ይህንን የቅዱስ ያእቆብን ጥቅስ እንደ እርእስ የመረጥነው ሰሞኑን እየተካሄደ ያለውን የምሽት መንፈሳዊ ጉባኤ ተካፍለን ካዳመጥነው መንፈሳዊ ትምሕርት በመነሳት ነው። ጉባኤው ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ባሻገር ባለው የኬንዋውያን ቤተክርስቲያን እየተካሄደ ያለ ሲሆን፤ ቅዳሜ ማታና እሁድ ማታም እንደሚቀጥል ለመረዳት ችለናል። ከሁለት መቶ ምእመናን በላይ ተሳታፊ የነበሩበትን ይህንን ጉባኤ ስንካፈል የተሰማን ሐዘን የጠለቀ ነበር። በፖለቲካው ብቻ ሳይሆን በሃይማኖትም መለያየታችን የሚያሳዝን ሆኖ ስላገኘነው። "ፈተና የሚመጣው እኮ ሰይጣን ጥንካሪያችንን ሲያይ ነው" ብለው የሰበኩት መምህር በተለይ ሰይጣን እንደማንበገር ሲያውቅ የጭቅ ጅራፉን ያወርደዋል ሲሉ ብዙ ነገር ታወሰን። እዚህ አገር እርችት ሲተኮስ ድብልቅልቁ የሚወጣው እኮ መጨረሻው ላይ ነው ብለን አሰብን። ታዲያ በአሁኑ ሰዓት በአንድ ወገን በጥቂት የቤተክርስቲያን አመራር ክፍልና በጣት በሚቆጠሩ ደጋፊዋቻቸው በአንጻሩ መብታችንን አናስደፍርም በካህን ታጅበን እንጂ በፖሊስ ተከበን አናመልክም በሚሉ ምእመናን መካከል የተጀመረውን መተናነቅ ስናስተውል እውነትም ፈተናው አስከፊ እንደሆነ ታየን። ከግንድ የተገነጠለ ቅርንጫፍ እንደሚደርቅ አትጠራጠሩ ብለው ያስተማሩት አባት ደግሞ ለመለምለም የወይን ዛፉ አካል መሆን እንዳለብን በምሳሌ ከማስተማራቸውም በላይ፤ የማይሆን የዛፍ ተቀጽላም ከዚያም አልፎ ተገድራም መሆን እንደሌለብን ሲያስተምሩ የሚያስተምሩት የኛን ችግር ተረድተው ይመስል ነበር። ቆይተን እንደተገነዘብነው ግን ተናጋሪው ያስተምሩ የነበረው ከሃይማኖት መራቅ እንደሌለብን ሆኖ አገኘነው። የወንጌል ትልቁ ጉልበቱ ደግሞ በተሰማ ቁጥር ከራስ ችግር ጋር፤ ከምናየው ጋር ሁሉ መመሳሰሉና ለዛም መልስ ይዞ መገኘቱ ነው። ታዲያ ቤተክርስቲያን እንደሌለን ተከራይተን ክርስቲያን እንዳልሆንን ሁሉ ተለያይተን መገኘቱ ካስደሰተን ያስተማሩን አባት እንዳሉት እራሳችንን ዞረን መመልከት ሊኖርብን ነው። እኛ ይህንን ገምግመን መስቀል ካልገዛው ሕግ ይዳኘው ብለው የተነሱትን ደግፈናል። የለም ካህናት መሰደብ አለባቸው፤ ምእመናን መታሰር ይኖርባቸዋል፤ የተዋጣው ገንዘብ ካለ እስኪያልቅ እንዋጋለን ሲያልቅ ቤቱን እንሸጣለን ከሚሉት መወገን የምንል ካለን መወገን። ካልሆነ እንደ ክርስቲያንነታችን ባመንበት ጸንተን በእምነታችን ሳንደራደር ለመብታችን ቆመን የሕግን የበላይነት የተቀበልን መሆን ይኖርብናል ብለን የምናምን ተጠናክረን መነሳት ይኖርብናል እንላለን። የኛ ችግር በመብት እረገጣ ላይ ነውና ለዚህ ደግሞ ከሕግ ውጭ መፍትሄ ይኖራል ብለን አናምንም። የሃገራችን ልማድ ተከትለን