Saturday, March 20, 2010

አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ ቁጥር ፲፰

ይሻላታል ብለው ገዳም ቢሰዷት፤
ነካክተው ነካክተው አባባሱባት።
ብለው የተቀኙት ማን እንደነበሩ ስማቸውን ማስታወስ ተቸገርን እንጂ ቅኔው እንዳለ ትላንትና የተቀኘ ይመስል አሁንም አዲስ ነው። ቀደም ባለው ጊዜ ነው፡ {ሆይ ጉድ እኛም እንዳባቶቻችን የሰገሌ ጦርነት አቆጣጠር አይነት ቀደም ባለው ሰዓት ማለት ጀመርን፡} ወረታ በተባለው ከተማ አካባቢ የተሾመ ወረዳ አስተዳዳሪ እንኳን ወረዳ አጥቢያም ማስተዳደር እንደማይችል ሲያውቁ ያካባቢው አዝማሪዎቹ በጠጅ ቤት ስም እየጠሩ ማመሳሰል ጀምረው ምን ብለው ዘፈኑ አሉ መሰላችሁ።
ምድር እንኴን ሲያረጅ ያበቅላል እንግጫ
አቶ አበበ ነወይ የጋሽ ክፍሌ ልውጫ።
እኛም ይኸው እድሜያችን ከረመና እነ አቶ ሙሉአለም መሪዎቻችን እነ አቶ አበበ ጤፉ የኤኮኖሚ ጠበብቶች የጂኦግራፊ ምሁሮች የቤተክርስቲያን ደብተራዎች እሆኑበት ዘመን ደረስን። ነገ ደግሞ የላበኩ ዶክተር ከደጀ ሰላሙ መሬት ተጋርተው የሆነ መጋረጃ ጋርደው ነርሱን አቶ አበራን ተከተለኝ በማለት ድውያን እፈውሳለሁ ብለው ተነስተዋል ቢባል መከተል ነው እንጂ ምን ምርጫ አለን የሚለው ምእመን ይበዛ ይሆናል ብለን ብንጠራጠር የምትፈርዱብን አይመስለንም። ቤተክርስቲያናችን ከድጡ ወደ ማጡ ከገባ ቆየ። ወንድሞችና እህቶች አሁን እየተጻፈ ያለውን ብሎግ ያነበብ ሁሉ ባካባቢያችን እየተደረገ ያለውን የፖለቲካ ሽኩቻ በሃይማኖት ሽፋን እየተላለቅን ለመሆኑ ምስክር መጥራት አስፈላጊ አይመስለንም። የሚገርመው ትላንትና ከትላንት ወዲያ እንዳልናችሁ ለሕዝብ መብት እንቆማለን፤ የፖለቲካ እምነት እናራምዳለን የሚሉት ግለስቦች በጠመንጃ ያልሆነላቸውን በመስቀል ሽፋን ሊታገሉ ሲነሱ ልባቸውን አራርቶት ይሆናል ብለን የምናምን ግለሰቦች ነፃ መረማመጃ መንገድ እየከፈትንላቸው እንደሆነ አለመገንዘባችን ነው። ቤተክርስቲያን ደግሞ አምልኮ እግዚአብሄር የሚካሄድበት ቦታ እንጂ ተንኮል የሚሸረብበት ደጋፊ የሚታቀፍበት የሚጠይቅ የተቃወመ የሚባረርበት ስፍራ ከሆነ ቤተክርስቲያንነቱ ቀርቶ የፖለቲካ አዳራሽ ሆነ ማለት ነው። ዛሬም በድጋሜ እንናገር በዚህ በቤተክርስቲያን የተከሰተው ችግር የሃይማኖት ሳይሆን የፖለቲካና የጥቅም ግጭት ነው ብለን እናምናለን። ገንዘብ ሳይኖረን እንዋደድ ነበር ገንዘብ ሲበዛ ጥላችንም በዛ ማለት እውነት ለመሆኑ ማስረጃውን እያየነው ነውና።

ለውይይት እንዲመች መረዋ ዛሬ ለሁላችንም ለየት ያለ ጥያቄ ይዞ ቀርቧል

ሁላችንም ለቤተክርስቲያኑ የከፈልነው ገንዘብ ስንት ነው? በጉልበት ምን አድርገናል? ብለን እራሳችንን እንጠይቅና ከመልሳችን በመንደርደር ወደቀጣዩ ነጥብ እናዝግም። ይህ ደግሞ ቤተክርስቲያኑ ከተጀመረበት ወቅት ጀምሮ ያዋጣነውን፡ ያደረግነውን ሁሉ ያጠቃልላል። አንድ ድርጅት ሲቌቌም የባለቤትነት ጥያቄን የሚመልሰው የመስራች አባላት ስብስብ ነው ብለን ስለምናምን። በመሆኑም በእኛ የማስታወስ አቅም አንዳንዶቹን እናንሳ። በገደፍነው ሞልታችሁ የተረሳውን አስባችሁ አንብቡት ለማለት ነው።
