝተው የነበሩት አባ መልከጸዴቅ የዳላስ ሚካኤልን ወደ ስደት ሲኖዶስ መጥቶ  የቤተክርስቲያኑ አመራሮ ች በመሃከል መገኘታቸውን ከማብሰራቸውም በላይ ከዚህ በፊትም 7 ዲያቆናትን የስደቱ ሲኖዶስ ድቁና  መስጠቱን አውስተዋል። በመቀጠልም ከኮሎምቦስ የስደት ሲኖዶሱ ካህን ወደ  ዳላስ ተልከው በስራ  ላይ እንደሆኑም መጠቆማቸውን የደረሰን ዜና  ያረጋግጣል። የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ዘማርያንም የቤተክርስቲያኑን አልባሰ መዘምራን አጥልቀው ይዘምሩ እንደነበርም ለማረጋገጥ  ችለናል።

ገለልተኛ የተባለው ይህ ቤተክርስቲያናችን ማንንም ሲኖዶስ አንደግፍም ሲባል ቆይቶ ዛሬ የቦርድ አባላት በእንግድነት ከነባለቦቶቻቸው መገኘት ብቻ  አይደለም መዘመር ከቻሉ ገለልታኛነቱ እምኑ ላይ እንደሆነ እራሳችሁ እንድትጠይቁ ለናንተ  እያቀረብን መረዋ  ከዓመት በፊት ያነሳው የቦርድ አባላት እቅድ እየተፈጸመ  መሆኑን ከመታዘብ በስተቀር አልተደነቅንም። ትላንትናም ሆነ  ዛሬ ትግሉ ቤተክርስቲያኑን ተቆጣጥሮ የፖለቲካ ዓላማ  መጠቀሚያ ለማድረግ እንደሆነ የምናውቀው ነገር ፣ የተናገርነው ነገር ነበር። ትላንት ውሸት ተብለን ነበር ዛሬ  ምን እንባል ይሆን?

የወር ሰው ይበለን?

የመብት ትግላችን ይቀጥላል።

Wednesday, February 9, 2011

ዘግይቶ የደረሰን

እንዴት ሰነበታችሁ ውድ አንባብያን

ባለፈው እትምታችን እንደነገርናችሁ ተከሳሽ የሆኑት የቤተክርስቲያኑ የቦርድ ባለስልጣናት ቀደም ባለው ዳኛ ተወስኖ የነበረውን

በመቅደስ ውስጥ ፖሊስ አታስገቡ
አማንያንን አታባሩ
መዛግብቶችንና የኮሚፒውተር መረጃዎችን እንዳታጠፉ ብሎ የወሰነባቸውን በመቃወም ይግባኝ  ማለታቸው የሚታወስ ነው። በመሆኑም በ2 / 7/ 2011 ያስቻለው የይግባኝ  ሰሚ ፍርድ ቤት በከሳሽና  በተከሳሾች ጠበቆች የቀረበውን የቃል ክርክር አዳምጠዋል። በወቅቱ የተሰየሙት 3 ዳኞችም ለሁለቱም ጠበቆች  እንዲብራራላቸው የፈለጉትን ጥያቄዎችም ጠይቀው መልሱን  አዳምጣዋል።

ከሳሾችን አናውቃቸውም ያሉት የተከሳሾች ጠበቃ ከሳሾች ማክዶናልድ  ምግብ ቤት ሃምበርገር ተመላልሰው በመበላታቸው የማክዶናል የቦርድ አሰራር አላማረንምና የመቀየር መብት አለን እንደሚል ግለሰብ ናቸው ብለዋል። ስለሆነም እኛም ያልመሰለንን  የማስዋጣት የማባረር መብታችን መጠበቅ አለበት ምክንያቱም ቤተክርስቲያን በመሆናችን  መንግስት ጣልቃ  ሊገባብን አይችልም መንግስት መግባት የሚችለው የንብረት ይገባኛል ጥያቄ ይዘው ቢቀርቡ ነበር  ማለታቸውን ለመረዳት ችለናል።
የከሳሾች ጠበቃ በበኩላቸው እነዚህ ተመራጮች ያላግባብ የተመረጡ ከመሆናቸውም በላይ ጥያቄ ተጠየቅን ብለው ሴትና ሕጻናት በተሰበሰቡበት ወገን ፖሊስ እያስገቡ ያሳሰሩ ብሎም መብታቸውን በመጠቀም አባላትን ለማባረር የተነሱ መሆ ናቸውን አውስተው ጉዳዩ የእምነት ሳይሆን የመብት መገፈፍ መሆኑን አስረድተዋል። በ2/10/2011 ዳኛ ስሚዝ በይግባኝ ሰሚነት የሚያዩት ለውሳኔ  የቀረበ  መዝገብ እንዲያሳዩ  በበታች ዳኛ  የተወሰነውን አሻፈረን በማለት አሁንም የቦርዶቹ ጠበቃ ያቀረበው ስለለ የእሱንም ውጤት የይግባኝ  ሰሚው ፍርድ ቤት መጠበቅ ይኖ ርበታል ብለዋል።
ፍርድ ቤቱ የቀኑን የጠበቆች ገላጻ አዳምጦ የእለቱ ሸንጎ ፍጻሜ  ሆኖ ተበትኗል።




ዘግይቶ  የደረሰን ዜና በነገው እለት 2/10/2011 ተቀጥሮ  የነበረው ይህ ቀጠሮ በከሳሾች ጠበቃና በዳኛው የፕሮግራም መጋጨት መተላለፉን ለመረዳት ችለናል።  የቀጠሮውን ቀን እንደደረሰን ለአንባብያን እናስታውቃለን።

የከርሞ  ሰው ይበለን። 

 

