ለተነገረው ሁሉ መልስ መስጠት፧ ለተባለው ውሸት ሁሉ ማስተባበያ ማቅረብ ፧ አስፈላጊ ባይሆንም አንዳንዱን ግን ዝም ብሎ ማለፍ አላስፈላጊ እየሆነ እያገኘነው ነው። ባለፈው ደጋግመን እንዳልነው ሁሉ በውሸት የተናቀ እንጂ የተከበረ እስካሁን አላየንም። መዋሸት ደግሞ እየበዛ ሲሄድ ህክምና የሚያስፈልገው፧ ጸሎት የሚደረግለት ጠበል የሚሞከርለት ይሆናል። ሲዳማዎች ሲተርቱ "አህያ ከመሞቱ መጎተቱ" ይሉ ነበር። በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተከሰተው ችግር እዚህ የደረሰው በኛ አመለካከት መብት በመደፈሩ የአንባገነንነት ሥራ በመለመዱ ጥቂቶች ብዙሃኑን አፍነን ከቤተክርስቲያን አባረን በራሳችን ደንብ በጥቂቶቻችን ውሳኔ ሕዝቡን እንነዳዋላን ካልሆነም እናባርረዋለን ከሚል ክርስቲያናዊ ካልሆነ የጥቅምና የፖለቲካ መንደርደሪያ በመነሳቱ ነው። ታዲያ ጥሉ የእምነት ሳይሆን የጥቅምና የፖለቲካ የመብት መከበርና ያለመከበር አባላትን የማክበርና የመናቅ ብሎም በቤተክርስቲያኑ ንዋይ ላይ ተመርኩዞ ሌላውን በመጫን ሙሉ ቁጥጥር ለማድረግ የሚደረግ ፍልሚያ መሆኑ ግልጽ ነው። ዛሬ ካህናትን የሚያባርረው ቦርድ በካህናቱ ላይ ሕጸጽ አግኝቶባቸው ሳይሆን የምንለውን አይፈጽሙም የቦርዱን አስተዳደር ትእዛዝ ሳይሆን የሚከተሉት የወንጌሉን ትእዛዝ ነው በሚል እንደሆነ ይታወቃል። ወንድሞቼ ከኢትዮጵያ በ DV ከመጡ ዓመት ያልሞላቸው ባልዬው ብቻ እየሰራ ያለ ገና ያልተቌቌሙ ቤተሰቦች ልጅ ወልደው ለክርስትና ማስነሻ ቦርዱ የወሰነውን $150 መክፈል አንችልም እባካችሁ አስተያየት አድርጉልን ባይሆን ከመጪው ሳምንት ደሞዜ ላይ $50 ለመክፈል ቃል ልግባ ብሎ ባልዬው ካህኑን በለመናቸው መሰረት አባታችን ሄደው ቦርዱን ሲማጸኑ የቦርድ አባላቱ ግን " አንዴ የተወሰነ ነገር ስለሆነ $150 ሳታስከፍል እንዳታነሳ" በመባለቸው ካህኑም በሁኔታው ተበሳጭተው "መልካም ልጆቼ፧ ክርስትና ለማንሳት ወደማያስከፍሉት አባት እመራቸዋለሁ" በማለታቸው ከስራ እንዲባረሩ ያበቃቸውን ወንጀል የዘረዘረው ደብዳቤ ይጠቅሳል። ክሱም "ክርስና በማንሳት ገቢ እንዳናገኝ ክርስትና የሚያስነሱትን ወደ ሌላ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልከሃል" የሚል ነበር ። ይህ ትክክል ነው አይደለም የሚለውን ለናንተ እንተውና፧ የሃይማኖት ጉዳይ ነውን? ለሚለው ግን መረዋ በግል የገንዘብ የንግድ እንጂ የክርስቲያን ስራ አለመሆኑን ያምናል።