አቶ ሰይፉ ይገዙ፦ ይህንን ቤተክርስቲያን በገዛንበት ወቅት የተጫወቱትን ሚና ሊክዱ የሚችሉት ዶክተሩና ደጋፊዎቻቸው ሊሆኑ ይችላሉ ብለን እንጠረጥራለን። ካልሆነ ቤታቸውን አሲዘው matching grant አስገኝተው ሕልማችን እውን እንዲሆን ያደረጉ ግለሰብ ለመሆናቸውና ለዚህ ቤተክርስቲያን የተቻላቸውን ለማድረጋቸው መመስከሩ እኛን ያስደስተናል እንጂ አያስፈራንም።
አቶ ሃይሉ እጅጉ ከጀማሪዎች አንዱና ከማንም በላይ ለቤተክርስቲያኑ ገንዘባቸውን የለገሱ በአርአያነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ግለሰብ በተመራጭነት ያገለገሉ።
አቶ እዩኤል ነጋ ከአመሰራረቱ ጀምሮ ጉልበታቸውን ጊዜአቸውን ገንዘባቸውን ለቤተክርስቲያኑ ያዋሉ ግለሰብ ለመሆናቸው ምስክር የሚያሻ አይመስለንም።
አቶ ምናሴ በየነ የቤተክርስቲያኑ ጀማሪ በጉልበት በገንዘብ ከሁሉም የማይተናነስ አስተዋጽኦ ያደረጉ።
አቶ ኪዳኔ ምስክር ከጀማሪዎቹ አንዱና በጉልበት በጊዜአቸው በገንዘብ ከማንኛችንም በላይ መስዋእትነት የከፈሉ። ሲሰድቧቸው የሚስቁ ሲገፏቸው ይቅርታ የሚጠይቁ። {የባለቤታቸውን ተሳትፎ ሁሉም የሚያውቀው በመሆኑ መናገር ደግሞ ቡራኬያቸውን መጋራት እንዳይሆን እንሰጋለን።}
ወይዘሮ ሃይማኖት በየነ የአቶ ኪዳኔ ምስክር እናት፦ ይህ ቤተክርስቲያን ሲመሰረት ያንገታቸው ወርቅ ሳይቀር አውልቀው በመሸጥ ለቤተክርስቲያኑ ያበረከቱ። ጊዜአቸውን ንብረታቸውን ያፈሰሱ።
ዲያቆን አርአያ ኃይለመስቀል {በዚህ አጋጣሚ የቤተክርስቲያኑ መስራች የነበሩትን እናታቸውን ወይዘሮ የሺሃረግ ወልደጊዮርጊስን ማስታወስ ተገቢ ይመስለናል}በድቁና በተመራጭነት በገንዘብ ከማንም ባላነሰ ያገለገሉ የከፈሉ።
አቶ ዬሴፍ እረታ በጀማሪነት ብሎም በተመራጭነት ያገለገሉ አሁንም በማገልገል ላይ ያሉ።
ዲያቆን ጌታቸው ወልደሚካኤል በድቁና በተመራጭነት በገንዘብ ቤተክርስቲያኑን ያሳደጉ።
አቶ ጌታቸው ትርፌ ከመስራቾች አንዱ ሆነው በተመራጭነት ለማገልገል ፈቃደኛ ባይሆኑም በኮሚቴ ውስጥ ያገለገሉ ገንዘባቸውን ጊዜአቸውን የሰው። {ባለቤታቸው ተመራጭ ሆነው ማገልገል ብቻ አይደለም በኮሚቴ ውስጥ ያገለገሉ መሆናቸውን መጥቀስ ያስፈልጋል}
አቶ ብዙአየሁ ጌታቸው በተመራጭነት አሁንም እያገለገሉ ያሉ ከመሆናቸውም በላይ ምናልባትም ከማንኛችንም ባላነሰ ገንዘባቸውን ያበረከቱ ጊዜአቸውን የለገሱ መክፈላቸው እንዳይሰማ ይደብቁ ስለነበር በመናገራችን ሐጥያቱን እኛ ተቀብለን በንስሃ ልናወርድ እንሞክራለን።
አቶ ጸሃይ ጽድቅ ቤተማርያም ለቤተክርስቲያኑ መሰቀሎችን ንዋዬ ቅዱሳትን በማቅረብ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የሚበሩትን 24 መብራቶችን ያበረከቱ በገንዘብ ቤተክርስቲያኑን የደጎሙ።