Monday, January 24, 2011

በትላንትናው ቀን የተጠራው ስብሰባ በሙሉ መግባባት ተፈጸመ።

ባለፈው እንደ ነገርናችሁ በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰላም መፍተሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በትላንትናው እለት ጠርቶት የነበረው ስብሰባ በመግባባትና በሙሉ ስምምነት መገባደዱን የደረሰን ዜና አስታውቋል። በወቅቱ በተደረገው ስብሰባ  የተገኙት እንግዶች ከምሳ ግብዣው በኋላ ሰፊ ውይይት እንዳደረጉ ሲነገር፣ በወቅቱ የአራቱም የኮሚቴው ተወካዮች በየተራ  ለተሰብሳቢው ስለተደረገው ያለፈ የኮሚቴ የስራ ክንውን መግለጫ መሰጠታቸውንም ለመረዳት ችለናል። በዜናችን መሰረት የመንፈሳዊ ኮሚቴ አባላት ከቤተክርስቲያናችን እየተገፉ የሚገኙትን አባላት መንፈሳዊ ጽናታቸን ለማጠናከር በዓርብ ምሽት የሚደረጉትን ትምህርቶች በየሰዎስት ወሩ የተዘጋጁትን የመንፈሳዊ ጉባኤዎች በሚያስደንቅ መልኩ ማካሄድ እንደቻሉ ለተሰብሳቢው ተናግረዋል። ይህንንም ማድረግ የተቻለው ዓርብ ማታ በሚደረገው መንፈሳዊ ትምህርት ተካፋዮች ጉልበትና ከኪስ በተዋጣ ወጭ እንደ ሆነም የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ተናግረዋል። በወቅቱ ኮሚቴውን በማሰባሰብና በማስተማር በመምራት ያገለገሉት ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በሌሊት በፖሊስ ተከበው የመሰናበቻ ወረቀቱን እንዲፈርሙ የተገደዱትና፡ ከቤተክርስቲያኑ ቦርድ ለኢሚግሬሽን በተጻፈ  ደብዳቤ  የኢምግሬሽናቸው ሁኔታ እንዲታገድና ከአገር ከነቤተሰባቸው እንዲባረሩ የተጠየቀባቸው መላከ ሳህል አወቀ ሲደልል እንደ ነበሩ ለተሰብሳቢዎቹ ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት መላከ ሳህል አወቀ አትላንታ የሚገኝ ደብር ቀጥሯቸው ወደ አትላንታ መሄዳቸውም ለተሰብሳቢው ተገልጿል። ስለሆነም ቀደም ብለው ወደ አዲሱ ሥራቸው የተዛወሩት መላከ ሳህል አወቀ የዳላስን ምእመናንን ለመጨረሻ ጊዜ ለመሰናበት በፊታችን ዓርብ 1/28/2011ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ባሻገር በሚገኘው የኬንያውያን ቤተክርስቲያን አዳራሽ ውስጥ እንደሚገኙ ሲነገር፡ ማንኛውም ምእመን ቤተሰባቸውንና እሳቸውን ለመሰናበት በዚሁ እለት እንዲገኝ ኮሚቴው ለሁሉም የዳላስ ምእመን ጥሪውን አቅርቧል። በዚህ አጋጣሚ መረዋ ለኝህ ቆራጥ ካህን ያለውን አድናቆትና ያላቸውን ቆራጥነት እያደነቀ፤ መጭው የሥራ ቦታቸው የተቃና እንዲሆን ምኞቱን ይገልጻል። መላከ ሳህል አወቀ እንደ አባት የሚርቁብን ቢሆንም ምሳሌነታቸው ግን ከልባችን ለዘላለም ይኖራል። የመንፈስ አባቶ ችን ስናነሳም እንደ ምሳሌ የምንጠቅሳቸው ይሆናሉ። ለቤተሰቦቻቸው ያለንንም አድናቆት ስንገልጽ በደስታ ነው። በተለይ ለውድ ባለቤታቸው መረዋ ያለውን አክብሮትና የመንፈሰ ጠንካራነት አርአያ መሆናቸውን መመልከቱን ሲጠቅስ በኩራት ነው።

የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ተዋካይ ደግሞ በተለያየ መንገድ ለአባላት የተላኩ መልእክቶች እንዲዳረሱ ማድረጉን በመናገር የኮሚቴው ልሳን የሆነው WWW.MELEKET4U.BLOGSPOT.COM ከመቼውም በበለጠ ከዚህ በፊት የተደረጉትንም ሆነ ወደፊት የሚደረጉትን ለአባላት ለማስነበብ በገጹ ላይ እንደሚለጥፍ ቃል ከመግባቱ ባሻገር ከብሎግ አልፎ WEB PAGE ወደፊት ለማውጣት እቅድ ላይ መሆኑን ተናግሯል።

የአባላት ኮሚቴ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት የደጋፊዎቻችን ቁጥር ከ200በላይ እንደሆነ  በመጠቆም አሁንም ከሌላው ወገን የሚሰነዘረውን የውሸት ወሬና ስድብ በተቋቋምን ቁጥር ካስተዋልኩት ደጋፊዎቻችን እየበዙ መሄዱን አውቃለሁ በማለት ጠቁመዋል። ለዚህም ዋናው መሳሪያችን ሲሳደቡ አለመሳደባችን፣ አለመዋሸታችን፣ ስንጀምር ያነሳነው የመብት ጥያቄ አሁንም በእንጥልጥል መሆኑና አለመዋዠቃችን  እንደሆነ ለተሰብሳቢው ተናግረዋል።

የሕግ ኮሚቴ ተወካይ በበኩላቸው ቤተክርስቲያን እንዴት ይከሰሳል የሚሉት ግለሰቦች ለምን የአባላት መብት ይደፈራል? ሲሉ ያለመሰማታቸውን ተናግረው፡ ለመብት እንቆማለን ያለ ማንም ግለሰብ መብቱ ሲጣስ ያለው አማራጭ በጉልበት መጠቀም ሳይሆን በሕግ መከላከል ብቻ ነው፥ ብለው የሚገርመው ቤተክርስቲያንችን ተከሰሰ  ያሉት የቦርድ  አባላት ባዲስ መልክ እንደ መከላከያ ያመጡት ነጥብ ቢኖር በቦርድ አባልነታችን በግል መከሰስ የለብንም ቢፈልጉ ከሳሾች ቤተክርስቲያኑን ይክሰሱ ብለው ፍርድ ቤቱን መጠየቃቸው እንዳስገረማቸው ተናግረዋል። ሆኖም ከትላንትናው በተሻለ ሁኔታ ጉዳዩ እየተፋጠነ መሆኑን አብራርተው ስለፍርድ ቤቱ ሁኔታ አጭር ገለጻ አድርገዋል፡፡

