ባለፈው የቦርድ አባላት ግለሰቦችን ከቤተክርስቲያን እንዳያባርሩ ዶሴዎችን እንዳያጠፉ ተጥሎባቸው የነበረውን እገዳ በመቃወም ይግባኝ ማለታቸው የሚታወስ ነው። በትላንትናው እለት ጉዳዩን የሰማው ፍርድ ቤት ዳኛው አስቀምጦት የነበረውን እገዳ በማንሳት ክርክሩን ወደሚያዳምጡት ዳኛ መልሶ መላኩን ለመረዳት ችለናል።
በዳኞቹ አባባል የመታደደሪያ ደንቡ ማንንም ሰው ቤተክርስቲያን እንዳይመጣ ቁርባን እንዳይቀበል ቦርዱ መከልከል አይችልም የሚለውን ይህ በውሰጥ ሊፈታ የሚችል በመሆኑ ፍርድ ቤት ማዘዝ አይችልም ብለው ሲወስኑ የጉዳዩን ጭብጥ ክርክር ግን አናይም በማለት ውሳኔው እገዳውን በተመለከት ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰው ሁኔታውን እንዲያዩትና ክርክሩን እንዲሰሙ ለዳኛ ስሚዝ ዶሴውን መልሰው መላካቸውን ጠቅሰዋል።
ገንዘብ እንዳያባክኑ ዶሴዎችን እንዳያጠፉ ተጥሎ የነበረውን እገዳ ዳኞቹ ቦርዱ ገንዘብ ለማባከኑና ዶሴዎችን ለማጥፋቱ የቀረበ መረጃ ባለመኖሩ እገዳውን አንስተንዋል ሲሉ ወደፊት ግን ይህ ለመደረጉ መረጃ መስማት እንዲችሉ ለዳኛ ስሚዝ ጉዳዩን ክፍት በማድረግ ትተውታል።
ይህንን አስመልክቶ ሊቀርብ የሚችል ብዙ መረጃ መኖሩን ስለምናውቅ የሚያስጨንቅ አለመሆኑን ለአንባብያን መናገር እንወዳለን። እስካሁን ምንም ክርክር ሳይጀመር ምስክር መስማት ሳይቻል በአሰራር ብቻ እየተወሰነ ያለውን ጉዳይ አለቀ የሚሉ ካሉ ትልቅ ስህተተ እየተሳሳቱ እንደሆነም መናገር እውነት ይሆናል።
የይግባኝ ፍርድ ቤቱ በእገዳው ላይ ብቻ ውሳኔ መስጠታቸውን ተናግረው ክሱን አስመልክቶ ምንም ውሳኔ አለመስጠታቸውን አስፍረዋል። ይህንን ማድረግ የሚችሉት ዳኛ ስሚዝ እንደሆኑም ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን። ለዚህም ነው ዶሴው ወደሳቸው ፍርድ ቤቱ የተመለሰው።
በ3/23/2011 9:15 AM
በዳኛ ስሚዝ ችሎት እንድንገናኝ ጥሪ እያቀረብን ለዛሬው በዚሁ እንሰናበታችኋለን።
ክርክሩ ተጀመረ እንጂ አላለቀም።