ወይዘሮ በየነች መኮንን እኝህ እናት ለወጣት ልጆቻችን ካላቸው ፍቅር ለታዳጊ ወጣቶች ያበረከቱት ግልጋሎት የማይረሳ ከመሆኑም በላይ በተመራጭነት በኮሚቴ ተወካይነትያገለገሉ።
አቶ ታደሰ ጸሃዬ በገንዘብ በጉልበት ከማንም ባላነሰ ለዚህ ቤተክርስቲያን አስተዋጽኦ ያደረጉ።
ዶክተር አምሃ ኃይለመስቀል በገንዘብ ብሎም የዘማርያንን አልባሳት ወጭ በመሸፈን በጉልበት ሁሉ ያገለገሉ።
አቶ አጽቀ ግርማ የድሮውን ቤተ ክርስቲን አጥር ለማሳጠር የወጣውን ወጪ በግላቸው የሸፈኑ ከማንም ያላነሰ የገንዘብ መዋጮ ያደረጉ።
ዶክተር ግርማ በቀለ በተመራጭነት ያገለገሉ በገንዘብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ።
አቶ ዳኜ ላቀው በተመራጭነት በሽማግሌነት ያገለገሉ።
አቶ ግርማቸው አድማሴ በገንዘብ በተለይም ቤተክርስቲያኑን ከችግር ለማዳን መተዳደሪያ ደንቡን እንዲያጠና የተቌቌመውን ኮሚቴ በሰብሳቢነት በመምራት ትልቅ ተጋድሎ ያደረጉ።
አቶ ዳዊት አለማየሁ በተመራጭነት በገንዘብ ቤተክርስቲያኑን የረዱ ሌት ከቀን ደከመኝ ሳይሉ ምንም ቀን ከመቅደሱ በር ሳይለዩ እያገለገሉ ያሉ አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰብ ናቸው።
አቶ ኪዳኔ በየ በተለያየ ወቅት ገንዘባቸውን መኪናቸውን ሳይቀር የለገሱ።
አቶ ኤልያስ ገ/ስላሴ በተጠየቁ ሰዓት ሳይሆን ሳይጠየቁም ለቤተክርስቲያን መለገስን እንደ ባህል የወሰዱ የውጭ መብራቶችን አሰርተው ያመጡ መኪና ሳይቀር የለገሱ በኮሚቴ ተመራጭነት ያገለገሉ።
ወይዘሮ ፍኖት ጋሻው ለቤተክርስቲያናችን እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ በዘማሪነት በተለያዩ ኮሚቴዎች ያገለገሉ በአርአያነት የሚጠቀሱ አኩሪ እናት ናቸው። [ባለቤታቸው ዲያቆን በላይ በችግሩ ጊዜ በድቁና ቤተክርስቲያኑን ሲያገለግሉ የነበረ፡ በተመራጭነት ይህንን ቤተክርስቲያን እዚህ ካደረሱት ግሰቦች አንዱ ናቸው።
ወይዘሮ ገነት ከበደ በገንዘብ በኮሚቴ አባልነት ደከመኝ ሳይሉ ይህንን ቤተክርስቲያን ከልባቸው ያገለገሉ።}


እነዚህና እናንተ የምታውቌቸውን ግለሰቦች ሰብስበን ለምን ይህ ቤተክርስቲያን ተቌቌመ? አላማችሁ ለፖለቲካ ተወካዮች አሳልፎ ለመስጠት ነበረ ወይ? ባቌቌማችሁት ቤተክርስቲያን ወሳኙ ሕዝብ መሆን ይኖርበታል ብላችሁ ታምናላችሁ ወይንስ በጉልበት ሕጉን ቀይሮ አማኞችን እያባረረ ክርስቶስን ሳይሆን የኛን የበላይነት መቀበል አለባችሁ የሚለውን ፈላጭ ቆራጭ ቦርድ? ቅንጅት ሆኖ ክርስቲያን ኢሕአፓ ሆኖ አማኝ ኢሰፓ ሆኖ ቆራቢ ኢዲው ሆኖ ደብተራ የሆነ እንዳለ ሁሉ በፖለቲካ የማያምን ግለሰብ ወይንም ኢትዮጵያ ያለውን መንግስት የሚደግፍ የኦርቶዶክስ አማኝ አለ ብላችሁ ታምናላችሁን? ካልሆነ እንደ ክርስቲያንነታችሁ ብቻ ሳይሆን እንደ መስራች አባልነታችሁ ለተደነቀረብን ችግር ለተፈጠረው ፈተና ምላሻችሁ ምንድነው? የቤተክርስቲያኑ የወደፊት ጉዞ ካላማረን ያዋጣነውን ድርሻችንን የመካፈል ጥያቄ ማቅረብ ቢጀመር መልሳችሁ ምን ይሆናል?