በገለጻቸው መሰረት ከዚህ በፊት ዳኛው  ምእመንን ከቤተክርስቲያን አትከልከሉ። ፖሊስ ወደ መቅደስ አታስገቡ። ዶሴዎችና ማናቸውንም መረጃዎች አታጥፉ ብለው ያዘዙትን  ትእዛዝ አንስማማም በማለትምእመንን የማባረር መብት አለን፣ ፖሊስ በመቅደስ ውስጥ  ማስገባት አለብን፣ ዶሴዎችንና ማናቸውንም መረጃዎች እንድናጠፋ ይፈቀድልን፣ ብለው ይግባኝ ባሉት መሰረት በ 2/7/2011 3:00PM ላይ በ ይግባኝ  ሰሚ ፍርድ ቤት 3 ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የከሳሽና የተከሳሽ ጠበቆች 30 ፤ 30 ደቂቃ ተሰጥቷቸው ክርክር ስለሚያደርጉ ማንኛውም ሰው፥
600 COMMERCE DALLAS COUNTY COURT BUILDING 2nd FLOOR በመገኘት ማዳመጥ  እንደሚችል ተናግረዋል።

በተጨማሪ በ 2/10/2011 192court በመገኘት ባለፈው እረዳት ዳኛ በቦርዱ ላይ የፈረዱባቸውን የከሳሾችን ጥያቄዎች እንዲመልሱ የታዘዙትን ቦርዱ አሻፈረኝ ብሎ  ይግባኝ ባለው መሰረት ዳኛ ስሚዝ ፊት ቀርበው የሁለቱም ጠበቆች እንደሚከራከሩ ስንነግራችሁ አሁንም የምትችሉ ሁሉ ከላይ ባለው አድራሻ በ 9:00 AM በመገኘት እንድታዳምጡ ብለው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። አያይዘውም ዳኛው በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰጡት ብይን ይግባኝ የሌለውና የመጨረሻ  መሆኑንም ለተሰብሳቢዎቹ ተናግረዋል።

በመደምደሚያው የስብሰባው ሰብሳቢ፣ ሁሉም ላደረጉት እርዳታ ከልብ መነካታቸውን ተናግረው ለመብት አለመቆም በራሱ ድክመት መሆኑን  ተናግረዋል። በተለያየ  መንገድ እርዳታ የሚያደርጉትን ግለሰቦች አመስግነው አሁንም እርዳታው እንዲቀጥል አሳስበዋል።

መረዋ ሁላችሁንም በተባሉት የፍርድ ቤት ቀጠሮዎች እንድትገኙ  ጥሪውን እያስተላለፈ ለዛሬው በዚሁ እንሰናበታችኋለን።

የሳምንት ሰው ይበለን።

Friday, January 14, 2011

የተናገርነው እየተፈጸመ በመሆኑ ትንቢተኞች ነን አላልንም።

ሰላምና  ፍቅር ለሁላችሁ ይሁን አንባብያን እንዴት ከረማችሁ።

አንድ ነገር ዛሬ ደጋግመን ደጋግመን መናገር የምንወደው ነገር አለ። መረዋ እንደ ጦማር መውጣት ከጀመረበት ሰዓት ጊዜ  ጀምሮ የዋሸነውና አንባቢዎቻችንን ያደናገርንበት ጊዜ የለም። ከጅምሩ ስንለው የነበረው ነገር በሙሉ እየተፈጸመ ስናይ ደግሞ ትንቢተኞች ነን ብለን አልተመጻደቅንም። እትምት ላይ የምናመጣውን ማናቸውንም ነገር ግራና ቀኝ ሳናገናዝብ ጽፈን አናውቅም። አጀማመራችን ለጉራ ሳይሆን ባለፈው እንዳልነው መረዋ ሞተ የምንለው ውሸት ይዞ የተነሳ እለት ነው ብለን ስለምናምን መጠንቀቃችንን ለናንተ ለማረጋገጥ ነው። ዛሬ የተለየ ዜና ይዘንላችሁ አልቀረብንም። ስትሰሙት የከረማችሁትን እንጂ። ባለፈው ሳምንት ከእትምት እንድንቆጠብ በተጠየቅነው መሰረት ቃላችንን ፈጽመናል። ያን ስናደርግ ደግሞ ለውጥ ይመጣል ብለን አስበን እንዳልነበረ ልታውቁልን ይገባል። ያ የገባንው ቃለ  ቀጠሮ  ሲያከትም እነሆ እትምታችንን ጀምረናል።

ሰሞኑን ምርጫ ለማካሄድ የቦርድ ተመራጮች ደፋ ቀና እያሉ ነው። የፖለቲካ ድርጅቶችም ይወክሉናል የሚሏቸውን ለምርጫ አሰልፈዋል። እነማን እንደሆኑ ደግሞ ያነበባችሁትና የሰማችሁት ጉዳይ ነው።አዲሶች ተመራጮች ሆነው የቀረቡት ግለሰቦች ትልቅ ሹመት የሚያገኙ መስሏቸው ተነስተው ከሆነ ትልቅ ስህተት እየተሳሳቱ ነው። እየነደደ  ባለ ቤት ነዳጅ ይዞ  መግባት እሳቱን ማፋጠን እንጂ የሚያጠፋው አይሆንም። መቃጠሉ ይሻላል የሚሉ ከሆነ ሹመት ያዳብር እንላቸዋለን።

ምርጫውን ለማስቆም ከ 60 በላይ የሚሆኑ የቤተክርስቲያኑ አባላት በፊርማ ቦርዱን እንደጠየቁም ሰምተናል። ምላሹ ምን ይሆን? ብለው የጠበቁ ካሉ አናውቅም እንጂ እኛ እንቢ እንደሚሏቸው እርግጠኞች ነበርን። እንዳልነውም የቦርዱ አባላት የተሰጣቸውን ፊርማ ወርውረው ምክንያት እየፈጠሩ ምርጫውን ማስቆም የሚችል ምንም ሃይል አይኖርም ማለታቸውን ሰምተናል። የፈራሚዎቹ አባላት ሌላ የምንጠይቀው አለን እኛ በእግዚአብሄር ቤት ተስፋ አንቆርጥም ማለታቸውንም ከተጨባጭ ምንጮች የደረሰን ዜና አብስሮናል። ሚካኤል ይርዳቸው እንላለን። እኛ ግን መብትን ማስከበር የሚቻለው በሕግ ብቻ  እንደሆነ  ከተቀበልን ቆይተናልና ከሕግ ወጪ ለውጥ እንደማይመጣ ከተገነዘብን ውሎ  አደረ። ለዚህም ነው መረዋ ክስ የመሰረቱት ግለሰቦች የመክሰስ ሱስ ይዞአቸው ሳይሆን መፈናፈኛና አማራጭ አጥተው ነው በማለት ከሳሶችን ደግፎ  የተነሳው።

