ለዚህ ያደረሰን አምላክ ክብር ይግባው እንደምንል ሁሉ መጭውንም ያሳምርልን ብሎ መለመን
ደግሞ የተገባ ነው። እንደኛ ሐጥያት ቢሆን ኖሮ ብዙ ቅጣት፣ ብዙ
ግርፋት፣ ይገባን ነበር። አምላክ ግን የምሕረትና የፍቅር አምላክ
በመሆኑ ለሐጥያታችን ይቅርታን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱንም ከፍሎልናልና
እነሆኝ አሁንም በምህረቱ እየዳሰሰን ነው። ለዚህም አምላክ ምስጋና ይድረሰው።
የቤተክርስቲያኑን
ክስ አስመልክቶ ሰሞኑን የሰማንው ዜና አለ። ታዲያ “የዋሸን እለት ሞትን ማለት ነው፡ እውነቱን ነግረናችሁ እበረንዳ ማደሩን እንመርጣለን”
ብለናችሁ ነበርና ዛሬም ቃላችንን አናጥፍም። ከናንተ የተደበቀ ምንም ነገር የለንም እስካሁን የሰነበትነው የናንተን አመኔታ በማካበታችን
ለመሆኑ ሌላ ምስክር መጥርት አያስፈልግም። በመሆኑም በርእሱ እንደገለጽነው The shortest distance between two points is a straight line የሚለው የሂሳብ ሕግ አንዳንዴ እንደማይሰራ መቀበል የግድ ይሏል። ስለሆነም ባለፈው ነግረናችሁ የነበረው
የቤተክርስቲያን ክስ ክሱን መስርተውት የነበሩት ጠበቃ በነደፉት መልኩ መቀጠል ይሻላል አይሻልም በሚል ሰፊ ውይይት ተካሂዶ ሁኔታውን
እንደገና በመዳሰስ ክሱን የተረከቡት ጠበቆች (THE LAW FIRM) ባቀረቡት ምክር ብሎም የሽምግልና ሂደትን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት
ብዙሃኑን ለማሳተፍ በሚልና ሌሎች አማራጮችንም በመዳሰስ የተጀመረ ሂደት ክስ እንዲሰረዝ ለዳኛው ማመልከቻ መግባቱን መስማታችንን
ልንነግራችሁ እንወዳለን። ይህንን በአባላት ላይ የደረሰውን የቤተክርስቲያን አባላት ችግር ለመፍታት በዋናነት የመልአኩ ፈቃድ እንዲታከልበት
ጸሎታችሁ አይለይ እያልን፣ ስለሁኔታው በሰፊው ዝርዝሩ እንደደረሰን
እንደምናሳውቃችሁ ቃል እንገባለን።
በተሳፋሪነት
የሚበሩ ሁሉ አብራሪው እኛ ነን ብለው ቢናገሩ ውሸት እንደሚሆን ሁሉ ጫፍ ይዘን ማሳረጊያ ልናወጋችሁ አንፈልግምና እስከዚያው ጆሯችሁን
ሰጥታችሁ ጠብቁን።
የሳምንት ሰው ይበለን።