ግማሾቻችሁ ከሳሽን እንጎዳለን ብላችሁ ያወጣችሁት መተዳደሪያ ደንብ ዛሬ እናንተንም አላላውስ ማለቱን ስታዩ ምን ተሰማችሁ?
ቤተክርስቲያናችን ከሰሱ በሚባሉት ሰዎች ነው ወይንስ በነሙሉዓለምና በምሁራን ተመራጮች ነው እየፈራረሰች ያለችው?
አበበ ጤፉ ሰላም ፈጣሪ፡ ዲያቆን አርአያ ቤተክርስቲያን በታኝ።
ሙሉአለም ክርስቲያን፡ ዲያቆን ጌታቸው ከሃዲ።
ዶክተር ግርማ ታማኝ፡ አቶ ተኮላ ዘራፊ።
አበራ ፊጣ ጸሎተኛ፡ አቶ በቀለ አስመሳይ።
ወይዘሮ ሰሎሜ መንፈሳዊ፡ ወይዘሮ ጥሩአየር ዓለማዊ። ናቸው ብላችሁ ታምናላችሁን? የነዚህን መልስ ከመለሳችሁ ችግሩ በቀላሉ ይፈታል ብለን እናምናለን።

ብዙዎቻችሁ አቌም ለመውሰድ የተቸገራችሁት ለምን ይሆን? ለሚባል ጥያቄ ብዙዎች ምእመናን ሲመልሱ ምንአልባት የላበኩ ዶክተር ያገኙባቸው መረጃ ቢኖር ይሆናል እንጂ ቢናገሩ የሚሰሙ ግለሰቦች ዝም ማለት አልነበረባቸውም የሚለው አባባል የከተማ መወያያ ነጥብ መሆኑን ሳትሰሙ የቀራችሁ አልመሰለንም። ችግር ፈጣሪዎቹ ከሳሾች ናቸው ከተባለ ከዶክተሩ ጋር በመቆም፡ የለም የከሳሾች ጥያቄ የመብት ጥያቄ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ደግሞ ከከሳሾች ጎን በመሰለፍ አስቸኴይ የሆነ መፍትሄ ማምጣት ስትችሉ ዝምታው ለምን እንደሆነ ሁሉንም ግራ ያጋባ ጉዳይ ነው። መተዳደሪያ ደንቡን የቀየርነው ለክስ መርቻ እንጂ ለዘለቄታ መፍትሄ ነው ብለን አልነበረም የሚሉት የትላንታና የቦርድ ተመራጭ የነበሩት እመቤት ስህተተ መሰራቱን ለመቀበል ዳር ዳር የሚሉ ይመስላል። ታዲያ እሳቸውን በድጋሜ ማስመረጥ ያቃታቸው ባለቤታቸው እንደውድ ባለቤታቸው ትላንት ተሳሰቼ ነበር ብለው ቢነሱ ምናልባት አንሰማህም ያላቸው ምእመን እንደገና ጆሮ ይለግሳቸው ይሆናል ብለን እናስባለን።
በእኛ እምነት ክርስቲያንን የሚያስፈራው ምንም ነገር ሊኖር አይችልም ብለን እናምናለን። የመጨረሻ ማስፈራሪያ ሞት ሆኖ ሳለ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ደግሞ በትንሳኤ ያምናልና። ስለዚህም ነው እውነትን ክዶ ከመኖር ለእውነት መሞትን መምረጥ ይሻላል የምንለው። ካልሆነ ግን በአዲስ መንፈስ ባዲስ ጉልበት ሊበታትኑን የተነሱት የቦርድ ተመራጭ ነን ባዬች ሳይበታትኑን እንደማይተኙ እመኑ። በርእሱ ላይ አዲስ እረኛ እንቅልፍ አያስተኛ የተባለውም ለዚህ ነው። በዚህ አጋጣሚ ነገሩ አንገብግቧችሁ እየተፋለማችሁ ያላችሁትን ስም እየተሰጣችሁ መሰደባችሁን ሳይሆን የተነሳችሁበትን አላም መወንጀላችሁን ሳይሆን እምነታችሁን ይዛችሁ ያላችሁትን ሁሉ ማመስገን እንወዳለን። የመረዋ ሃሳብ እንቅልፍ የነሳቸው ደካሞች መረዋ በሚል ሌላ BLOGS ከፍተው እየጻፉ እንደሆነ ባለፈው ነግረናችሁ ነበር። እባካችሁ ገብታችሁ አንብቡላቸው። ያንን ካላነበባችሁ ድክመታቸውን ልትገነዘቡት አትችሉም። እነዚሁ ግለሰቦች SENEBETE በሚልም ስያሜ ስለሚጽፉ ገብታችሁ እንድታነቡላቸው እንለምናችኋለን እዳሪና አፈር የሚለየው በሽታው ነውና።