እሩቅ ሳንሄድ ባለፈው እሑድ 22 MAY 2010 በመቅደሱ ፊት ቆሞ የፍርድ ቤት ውሳኔ በሚል የቦርዱ ምክትል ሊቀ መንበር ባነበበው ጽሁፍ ላይ "ምስክሮች ከተደመጡ በኋላ ክቡር ፍርድ ቤቱ በቤተክርስቲያኗ ላይ የተደረጉት ማገጃዎች እንዲነሱና በከሳሾች በአቶ ተኮላ መኮንንና በአቶ ጸሐይ ጽድቅ ቤተማርያም የተመሰረተው ክስ ደግሞ ቀደም ሲል በአቶ ዳግም ካሳሁን እና በወ/ሮ ጥሩ አየር ፍስሀ በቤተክርስቲያናችን ላይ የተመሰረተን ክስ ውድቅ ወዳደረገው ወደ 192nd (DISTRICT COURT) ፍርድ ቤት እንዲዘዋወር ( እንዲመለስ ወስኗል)። ይህም የተደረገበት ምክንያት የሁለቱ ክሶች ከሳሾች ስም ዝርዝር ይለያይ እንጂ ክሶቹ ተመሳሳይ ስለሆኑ ነው።" ውድ ምእመናን ማታለል ሌላ ነገር ሆኖ ፍርድ ቤት ያላለውን መናገር ደግሞ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን መረዋ ሊያስጠነቅቃቸው ይወዳለል።
ለነገሩማ በሚመጣው ወር ማለትም በ 6/ 25 / 2010 9:00 AM ላይ በ 101 DISTRICT COURT, JUDGE MARTIN LOWY የቀጠሩት የጠበቃዎች CONFERENCE መኖሩን ብንነግራቸው አቶ ሙሉአለም ይቅርታ ዋሽቻለሁ የሚሉ ይመስላችኌል? መዋሸት መሳሳት ብቻ ሳይሆን ሆን ተብሎ ከተደረገ ደግሞ የሚያስቀጣበት ሰዓት እንዳለም መታወቅ ይኖርበታል። ወንድሞች እድሜ ይስጠን እንጂ ሁሉንም ወደፊት የምናየው ጉዳይ ይመስለናል።
ከላይ እንዳነበባችሁት እኝሁ ምክትል ሊቀመንበራችን "በቤተክርስቲያኗ ላይ የተደረጉት ማገጃዎች እንዲነሱ ፍርድ ቤቱ ............ ወስኗል" ይሉናል። ለነገሩ ገንዘብን አስመልክቶ የነበረው እገዳ ከመነሳቱ በስተቀር ዳኛው የፍርድ ቤቱ እገዳ ተሻሽሏል አሉ እንጂ ተነስቷል አላሉም። ውሳኔው የቦርድ አባላት
1 አማንያንን ከቤተክርስቲያን ለማባረር ለመከልከል እንደማይችሉ
2 DOCUMENTS ማጥፋት እንደማይችሉ
3 ፖሊስ መቅደስ ውስጥ ማስገባት እንደማይችሉ የተወሰነ መሆኑን ለምን ይክዳሉ
መጀመሪያስ ቢሆን የከሳሾች ክስ አታባርሩንም፧ ለጸሎት የሚመጣን መከልከል አትችሉም፧ ፖሊስ መቅደሱ ውስጥ ማስገባት አትችሉም የሚል አልነበረምን?