በሽማግሌ ለመፍታት ካንዴም ከአራት ከአምስት ጊዜ በላይ እንደተሞከረ ሁላችሁም የምታውቁት ጉዳይ ነው። ከሳሾቹ ችግሩን ለመፍታት ሽማግሌዎችን አክብረው ተቀምጠው ተወያዩ። የቤተክርስቲያን አንባገነን መሪዎች ግን ገደል ግቡ አሉ። ይባስ ብለው ፖሊስ ቀጥረው ውሻ አሳጅበው ሊያስፈራሩን ተነሱ። በብሎጋቸው ላይ የቤተክርስቲያኑን አንጋፋዎችና መስራቾች አንተ እያሉ መዝለፍ ጀመሩ። ማ ከማ ጋር ወሲብ እንዳደረገ ማ እንዴት ልጅ እንደወለደ ማ ምን የፖለቲካ አመለካከት እንዳለው ዘገቡ። ካሕናቱን እንደ ሰፈር ዳንዴ ፈረጁ በወሲብ ከባለትዳር ግለሰብ ጋር በመጠርጠር ስም አጠፉ። ይህንን ሲያደርጉ ትዳር እያፈረሱ ቁርባንን እያረከሱ መሆኑ ግን አላስጨነቃቸውም። ዘር ቆጥረው የመንግስት ደጋፊ ናቸው ብለው ትላንት አብረዋቸው የነበሩትን እየተገባበዙ የበሉበትን ሳህን እየሰበሩ የጠጡበትን ጽዋ እየደፉ ታዩ። መንግስትን መደገፍ መብት መሆኑ ግን አልተገለጸላቸውም። ይህን ሁሉ አድርገው ታዲያ ታዛቢያቸው በዛ እንጂ ደጋፊያቸው እንዳልጨመረ በሚካኤል ስም መመስከር ይቻላል። ያ አልበቃቸውም
ካህናትን ሊያዋርዱ ተነሱ ከሸፈ።
በዘር መጡ ተመቱ።
በፖሊስ መጡ ተረቱ።
በፖለቲካ ተንቀሳቀሱ ፈራረሱ።
በገንዘብ ተመኩ ቋቱ እየደረቀ መጣ።
በጉልበት መጡ ጉልበት የሚካኤል ሆነባቸው።
ዛሬ የቀራቸው ለቡድናቸው የሰጡት "የሚካኤል ሰይፍ" የሚለው ስም ብቻ ነው። ያ ደግሞ የድሮውን የቻይና ግሩፕን ያስታውሰናል።
ወንድሞችና እህቶች
"ከራበው ልጄ ይልቅ ለጠገበው ልጄ አስባለሁ" ያሉት ዳላስ ነዋሪ የሆኑ ቤተሰቦች አልነበሩም። አባባሉ የቆየ ነው ለማለት ነው።የራበው ልጅ እቤት ተኮራምቶ ይቀመጣል የጠገበው ግን ማን አለብኝ ብሎ ይደባደብና ወይ ነፍስ ያጠፋና ቤተሰቡን ችግር ላይ ይጥላል ለማለት ነው። እዚህም በዳላስ አካባቢ ታዲያ ከላይ እንደጠቀስነው ሰላም ሲሰፍን እንቅልፍ የሚነሳቸው የሕዝቡ መፋቀር የሚያናድዳቸው፡ ከመጋረጃ ጀርባ ተደብቀው ሲናገሩ በድምጻቸው የማይታወቁ፤ በብእራቸው የማይለዩ፤ በተግባራቸው የማይፈረጁ የሚመስላቸው ግለሰቦች ከትላንትናው ቁጥራቸው እየመነመነ እርስ በርሳቸው እየተወነጃጀሉ ለመሆኑ ብዙ ፍንጭ እየየን ያለ ይመስለናል። በዚህ በከተማችን ለእምነታቸው የቆሙ ትክክል አይደለም ብለው ያመኑትን የተናገሩ ዲሞክራሲ በሰፈነበት አገር መብታችንን አናስደፍርም በጥቂት አንባገነኖች አንገታችንን አንደፋም መብታችንን የሃገሩን ሕግ ተጠቅመን እናስከብራለን ባሉ "ቅዱሳን ነን"በሚሉ ተሰድበዋል "ከኛ ወዲያ ክርስቲያን የለም" በሚሉ ተዘልፈዋል። ያም ሆኖ ግን የተዋረዱት ሰዳቢዎቹ እንጂ የተሰደቡት አልነበሩም።

