በዛሬ እለት ተጠርቶ የነበረው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አጠቃላይ ስብሰባ ምልአተ ጉባኤ አልሞላም ተብሎ ስብሰባው መበተኑን ልንነግራችሁ እንወዳለን። መረዋ መቼም ቢሆን ቦርዱ ቅንነት ያለበት የምእመናን ስብሰባ እንዲደረግ ያደርጋል ብሎ ተጠራጥሮ ስለማያውቅ ለሁኔታው አዲስ አልሆንም። እንዴውም ጥርጣሬውን የበለጠ አጠናከረው ማለት እውነት ይሆናል። እንደ ቦርድ አባላቱ አባባል የተመዘገበው የአባላት ቁጥር 328 አካባቢ መሆኑ ሲነገር ለስብሰባው የተገኘው ምእመናን ቁጥር ግን ወደ 65 አካባቢ እንደነበር ስንነግራችሁ ይህ ቁጥር ደግሞ በሆቴል ተሰብስቦ የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ አሳስቦናል ካለው ከሁለት ጊዜ ስብስብ እጅጉን አንሶ መገኘቱን ስናይ የሞራል ድጋፍ ሆኖናል የቦርዱን ደጋፊዎች ደግሞ እንደሚስደነግጥ እርግጠኞች ነን። ለምን ምእመናት አልተገኙም ለሚለው ብዙ ማለት ቢቻልም የቦርዱ አባላት ግን በነደፉት መተዳደሪያ ደንባቸው 2.6 ላይ እንደሚለው (....... if the a meeting is called but fails for lack of a quorum two times, the matter under consideration may be determined by the Board of Trustees in its discretion.......) ስብሰባ ተጠርቶ በምልአተ ጉባኤ አለመሙላት ሁለት ጊዜ ከተበተነ ለውይይት ሊቀርብ የታሰበው ጉዳይ ቦርዱ በመሰለው ይወሰናል..... ትርጉም የራሳችን የሚለውን ተጠቅሞ ለመወሰን የታቀደ እንደሆነ ለመገመት ግን ጊዜ አልወሰደብንም።
በተለያየ ሰዓት እንደ ዳላስ አየር የሚቀያየረው "የአባላት ቁጥር ከመቼው 300 ገባ? ብለው የጠየቁ ተሰብሳቤዎች እንደነበሩ ስንነግራችሁ ከተሰብሳቢዎቹ መሃከል በቦርዱ በተደነገገው መተዳደሪያ ደንብ 9.1 (........... For a purpose reasonabel to the member's interests as a member, any member of the church may:
(i) inspect and copy the records of member's names and address during usual church hours upon resonable written notice to the Secretary;........................ ) እንደ አባል የአባላትን ጥቅም አስመልክቶ ማንም የቤተክርስቲያኑ አባል ምናልባት:
(ለቤተክርስቲያኑ ጸሃፊ በቂ ጊዜ የሚሰጥ ደብዳቤ ጽፎ በማስገባት በስራ ሰዓት የአባላትን ዝርዝር ስምና አድራሻ የመመርመር ብሎም የመገልበጥ መብት ይኖረዋል....... )
የሚለውን በመጥቀስ የአባላት ዝርዝር እንዲያሳዮቸው መጠየቃቸውን ልናወሳችሁ እንወዳለን። ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ቦርዱ ፍርድ ቤት ድረስ የተከራከረበት ጉዳይ በመሆኑ በቀላሉ ሕግ አክብረው ያሳዩናል ብለው ከጠበቁ የዋህነት ያለ ይመስለናል። በተለይም ስብሰባው ሆን ተብሎ የተዘጋጀ እንደነበረ ከብሎጋቸው የተጻፈውን አጀንዳ ማየቱ ጠቃሚ ይመስለናል።
ያም ሆነ ይህ
ተው አትነካኩን አትፍጁን በነገር
እኛም ትኋን በልቶን አልተኛንም ነበር
ያለው ባንሳሳት የወገራ ሰው ነበር መሰል።
ጊዜ ያመጣውን ጊዜ እስኪመልሰው
........... ተጫወተ በሰው። ያለው ዘፋኝ ግን ስሙን ዘነጋነው።
በጉልበት የተነጠቀ መብታችን በሕግ ይከበራል። እኛ ከሕግና ከእምነት ውጭ ጉልበት የለንም።