ወንድሞቼ የቦርድ አባላት ምእመናን ላይ መቀለድ ትችሉ ይሆናል፤ በፍርድ ቤት ወሳኔ ላይ ግን ባትቀልዱ መልካም ነው። ይህ ደግሞ ወደ መጥፎ ሁኔታ ያመራል ብለን እንሠጋለን። ያኔ ማንንም መውቀስ አትችሉም ምላስን ብቻ እንጂ። የፍርድ ቤቱን ውሳኔም ሆነ ም/ ሊቀመንበሩ ያነበቡትን ደብዳቤ የሚከተለውን የድሕረ ገጽ አድራሻ በመጫን ከተለጠፈበት ከቤተክርስቲያኑ ድሕረ ገጽ ማንበብ ትችላላችሁ።
ስለእውነት የተባለውን እንዳለ አቅርቦ ለምእመናን የመንገር ሃላፊነት ያለበት ቦርድ ዛሬም በቤተክርስቲያን አውደ ምሕረት ላይ ቆሞ ያልተባለ መናገሩ ያሳዝናል። ያሳፍራልም። ቀደም ባለው ጊዜ እንደተናገርነው ቤተክርስቲያኑን ወደ ስደት ሲኖዶስ ለመውሰድ እየተመቻቸ፧ ሰባክያን ከዚሁ ከስደት ሲኖዶስ እየተጋበዙ እየመጡ ለመሆኑ በተከታታይ ያያችሁት ጉዳይ ነው። ሰባኪዎቹም ለይስሙላም ሆነ ከልብ የቦርድ አባላት ገንዘብ ላይ ያላቸውን አመለካከት እንዲቀይሩ አማንያን የሌለው ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ሊባል እንደማይችል መናገራቸውንም የሰማነው ጉዳይ ነው። አንድ ነገር እዚህ ላይ ለመናገር የምንወደው ለጥቅም የተነሳ ማንም ግለሰብ ከማንም ጋር ሊስማማ እንደማይችል ነው።
ይህንን የቤተክርስቲያን ችግር በሰላም ለመፍታት የተነሱትን ግለሰቦች ስም የማጥፋት ዘመቻም ወደ አሳፋሪ ሁኔታ እየሄደ ያለ ይመስለናል። ማንም የማንንም ሥም ማጥፋት ይችላል የሚል አመለካከት ያላቸው ግለሰቦች ሁኔታዎች ወደ መጥፎ እየሄዱ ነውና ቢያስቡበት መልካም ነው።
በተረፈ ባለፈው ወር ተደርጎ በነበረው የምእመናን ስብሰባ የተመረጡ የኮሚቴ አባላት ቦርዱ ሊያነጋግራቸው ፈቃደኛ ባለመሆኑ የቦርዱን ውሳኔ ትክክል አለመሆን ተቀብለው ያወጡትን መግለጫ መረዋ ከዚህ በታች ያቀርባል።
መልካሙን ያሰማን
የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመፍትሄ ኮሚቴUNITED ST. MICHAEL CHURCH RESOLUTION COMMITTEE
4509 Beaus Way, Garland, TX 75043 (972) 226-172805-23-10
ውድ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምእመናን።
በ 5-8-10 ባደረግነው ስብሰባ ላይ በሰጣችሁን ኃላፊነትና ውክልና የአስተዳደር ቦርዱን ለማነጋገር ሞክረን ሳይሳካልን ቀርቷል። እስክ 5-18-10 በደብዳቤ መልስ እንዲሰጡን የጊዜ ገደብ ስንሰጣቸው፣ በቃል ደግሞ ሁለት ቀን ጨምረንላቸው፣ በስልክም፣ በግንባር በማነጋገርም የምእመናኑን ጥያቄ ለማቅረብ ተማፅነን ነበር። ይህ እንዲህ እንዳለ፣ በ 5-23-10 የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ስብሰባ ከመጥራታችን በፊት፣ በ 5-22-10 ከዚህ ጋር አያይዘን የምናቀርበውን የመልስ ደብዳቤ ከቦርዱ ደረሰን።
ለአስተዳደር ቦርዱ ግልፅ ውይይት ፍቃደኝነት ለመስጠት ብለን የስብሰባውን አቋም የሚገልጽ መግለጫ አዘግይተን ዛሬ ከዚህ መሸኛ ደብዳቤ ጋር ለናንተ በትህትና እናቀርባለን።