ከሳሾች አባል አይደሉም ያሉ የቦርድ ተመራጮች አባል ያልሆኑትን ለቦርድ እጩ አድርገው እያቀረቡ ነው።
የአባላትን ቁጥር ለማብዛት ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አባላትን እየተዋሱ እንደሆነም እየተመለከትን ነው።
የጊዮርጊስ አስመራጭ ኮሚቴ አባል የሚካኤል እጩ የሆኑት ባለቤታቸው ጊዮርጊስ ስላልተመረጡ ተናደው ነው ሲባል አልሳቅንም ቀልዳችሁን ነው አልን እንጂ።  
በኮሚቴ አባልነት ያላገለገሉ ተመራጭ ሆነው ሲቀርቡ ምነው?  አላልንም የምናውቀውን አጠናከረልን እንጂ። የራሳችን መተዳደሪያ ሕግ ነው የሚሉት ሊሰራ የሚችለው እነሱን ከጠቀመ  ብቻ  እንደሆነ ካወቅን ውሎ  አደረ። ካልሆነ ይሻራል። 
ሚካኤል ፖሊስ ቀጥሮ የቦርድ አባላት እንዳይሳሳቱ ሃጥያት እንዳይሰሩ ለማድረጉ ደግሞ ባለፈው የተፈጠረውን  የቦረዱን አባል የሴትኛ አዳሪ አፈላማ እንደ ማስረጃ ያወሱናል ይህ ደግሞ  ቤት ሊሰብሩ የሚሄዱ ወይም ኪስ ለማውለቅ የሚሄዱ ሌቦች ለጊዮርጊስ ይሳላሉ የሚለውን አባባል ያስታውሰናል። 

ትላንት አባል ካልሆናችሁ ብለው ይናገሩ የነበሩትን ግለሰቦች ክስ ከመሰረቱት ውስጥ   አንዱ ሲመልሱ "አንድ ሰው አባል የሚሆነው እኮ መብት ካለው ብቻ ነው። እኛ ከቤተክርስቲያን በፖሊስ የተባረርነው አባል ሆነን እኮ ነው።
አትናገሩም የተባልነው አባል ሆነን ነው።
ስብሰባ  አይጠራላችሁም የተባልነው 126  አባላትን አስፈርመን  እኮ  ነው"
ብለው ሲናገሩ አድምጠን ነበር። አሁንም ያ ድርጊት ሲደገም እያስተዋልን ነው።

ሽምግሌ  የማይቀበሉ
የአባላትን ፊርማ አሽቀንጥረው የሚጥሉ
ለቤተክርስቲያኑ የምናስበው እኛ እንጂ ብዙሃን አይደሉም የሚሉ
እነሱ ከስደት ሲኖዶስ ጋር እየተነጋገሩ ከሳሾች ቤተክርስቲያናችሁን ነጥቀው ለኢትዮጵያ ሲኖዶስ ሊሰጡባችሁ ነው እያሉ የሚቀጥፉ
የነሱን የፖለቲካ ሽኩቻ ይዘው መምጣታቸውን ደብቀው የሌለ ኢሕአደግ እየመጣባችሁ ነው ብለው የሚያስፈራሩ
በፖለቲካ ዓለም ማንም ፓርቲ መመሪያና መርህ እንዳለው ሳይናገሩ ከሳሾች 52 ነጥብ አስፈጻሚዎች ናቸው ብለው ሲወነጅሉ ቅር የማይላቸው።
ኢትዮጵያ ያለው መንግሥት ገንዘብ አጥቶ የቤተክርስትያኑን (የከፈሉበት ይመስል) $400,000 ለመውሰድ እየሸረበ  ነው ብለው ሊያሳምኑ የተነሱ
ትላንት ያወድሷቸው የነበሩትን ግለሰቦች አሁንስ አበዛችሁት ሲሏቸው 360 ዲግሪ ተሽከርክረው ዘራቸውን እየቆጠሩ ሲሳደቡ ቅር የማይላቸው የቦርድ አባላትና ደጋፊዎቻቸው
ማ ከማ ጋር አንሶላ  ተጋፈፈ  ብለው ሲያወሩን የነበሩ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው
የነፍስ ግድያ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችን እናውቃለን በማለት ስም እየጠቀሱ የመያውቁትን ፈጥረው ያልተባለ  ቀጥለው ያሰራጩ
ያልደገፏቸውን ግለሰቦች ትዳራቸው እንዲፈርስ ሚስቶቻቸውንና ባሎቻቸውን እርጃ ውሰዱ (ተለያዩ)  ያሉ ግለሰቦች
ዛሬ  ልብ ገዝተው ፈሪሃ  እግዚአብሄር አድሮባቸው ካለ  ፍርድ ቤት ትእዛዝ ምርጫ አስቁመው የሕዝቡን ቃል ያከብራሉ ማለት ለኛ አይዋጥልንም።

ሆኖም ፊርማ ሲያስፈርሙ የከረሙት ወንድሞችና እህቶች አሁንም ቦርዱን በመጠየቅ በማነጋገር መስመር ማስያዝ ይቻላል ማለታቸውን ስንሰማ በተአምር እናምናለንና ይሳካላችሁ ብለናል።

ውድ አንባብያን በሚመጣው ሳምንት 1/23/11 እሁድ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ሙሉ ገለጻ እንደሚደረግ የገለጹልን የመብት አስከባሪ ቡድኖች ሁላችሁም እንድትገኙ በድጋሜ ጥሪ ያደርጋሉ።

ሚካኤል ፈቃዱ ከሆነ ምናልባት የምስራች ይኖረን ይሆናል።

የሳምንት ይበለን

Wednesday, January 12, 2011

የስብሰባ ጥሪ እንደገና

ጠቅላላ የምእመናን ስብሰባ ጥሪ”



ተፈጥሮ በነበረው ሐዘን ምክንያት የተሰረዘው የምእመናን ስብሰባ ጥሪ እንደገና እየተጠራ ነው።

ሁላችሁም ስብሰባውን ለመካፈል ተዘጋጁ!!!