ባለፈው እንደተናገርነው ሁሉ ማንነታቸውን እያወቅን ስም ጠርተን፤ ድክመታቸውን ፈልፍለን፤ የመኝታ ቤታቸውን ምስጢር አውጥተን ለአንባብያን አላቀረብንም። ያን ባለማድረጋችን ፈሪዎች ተብለን ይሆናል። እኛ ግን በደረቅ መሬት በመጓዛችን እንደነሱ በማጥ ውስጥ አልዳከርንም። ለቤተክርስቲያንናችን በ ሺህ የሚቆጠር ገንዘባቸውን ያፈሰሱ ምእመንን በስድብ ውርጅብኝ የገረፏቸው ግለሰቦች እነማን እንደሆኑ እናውቃለን። ግን ማንነታቸውን በመናገር እነሱን ማስተዋወቅ ደግሞ ለነሱ ክብር እንደሚሆን ስለተሰማን እንዳላወቅን አለፍናቸው። ባለፈ በመረዋ እትምታችን እንደተናገርነው ለአንባብያን ፍንጭ እንዲሆን የተሰደቡትን አባላት ስትለዩ የሚሳደቡት እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ደቂቃ አይፈጅባችሁም። እኛ መልእክቱ እንጂ መልእክተኛው ምን ያደርጋል በሚል እራሳችን ማስተዋወቅ አልወደድንም የመደበቅ ፍላጎት ኖሮን እንዳልሆነ ግን ምስክራችን ሚካኤል ነው። በምንም ሰዓት በሃሳብ ላይ በመታገል እንጂ በስድብ ለውጥ ተገኘ ሲባል ሰምተንም አይተንም አናውቅምና መሳደብን እንደመሳሪያ መጠቀም አልፈለግንም። መኪናችን ቢሰበር የሚጎትትልን ሰው እናጣለን ብለን ሰግተንም አናውቅ። እንጀራ ንግድ ውስጥ ስለሌለንበት ደግሞ የደንበኛ ልምምጥ የለብንም። ገንዘቡና ጊዜው በተገኘ እንጂ አውሮፕላን ጣቢያ የሚያደርሰን ይጠፋል ብለን አንጨነቅም። ለቦርድ የመመረጥ ፍላጎት ስለሌለን ማን ይመርጠናል ብለን አንሰጋም። ሌሎች እንደሚያደርጉት የራሳችንን የቤተሰባችንን ገድል እያወራን ቅዱስነታችንን እየተናገርን ለምርጫ እንዳትረሱን አንልም። የቤተክርስቲያን ስራ በልመና ለብቁዎች የሚሰጥ እንጂ በቅስቀሳ ምረጡኝ ሲባል ጥቅም አለበት እንዴ? ሊያሰኝ ይችላልና።
አገር ቤት ያልተሳካ ፖለቲካ ዳላስ ያለውን ምእመን በማመስ በለስ ሊቀናን ይችል ይሆናል ብሎ ማለም ደግሞ በፖለቲካ አለመብሰል ይመስለናል።
የሚያስጨንቀን ነገር ቢኖር ያልነበሩ ሲመሰክሩ ያልከፈሉ የከፈሉትን አባቶች ሲያዋርዱ ያደጉበት አስነዋሪ ጠባያቸው በስተርጅና ሲያገረሽባቸው ስናስተውል ነው።
የሚያስጨንቀን "ክርስቲያን ነን" እያሉ አዛውንቶችን፤ መንፈሳውያን ነን እያሉ ወንድም እህቶችን የመንደር ዱርዬ እንኳን በማይጠቀምበት አስነዋሪ ቃላት ሲሳደቡ መስማታችን ነው።
እኛ የሚያስጨንቀን በሕዝብ ገንዘብ ንጉሥ ሆነው ባልከፈሉበት አዛዥ ባላጠራቀሙት በታኝ ባልሰበሰቡት ወሳኝ መሆናቸው ነው።የሚያስጨንቀን ክርስቲያንን አባረን የክርስቲያን ስብስብ ነን ሲሉ ስንሰማ ነው።
የሚያስጨንቀን በሬ ወለደ ብለው ሲያወሩ ነው።
