እንዴት ሰነበታችሁ ውድ አንባብያን
በዛሬው እለት በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ስርአተ ቅዳሴ የተሳተፋችሁ በመላ የሰማችሁት አዲስ ነገር እንዳለ ይገባናል። ይኸውም የቦርዱ ጸሃፊ ከቅዳሴ በኋላ ተነስተው የተናገሩት በየብሎጉ ላይ የሚጻፈው ስድብ የቤተክርስቲያንን ሽማግሎዎች የሚዘልፈው ስም የሚያጠፋው ሁሉ መቆም እንዳለበትና ይህም በየብሎጉ የተጻፈው የቦርዱ ጽሑፍ እንዳልሆነ የሚያስተባብል ነበር ። ክርስቲያኖች የልባቸው ሲነካና ሲደሰቱ ሃሌ ሉያ ይላሉና መረዋም ሃሌ ሉያ ሊል ይወዳል። እነዚህ በስድብ የተካኑ የቦርዱ ደጋፊ ብሎጎች ያትሙትና ያወጡት የነበረው ብዙው ከቦርዱ ብቻ ሊያገኙ የሚችሉትን ዶክሜንቶች እንደነበረ ያደባባይ ሚስጥር ስለነበረ ዛሬ ሁኔታው ወዳላሰቡበት መንገድ እየሄደባቸው በመሆኑ እራሳቸውን ሊያሸሹ ቢሞክሩ አንደንቅም። እንዴውም ባለፈው በክራውን ፕላዛ ተደርጎ በነበረ የምእመናን ስብሰባ ላይ አንድ ግለሰብ "ይህንን በየብሎጉ የሚጻፉ አሳፋሪ ጽሑፎችን ቦርዱ እስካሁን ያላስተባበለው ከመሆኑን በላይ ጸሃፊዎቹ በጽሑፋቸው እንደ ቦርድ እንጂ እንደ ውጭ ታዛቢ አለመዘገባቸው የቦርዱ አበጃችሁ ባይነት ማስረጃ መሆኑን ተናግረው ነበር።" ተናጋሪው "ባገራችን ሙት ክቡር እንደሆነና አሁን ግን የሙታንን ስም እየጠሩ ለማስፈራሪያ መጠቀማቸው ያሳዘናቸው መሆኑንም "መናገራቸውን እናስታውሳለን። እነሆ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የቦርዱን ጆሮ ስቦ ማስተባበያ መስጠት ላይ ከደረሱ የስብስቡ ሃይል እየሰራ ነው ብለን እያመንን ነው።
በተጨማሪም ቦርዱ በያዝነው ወር በ 17 በጠራው ስብሰባ ላይ ምንም እንኴን አጀንዳ ነው ብለው የሚያቀርቡት ገንዘብን አስመልክቶ ኦዲት አድርገናል ለማለትና ለክስ መከላከያ መሆኑ ቢገባንም። ከቁጥጥራቸው ውጭ ሆኖ የብሎግና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ባባላት ቢነሱ ተናግረናል ለማለትና ባጭር ለመቅጨት የታሰበ እቅድ መሆኑን ለማወቅም ምሑርነትን አልጠየቀንም።
በተጨማሪም ካህኑ የስድብ ብሎግን አስመልክቶ ማውገዛቸውን ስናዳምጥ ያልነው ነገር ቢኖር "ውግዘቱ ባልከፋ። ክርስቲያን ምእመናን ማባረራቸው አግባብ አይደለም የሚለውን ቢያጠቃልል ኖሮ።
ውግዘቱ ባልከፋ የመንፈሳዊ አባት በጭለማ ቤተክርስቲያን እንዲመጡ ተጠርተው በፖሊስ ታጅበው መባረራቸው ኦርቶዶክሳዊ አለመሆኑን ቢያጠቃልል ኖሮ።
ውግዘቱ ባልከፋ አንዱ ካህን ያልወደዱት ካህን መቅደስ አይገባም ማለት ኦርቶዶክሲያዊ እምነታችንም ሆነ መንፈሳዊ መመሪያችን አለመሆኑን ቢያጠቃልል ኖሮ።
ውግዘቱ ባልከፋ ምእመናን በፖሊስ መባረራቸው አግባብ አለመሆኑን ቢያጠቃልል ኖሮ።
ውግዘቱ ባልከፋ ሰባኪዎች የሚያስተምሩት ወንጌል እኛ ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ ያስተማረው ካህን ከመቅደስ እንዳይደርስ ወስነናል የሚለውን የቦርዱን ውሳኔ ትክክል አለመሆን ቢያጠቃልል ኖሮ።
ውግዘቱ ባልከፋ አባላትን እንዴት ማባረር እንችላለን ብሎ ነገር መሸረብ ክርስቲያናዊ አለመሆኑን ቢያጠቃልል ኖሮ።
ውግዘቱ ባልከፋ ቦርዱ የሃይማኖት የበላይ ሊሆን እንደማይችል ቢነገርና ጳጳስን ሊተኩ መነሳታቸው አግባብ አለመሆኑን ቢያጠቃልል ኖሮ።
ስለሆነም አህያውን ፈርተው ዳውላውን እንዳይሆን እያሰብን መረዋ ግን በስድቡ ውስጥ የሌለ በመሆኑ የተባለው እንደማይመለከተን ምስክሮቻችን እናንተ በመሆናችሁ መደጋገም አንፈልግም።
ለማንኛውም ሰላም ለመፍጠር መደማመጥ መወያየት እንጂ እልህና የኔ ብቻ እንደማያዋጣ የተገነዘብን ይመስለናል። በሌላ መልኩ በማስፈራራት ፍቅር፡ በውሸት ሰላም፡ በማባረር ሕብረት፡ በንቀት ክብረት፡ በስድብ አንገት ማስደፋት ይቻላል ብሎ ማሰብ የዋህነት መሆኑን መቀበል አዋቂነት ነው እንላለን።
መረዋ እንደትላንቱ እውነተኛውን መንገድ እየመረጠ መጔዙን ይቀጥላል።
የሰላም ሳምንት ያድርግልን