 
ቀኑ፡- ጥር ፲፭ ቀን ፳፻፫ እሑድ


January 23, 2011, Sunday


ሰዓት፡-1፡00 P.M    

ምሳ አለ።


ቦታው፡- Dream Club

7035 Greenville Ave #E

Dallas, TX 75231-5109

በበለጠ ለመረዳት

በ(214) 368-4981

ወይንም

(469) 879-8650 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።


የተባለውን ለመስማት ብቻ  ሳይሆን የራሳችሁን ሃሳብ

ለማካፈልም ወደ ስብሰባው መምጣት የግድ ነው።

ላልሰሙ ሁሉ ተናገሩ።

እንደገና  ተላልፎ  የነበረው ስብሰባ
 በድጋሜ ተጠራ።

የመልአኩ እርዳታ ይታከልበት። በችግር ምክንያት መምጣት የማትችሉ ብትኖሩ በጸሎታችሁ አስቡን።

ከየቅዱስ ሚካኤል የሰላምና የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የቀረበ።





Wednesday, January 5, 2011

ዝም ያለ ሰው እያዳመጠ እንጂ መናገር አቅቶት አይደለም። ቁጥር ፶፭

ሰሞኑን ከአንባብያን ለደረሱንን የድጋፍ መግለጫዎች ሁሉ እያመሰገንን ለተሰደቡት ብርታትን፣ ለተወነጀሉት ጽናትን፣ ይስጣቸው እንላለን። ብዙዎቻችሁ በመረዋ ላይ መግለጫ ለመለጠፍ ጠይቃችሁን ነበር። ነገር ግን የመረዋ አነሳስም ሆነ ጉዞ የፖለቲካ ስንክሳር ለማራመድ ባለመሆኑና የአንባቢዎቻችንን ፍላጎትም በመገንዘብ ከአጀማመሩ ያ እንዳይሆን አቋም የወሰድንበት ጉዳይ ስለሆነ ጥያቄአችሁን ባለመቀበላችን ይቅርታ  እንጠይቃለን። ያም ቢሆን ለተሰደቡ ደጋፊዎቻችን ያለንን አድናቆት እየገለጽን የተሰደባችሁትና በሃሰት የተወነጀላችሁት እውነት በመናገራችሁ፤ ለመብት በመቆ ማችሁ በመሆኑ ልትኮሩ እንጂ ልታፍሩ አይገባችሁም እንላለን። እውነት የሆነውን ሁሉ ብንጽፍ ደግሞ በሃሰት  የተሰለፉትን ከስራ ማፈናቀል ይሆናል። ለመብት የቆሙ ደግሞ ጠንካሮች እንደሆኑ ማስረጃ የሚያስፈልግ አይሆንም። በየቀኑ የምታሳዩን እውነታ ነውና። እናንተን እያየን በየቀኑ እየተማርን ነው። መረዋ እውነትን ይዘው ከቆሙት ጎን በመቆሙ አሁንም ደስተኛ ነው። እውነት ለማሸነፉ ደግሞ ጥርጥር የለንም።

ዛሬ ከመረዋ  ከሰነበቱ እትሞች አለፍ አለፍ እያልን ልናስነብባችሁ እንወዳለን።ያለፈውን በማየት መጭውን ዳግም እንድናቃኝ ይረዳናልና።


ከመረዋ  ቁጥር ፩
11/26/09

"አሁን ለምን ሽማግሌዎች ሊያስታርቁ ተነሱ" ብሎ መተቸትና መሰናክል ለመፍጠር መነሳት ግን ሌላ ስህተት ነው ብለን ደግሞ እናምናለን። በፍርድ ቤት ትእዛዝ ችግራችን ይፈታል ብሎ የሚያምን ካለ የዋህ ነው ብሎ መናገር ማስፈራት የለበትም። ፍርድ ቤት በሚሰጠው ብያኔ ፍቅር አይመጣም አንድነት አይፈጠርም። ይህ ሊሆን የሚችለው የተለያየ ሃሳብ ይዞ የሚከራከረው ቡድን ተቀምጦ መነጋገር ሲችል ብቻ ነው። ክስ የመሰረቱትን ለምን ክስ መሰረቱ ብሎ መኮነን ደግሞ ሲደረግ የነበረውን መካድ ይህንን ባያደርጉ ኖሮ ዛሬ እንደዚህ ለመናገር የማንችልበት ሁኔታ ላይ እንሆን እንደነበር አለመቀበል ይሆናል። የቤተክርስቲያን ገንዘብ ስላለ ከሳሾቹን ገንዘባቸውን አስጨርሰን እንዲሸነፉ እናደርጋለን የሚሉት የቤተክርስቲያኑ ተመራጮች ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር የተመኩበት ገንዘብ ከምእመናን የተዋጣ መሆኑን ነው። ምእመኑ ካልደገፈ የገንዘቡ ቌት እንደሚሟጠጥ ከሳሾችንም ከአሁኑ በበለጠ እየደጎሙ እየደገፉ እንዲቀጥሉ ሊያበረታቱ እንደሚችሉ ማሰብም የተገባ ነው። ከሳሶችም ሆኑ የቤተክርስቲያኑ ተመራጮች ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር ያለ ምእመን ድጋፍ የትም ሊሄዱ እንደማይሄችሉ ነው። በተናጠል ቤተክርስቲያን አይገነባምና። ተሰዳደብን፡ ተካሰስን፡ ተወነጃጅለን አሁን ደግሞ ወደ አንድነት ለመምጣት ምን አስተዋጽኦ እናድርግ ብሎ መነሳት ክርስቲያናዊ ነውና ሁላችንም በተናጠል እራሳችንን ጠይቀን ለሰላም እንነሳ። እከሌን ብናገረው እንጣላለን ከመሃበር ያባርሩኛል ያልሆንኩትን ስም ይሰጡኛል፡ ዝምድናችን ይፈርሳል ጔደኝነታችን ይቀራል በቡድን ያጠቁኛል ብሎ በመፍራት ለእውነትና ለመብት አለመነሳት ደግሞ በሕሊና ማስጠየቅ ይኖርበታል እንላለን። ስለሆነም ለሁላችሁም ዛሬ ጥያቄዎች ማቅረብ እንወዳለን። በግል ምን እያደረግን ነው? ሰለኛ ሌሎች እስከመቼ ይወስናሉ?መብትና እምነት፡ ሕግና አምልኮን መለየት የምንችለው መቼ ነው?

ወንድሞችና እህቶች ይህ ከዚህ በላይ ያነበባችሁት መረዋ የመጀመሪያ እትምቱን ሲያወጣ የዘገበው ነው። እኛ ዛሬ ስናነበው የዛሬ ጽሑፍ መሰለን እናንተስ?