ትላንት ለኢትዮጵያ ቀን እንዳትሄዱ ሲሉ ከርመው፤ የኢትዮጵያ ቀን ሳይሳካ ቀረ ሲሉ ሰንብተው፤ መረዋ የነበረውን ለአንባብያን ሲተነትን ገንዘብ ያዋጡትን ግለሰቦች ስም ሳይቀር ሲናገር ውሸታቸው መጋለጡን ሲገነዘቡ አቶ ሰይፉ ካሉበት አቶ መደቅሳ ከገቡበት ችግር የለብንም ብለው መናገር ጀመሩ። ባንድ አፍ ሁለት ምላስ ይሏችኌል ይህ ነው። የወያኔ ቀን ነውና እንዳትሄዱ ብለው በጻፉት ብእራቸው፤የቅዳሜው እለት አልተሳካም እሁድም የተገኙት የእድር ሰዎችና ቤተሰቦች ብቻ ናቸው እንዳላሉ መረዋ ገንዘብ ያዋጡትን ከፊል ስሞች አውጥተው ሲያዩ ተደናገጡ። ግለሰቦቹን እንዳይሳደቡ ደግሞ ገንዘብ አዋጡ ተብለው ስማቸው ከተጠቀሰው አንዳንዶቹ በቤተክርስቲያኑ ጉዳይ ቢያግዟቸውም በመረዳጃ መሃበሩ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አመለካከት እንደማይጋሩ የተገነዘቡት ሆነ። ታዲያ እነሱን ቢሳደቡ ጸሐፊዎቹ እነማን እንደሆኑ ስለሚያውቌቸው የሚመጣባቸው ችግር ስለታያቸው ሕዝቡም እየሸሻቸው መምጣቱን ሲገነዘቡ ተገልብጠው መልካም ጅምር ነው ማለት ጀመሩ። ሃሌ ሉያ። የሚደገፍ አቋም ነው። ይህንን ስላደረጉ ደግሞ እኛ እነሱ በሄዱበት ጎዳና በምንም አይነት አንደማንጔዝ ቃል እንገባላችኋለን። የኛን መንገድ ሲቀላቀሉ ደግሞ ደስተኛ እንሆናለን እንጂ ለምን አጣበባችሁን ብለን አንከፋም። በብሎጋቸው የጻፉትን አንስማማበትም አቶ ዮሴፍ ላይ የተጻፈው የኛ አቌም አይደለም አሉና አረፉት። አሁንም ግን ስለ ጋሼ ሃይሉ የተጻፈውን አልኮነኑም። ስለፍቅረማርያም ያወሩትን አልኮነኑም፤ ስለ አዜብ የተሳደቡትን ይቅርታ አልጠየቁበትም፤ ስለብዙአየሁ ያወሩትን አላፈሩበትም፤ ስለ አቶ ጌታቸው ትርፌ በተደጋጋሚ ያወጡትን እንደኮሩበት ነው። ስለፈትለወርቅ የተናገሩት አላሳፈራቸውም። ስለ ተፈራወርቅ የጻፉትን ይኮሩበታል ማለት ነው። ስለአቶ ተኮላ የዋሹትን አልተሸማቀቁበትም። ጥሩአየር ሲዘልፉ ምን ማለታቸው እንደሆነ እራሳቸውም ግራ የተጋቡ ለመሆኑ ያወቁት አይመስለም። አቶ ግርማቸውን በመሳደባቸው አሁንም ትልቅ የሆኑ እንደመሰላቸው ነው። ስለሙላው ሲዘባርቁ ያሸነፉ እንደመሰላቸው ነው። ስለ ጸሃይ ጽድቅ ወንጀል ሲያወሩ የሚያስከትለው ምን ይሆን? ብለው አልነበረም። ከሁሉም የሚገርመው ዳዊት አለማየሁን በዘሩ ሳይቀር ተሳድበው እንቅልፍ ወስዷቸው ካደረ ወንድሞቼ እነዚህ ሰዎች ወንጀለኞች ናቸው። ብዙ መጥቀስ ይቻላል። ስለተሳደቡ ግን አላሸነፉም እንደምታዩት እየተሸነፉ መጡ እንጂ። ከሁሉ የገረመን ለቤተክርስቲያኑ ገነዘባቸውን ያፈሰሱት አቶ ሃይሉና አቶ ምናሴ የስድብ ውርጅብኝ ሲያወርዱባቸው ተዋቸው እንሱን በፍቅር መዋጋት ብቻ ነው ያለብን ብለው ሲናገሩ ስንሰማ ነው። ያንዳንዱን የመንፈስ ደካማነት በማየት የሚያዝን ሰው በሌላው ጥናት ይጽናናል ማለታችን ነው።

ዛሬ እርስ በራሳቸው እየተላተሙ ነው። ነገ አቀርቅረው እንደሚቀሩ ደግሞ ምንም ጥርጥር የለንም።
የሳምንት ሰው ይበለን