ከመረዋ  ቁጥር ፵፬ ደግሞ  እስቲ እናንብብ
10/06/10

 
ይህ ክስ አባላትን ማባረር ከጀመሩ በኋላ የተመሰረት መብትን ለማስከበር የተመሰረት ክስ መሆኑም ለሁላችንም ግልጽ ነው።
ስለሆነም በነገው እለት ምንም ተፈጠረ ምን
መተዳደሪያ ደንቡ ወደነበረበት ካልተመለሰ
የተባረሩ አባላት ካልተመለሱ
የአባላት ክፍያ ወደነበረበት ካልተመለሰ
አንዱ ልጅ ሌላው እንጀራ ልጅ መሆኑ ካልቀረ

የአባላት መብት ካልተጠበቀ
ፖለቲከኞች ከቤተክርስቲያን ውስጥ ፖለቲካቸውን ካላቆሙ
የምእመናንን ጥቅም አስከባሪ ቦርድ እስካልተቋቋመ
ብሎም
ባለፈው እንዳደረጉት ቦርዱ በመሰብሰቢያ አዳራሻቸው እነ አቶ ሃይሉ እጅጉን ጠርተው እየተሳደቡት ክስ ከመሰረቱት ውስጥ ነህና ካላረፍክ እንከስሃለን የክስ አጋሮችህንም አብረን ለፍርድ እናቆማለን እንዳሉት በተናጠል ማስፈራራት እስካላቆሙ ድረስ
በቦርዱ ብሎግ መሳደባቸውን እስካልገቱ ድረስ
መታገላችንን አናቆምም


አንዳዴ  ትላንት የተጻፉ ጽሑፎች ዛሬም እንዳዲስ የዛሬውን የሚተርኩ ይመስላሉ።

ይህንን ዳግም ልናስነብባችሁ የተነሳነው መረዋ ትላንትና የዘገበው ዛሬም እውነት መሆኑን ለአንባቢዎቻችን ለማስይረዳል ይጠቅማል ብለን በማሰብ ነው። ከሳሾች በስድብ አልደነበሩም። በማስፈራራት አልተበተኑም። በውሸት ወሬ አልበረገጉም። የሚንበረከኩት ለፍቅር፤ ለእውነት ለመሆኑ ደግሞ ጥርጥር የለንም። ይህንንም በተደጋጋሚ ሊያወያዩ ለተነሱ አዛውንቶች ሁሉ ያረጋገጡት ለመሆኑ መስካሪዎቹ አዛውንቶቹ ይሆናሉ እንላለን። በመወያየት የሚያምኑት የከሳሽ ወገኖች የሚያሸንፉትም ሆነ የሚሸነፉት በውይይት ብቻ እንደሆነ ያምናሉ። ለካሳ አልተነሱም፡ ለመብት መከበር እንጂ። አማንያንን ለመበታተን አልተነሱም የተበተነውን ለመሰብሰብ እንጂ። ለመከፋፈል አልተነሱም አንድነትን ለመፍጠር እንጂ። ይህ ደግሞ ሊመጣ የሚችለው በመነጋገር ብቻ እንደሆነ  ጥርጣሬ  የላቸውም።   የመነጋገር በሩ ከተዘጋ ግን አማራጩ አንድ ብቻ ይሆናል። መብትን በፍርድ ቤት ማስከበር ብቻ። ይህ ሳይሆን ክሱን ተው ብሎ መጠየቅ ግን "ታንክ ከያዘ ጠላት ፊት ቡጢ ይዛችሁ ቅረቡ" እንደ ማለት  ይመስላል።
ከሳሽ የምንላቸው ግለሰቦች ገንዘባቸውንና ጊዜአቸውን የማባከን ሱስ የለባቸውም። ለመብታቸው ትግል ባይጀምሩ ኖሮ ግን እንደማይሰደቡም ያውቃሉ። እንደ ቦርድ አባላት በ ሺ የሚቆጠር እንደፈለጉት የሚያጠፉት የባንክ ደብተርም የላቸውም። ከደጋፊዎች የሚሰበሰብ የድጋፍ መዋጮ እንጂ። ታዲያ የሚያገኙት ምንድነው ለሚሉ ግለሰቦች መልሱ መብታቸውን ማስከበ ይሆናል። ትላንት ፍርድ ቤት ባይሄዱ ኖሮ   81 የቤተክርስቲያን አባላት ከቤተክርስቲያን በፖሊስ ተባረው ነበር። ፍርድ ቤት ባይሄዱ ኖሮ ቤተክርስቲያን ለአምልኮ እንኳን እንዳይደርሱ ተከልክለው ነበር። ይህንን እንዳያደርጉ በፍርድ ቤት ሲታዘዙ አይደለም እንዴ የቦርድ አባላት ይግባኝ ብለው ዛሬም የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በጉጉት የሚጠብቁት። ለምን እንደባበቃለን። ከሳሾች አባላት አይደሉም አናውቃቸውም ያሉት የቦርድ አባላት አይደሉምን?ለምን እንደባበቃለን። ከሳሾች የጀርመን ናዚ ፋሽስት የወጣት አባላት አይነት ናቸው ብለው ለፍርድ ቤት ቃላቸውን የሰጡት አሁንም የቦርዱ አባላት አይደሉምን?
ለምን እንደብቃለን? ከሳሾች ልጆች እንደሌላቸው ሁሉ፣ ሕጻናቶችን ከጫማ ጋር ከፎቅ ላይ ወደ መሬት ሊወረውሩ ነበር ተብለው በፍርድቤት አልተወነጀሉምን? ይኸ ልክ አይደለም ያሉ ሁሉ ከሳሾችን ለመርዳት ቃል እንዲገቡ አደረጋቸው እንጂ እነሱ እንዳሰቡት ደጋፊ አላሳጣቸውም። የቦርድ ደጋፊ ነን ባይ ጦማርም "they are  inocent till they are prooven  gilty"  ሲሉ አላዳመጥንም። ብቻ  ሆድ ይፍጀው። አገሩ ደግሞ  የዲሞክራሲና  የመብት አገር የሕግ የበላይነት ያለበት ምድር መሆኑ እረዳን።

ይህንን በዚህ እናጣፋና ወደ ሌላ ጉዳይ እንግባ

ከዚህ በፊት በደረሰው በወጣቱ ሐዘን ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፎ የነበረው የተባበሩት የሰላምና ፍትሕ አስተባባሪ ኮሚቴ  አጠቃላይ ስብሰባ እሁድ
January  23, 2011 ከቀኑ 1:00 PM
በ DREAMZ CLUB 
እንደሚደረግ የደረሰን ማሳሰቢያ ይገልጻል። በወቅቱ ከስብሰባው በፊት ምሳ  እንደሚኖርም ለመረዳት ችለናል።

ሳንረሳው መጥቀስ የምንወደው ሌላ ጉዳይ አለ። ሰሞኑን በሌላው ጦማር እንደ ተለመደው በአቶ ተኮላ መኮንን ላይ የተሰነዘረውን የሃሰት ውንጀላ አስመልክቶ የተጻፉ መልሶች

 በ WWW.ASSIMBA.COM

እየተለጠፉ እንደሆነ መገንዘባችንን ለአንባቢዎቻችን እንገልጻለን።



የከርሞ ሰው ይበለን።













































Friday, December 31, 2010

በኢሜል ከደረሰን

ውሸታም ሰው ተፈጥሮው ነው። ተቀብሎ ውሸትን የሚያሟሙቀው ግን አደገኛ ነው።

ወድ አንባብያን በዚህ ጽሁፍ ብዙ ለማለት አልፈልግም። በቅርቡ ሰፋ ያለ በእውነት የተደገፈ  ማስረጃ በዳላስ ኢኦቲሲ ጦማር (DALLASEOTC.BLOG)ላይ በወዳጄ  በአቶ  ተኮላ መኮንን ላይ የተነዛውን በሬ ወለድ ጽሁፍ ወደ መጣበት ይመለስ ዘንድ ሙግቴን አቀርባለሁ። ለዛሬ ግን በዚህ በዳላስ ኢኦቲሲ በሚባል ጦማር ላይ የሚነዛው የውሸት ቧንቧ በተለይ ሰሞኑን በሃዘን ሁሉም የዳላስ ኢትዮጵያዊ ባዘነበት ሰሞን ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በጎደለው መንገድ ስለሃዘኑ የጻፉት ሲያሳዝነኝ ይባስ ብለው የውሸት ወሬ ተቀብለው ሲደልቁት ሳይ በዝምታ መታለፍ እነደሌለበት በማመኔ ትንሽ ለመጫር ተገደድኩኝ። ለማንኛውም በቅርቡ በሰፊው እመለስበታለሁ ለዛሬው ለሁላችሁም መልካም አዲስ አመት እያልኩ ከበሬ ወለደ ወሬኞች ያድነን እያልኩ እሰናበታችኋለሁ።


ደም መላሽ ደበበ
ከዳላስ
12/31/2010 4:00 ፒ መ




መከበር ላልፈለጉበተደጋሚ ለማስፈራራት በማሰብ የስድብ ውርጅብኝ በዳላስ ኢኦቲሲ ሲሰነዘርብኝ ቆይቷል። ሁሉንም በንቀት በማለፌ ዛሬ በሬ ወለደ አሉባልታ እየነዙ ይገኛሉ። ለተጻፈው ውሸት በዳስ የሚኖሩ ሳይቀር በብዛት የሕይወት ምስክሮች በአሜሪካ ስለሚገኙ ደንታም አይሰጠኝም። የውሸት ስም ማጥፋትና የአንድ ወር ማስጠን ቀቂያ ግን ሕጋዊ መብቴን መጋፋት በመሆኑ ቤተሰቤንና ሕይወቴን ለመጠበቅ የሚቻለኝን ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ተገድጃለሁ። መረዋ ባይኖር ኖሮ መተንፈሻ ቦታ አናገኝም ነበር።



From: TEKOLA MEKONEN Add to Contacts


To: Yetayal ewnetu





ለመረዋ ምስጋናዬ የላቀ ነው።



ተኮላ መኮንን

t.mekonen@verizon.net

Wednesday, December 29, 2010

በሐዘን የሚቀልድ ደካማ ሰው ብቻ ነው። ቁጥር ፶፬

ውድ የመረዋ አንባብያን ሰሞኑን የደረሰብን ሐዘን መሪር ነበር።  ሁሉም በወጣቱ ልጃችን በማትያስ ከበደ ብርሃኑ ሞት እጅጉን ለማዘኑ በወቅቱ ተሰብስቦ የነበረውን ምእመን ለቅሶ በማየት መገመት ይቻል ነበር። ወጣቶችና ሕጻናት ከመካከላቸው የተለየውን ጨቅላ ለመሰናበት ተሰብስበው የተናገሩትን ሁሉ ስናስታውስ ልጆቻችን ከኛ የተለየ አመለካከት፤ ከእኛ ዘንድ የራቀ ፍቅር እንዳላቸው አየንና በነሱ ተስፋ ተጽናናን። የቤተክርስቲያኑ መሪዎችም ልባቸው በሐዘኑ ተነክቶ የቤተክርስቲያኑን  አዳራሽ መፍቀዳቸውን ስናይ ደግሞ ሚካኤል ዋጋቸውን ይክፈላቸው እንዳልን ሁሉ በሐዘንም ፖለቲካ ሲጠቀሙ ማየታችን ግን አሳዝኖናል። ሊነበቡ የተዘጋጁትን ጽሑፎች እንዳይነበቡ  መከልከል አግባብ አልነበረም። ጽሑፉን ያዘጋጁትን ግለሰቦች ለመቅጣት በማሰብ ሃዘንተኛውን አብሮ መቅጣት በኛ አመለካከት ትክክል አልነበረም። አቶ አበበ ጤፉና አቶ ሙሉአለም ስለ ግለሰቦች ከመፍረዳቸው በፊት እራሳቸውን ቢያስተውሉ ኖሮ   እንደዚያ አይነት ውሳኔ ላይ ባልደረሱም ነበር።  ሰውን በፍቅር እንጂ በጥላቻ ማሸነፍ አይቻልም። ያም ሆነ ይህ ሐዘኑን ተወጣነው። በድጋሜ ዛሬም ለልጃችን ዘለዓለማያዊ እረፍትን ለወላጆቹ ጽናትን ለቤተሰብና ጓደኛ ብርታትን እንለምናለን።

በዚሁ ባለፈው ሳምንት ለብዙ ጊዜ አብረውን የነበሩ እናታችን ወይዘሮ ሰናይት ኃይሌም ከመካከላችን ተለይተውናል። ከጅምሩ የዚህ ቤተክርስቲያን መስራች የነበሩት ወይዘሮ ሰናይት ኃይሌ ለዳላስ ሚካኤል ያበረከቱት አስተዋጽኦ ቀላል አልነበረም። ልጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጭምር ለሚካኤል እድገት አስተዋጽኦ ያደረጉ ግለሰቦች ሥም ሲጠራ የመጀመሪያውን ስፍራ እንደሚይዙ የማይስማማ  ግለሰብ ቢኖር የቤተክርስቲያናችንን ታሪክ የማያውቅ ወደ ከተማችን በቅርቡ ጎራ ያለ ብቻ ይሆናል።  ለወይዘሮ ሰናይት መንግስተ ሰማያትን ለልጆቻቸውና ቤተሰባቸው  መጽናናትን መረዋ  እየተመኘ፡ የሐዘናቸው ተካፋይ እንደሆነም  ይገልጻል።

ይህንን ካልን ዘንዳ፡

በዛሬው እለት የምናስነብባችሁ የዳላስ ምእመን በመላ በሐዘን ላይ እያለን የቦርድ ደጋፊዎች ነን የሚለው ጦማር (BLOGS)በገጹ ላይ የለጠፈውን ጽሑፍ ነው። ጽሑፉን እንዳለ ገልብጠን ለአንባብያን አቅርበነዋል። ከዚህ በታች ያለውን አንብቡና ፍቀር እምነት እያሉ የሚሰብኩን አስመሳዮች ለሐዘን ደንታ የሌላቸው ፈሪሃ እግዚአብሔር የራቃቸው ለመሆናቸው ምስክር የሆነውን ብእራቸውን እዩላቸው።እኛ ባባላቸው ካዘንን በ ድርጊታቸው ከተጸጸትንላቸው ቆየን። የጻፉት ጽሑፍ ከዚህ በታች አቅርበንላችኋል መልካም ንባብ። 
[Post a Comment On: Dallaseotc"የተጀመረው መሻሻል ከግቡ እንዲደርስ"




2 Comments - Show Original Post

በጎረቤታችን ላይ የተንኮል ተግባር ከመፈጸማችን በፊት በአምላክ ፊት ምን እንደሚጠብቀን አስቀድመን ብናውቅ ሁላችንም የመጀመሪያውን ድንጋይ ለመወርወር ባልቃጣን ነበር። በዚህ በያዝነው ሳምንት ውስጥ ፈጣሪያችን አምላካችን ለ ዳላስ አካባቢ የክርስቶስ አማኞችና የቅዱስ ሚካኤል ምእመን ብዙ ተአምር አሳይቶናል። እንድንጠነቀቅም ፊታችንንም ወደ ፈጣሪያችን እንድንመልስ ሊያደርገን ሁለት ተአምር አሳይቶናል። አንደኛው የቤተክርስቲያናችን አባል የሆነው ጸሃፊያችን የልቡን አይቶ ሃጢአት ውስጥ እንዳይገባና እንዳይረክስ መልአኩን በ ፖሊስ መልክ ልኮ ከ መጥፎ ተግባር እንዲድን አድርጎታል።




ባኳያውም የዚህን ግለሰብ ኅጢአት ከፖሊስ ሰነድ ውስጥ አውጥቶ በየታክሲያችን ላይ ሲበትንና ያገሩን ልጅ ስም ሲያጠፋ የነበረው ( ስሙን በደረሰበት አደጋ ምክንያት ለመጥቀስ በማንፈልገው ግለሰብ ) ላይ በደረሰው የአባት ሃጢአት ለልጅ በተላለፈ አደጋ ልጁን ያጣው ሰው የቅዱስ ሚካኤልን ደጀ ሰላም መጥናኛ እንዲሆን ያውም በትምህርት ቀን ያስፈቀደለት ማን ይመስላችኋል!


መድረኩን ማስፈቀድ ብቻ ሳይሆን ቀሳውስቱና ዲያቆናት እንዲተባበሩ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረገው ሰው ነው። አሱም ፤በ እኔ ላይ የራሱን ጉድ ደብቆ ልጆቹን በትኖ ብህግ ያገባት ሚስቱን የልጆቹን እናት


ጥሎ ወደ ሴተኛ አዳሪ ቤት የገባ ሰው የኔን ሃጢአት እያጋነነ ለጠላት ስለሰጠብኝ ብሎ አልተቀየመውም። ይሄን ያልነው እኛ ጉዱን የምናውቅ ነን። ይልቅስ በማያውቀው ሓጢአት ዉስጥ ገብቶ ልጁን ማጣቱ አሳዝኖት እንደማንኛችንም ሲያለቅስ አምሽቷል። ታዲያ እኛ እን ማን ሆነን ነው የቅዱስ ሚካኤልን ሥራ ነገ በኛ ላይ የሚደርሰውን አዉቀን የሰው ስም ለማጥፋትና በሃሰት ሰው ለመክሰስ እምንመኘው።


ለዚህ ነው ነገ የሚደርስብንን ብናውቅ ዛሬ እማጥ ውስጥ አንገባም ነበር ያልኩት። በሰው ላይ ተንኮል ለመስራት አንሯሯጥ ሰው ባያውቅብን እግዚአቤሔር ያውቀዋልና፤ ከሱ የሚሸሸግ ነገር እንደሌለ እንወቅ።


አሜን;






December 18, 2010 1:52 PM]

ይህ የኛ ሳይሆን የአስተያየት ሰጭዎች ነው ሊሏችሁ ይነሱ ይሆናል። እውነቱ ግን እነሱ አንብበው ያጸደቁት ብቻ እንደሚወጣ እራሳቸው የሚክዱ ካለመሆኑም በላይ በጦማራቸው BLOGS በአስተያየት መስጫ አምዳቸው በግልጽ ሃላፊነት እንደሚወስዱበት አንብበው እንደሚለጥፉት የተጻፈ ነው። 
እነዚህ ከሆኑ የእምነት ሰዎች በእውነት ብዙ የሚያነጋግረን ጉዳይ አለን። እነዚህ ከሆኑ የመሪዎቻችን ደጋፊዎች ወንድሞቼ ቤታችንን ለማፍረስ ትልቅ ትግል እየተካሄደ ነው። እነዚህ ከሆኑ የቤተክርስቲያናችን አንጋፋዎች ቤተክርስቲያናችን ሽማግሌ የለበትም የሚያሰኝ ነው። ይህ ከሆነ ሐዘንተኛን ማጽናናት ወንድሞቼ ለእናንተው ፍርዱን እንተዋለን። በባህላችን ከምንም በላይ ሃዘንን እናከብራለን። ያንን የማይቀበል ስለሐዘን ደንታ  የሌለው ብቻ  ነው። በመሳደብ ለወጥ ሲመጣ አላየንም። በማስፈራራት ደግሞ ፍቅር አይገነባም።   

የሳምንት ሰው ይበለን።