በሚቀጥሉት ሁለት ወይንም ሶስት ሳምንታት ኮሚቴው እስከ አሁን የወሰደውን ተግባር የሚገመግምና ለወደፊቱ በምን ዓይነት መልኩ ችግሩን ለማስወገድ የሚቻልበት እቅድ ለመንደፍ አጠቃላይ ሁሉን አቀፍ የሆነ ስብሰባ እንጠራለን። ቦታውንና ጊዜውን ቀደም ብለን እናስታውቃችኋለን።
1ኛ፡ አቶ ተፈራወርቅ አሰፋ ሊቀመንበር
2ኛ፡ አቶ ግርማቸው አድማሴ ም/ሊቀመንበር
3ኛ፡ አቶ ብርሃነማርቆስ ታደሰ ፀሐፊ
4ኛ፡ አቶ ሳሙኤል ደንቢ ፈረደ ቃለ ጉባኤና የEቅድ ሥራ
5ኛ፡ ዲ/ን አርአያ ኃይለመስቀል የኃይማኖት Aማካሪ
6ኛ: አቶ ንጉሤ ጀንበሩ የፍትሕና የሕግ Aማካሪ
7ኛ፡ አቶ ቢራቱ ዎዳ የፍትሕና የሕግ አማካሪ
8ኛ፡ አቶ ደመላሽ ደበበ የሕዝብ ግንኙነት
9ኛ፡ ወ/ሮ በየነች መኮንን የሕዝብ ግንኙነት
የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመፍትሄ
UNITED ST. MICHAEL CHURCH RESOLUTION COMMITTEE
4509 Beaus Way, Garland, TX 75043 (972) 226-1728
tadesse1@aol.com
በስመ አብ፣ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱስ፣ አሀዱ Aምላክ Aሜን።
5-13-10
ለተከበራችሁ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የቦርድ አባላት።
የአክብሮት መንፈሳዊ ሰላምታችንን እናቀርባለን።
ቤተክርስቲያናችን ውስጥ በተፈጠረው ችግር በግምት ቁጥራቸው ወደ 200 የሚጠጉ ምእመናን ግንቦት 1 ቀን 2002 ዓም (May 8, 2010) ተሰብስበው ከተወያዩ በኋላ ከቤተ ክርስቲያኑ የቦርድ አባላት ጋር ተነጋግሮ የደረሰበትን ውጤት በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የሚያቀርብለትን ኮሚቴ በመሰየም ጉዳዩን እንድንከታተል በመጨረሻው ስማችን የተዘረዘረውን መርጦ ተለያይቷል።
የቤተ ክርስቲያኑን ችግር በቦርድ አባላት ላይ ብቻ ጥሎ በጎን ሆኖ መመልከት ክርስቲያናዊ አሰራር ያለመሆኑን ያመነበት ጉባኤ ሲልከን እኛም አቅማችን የፈቀደውን ያህል ለመርዳት ፈቃደኞች መሆናችንን አረጋግጠናል።
ስለዚህ፤ ምንም እንኳን ለችግሩ ከማንም የበለጠ የቦርዱ አባላት ኃላፊነትና ግዴታ መሆኑን ብንረዳም እኛም አደራ ለጣለብን ምእመናን በሰጠን የጊዜ ገደብ ውስጥ መልስ ለመስጠት እንድንችል ከግንቦት 11 ቀን 2002 ዓም (May 18, 2010) በፊት በጋራ ለመሰባሰብ ቀንና ሰዓቱ ቀደም ብሎ እንዲገለጽልን እናሳስባለን።
ቅዱስ ሚካኤል ሰላሙን ይስጠን።
አባላት፡ ተፈራወርቅ አሰፋ የኮሚቴ ሰብሳቢ
ግርማቸው አድማሴ
ንጉሴ ጀንበሩ
ብርሃነማርቆስ ታደሰ
ደመላሽ ደበበ
በየነች መኮንን
ዲ/ን አርአያ ኃይለመስቀል
ቢራቱ ዎዳ
ሳሙኤል ደንቢ ፈረጃ
የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመፍትሄ
UNITED ST. MICHAEL CHURCH RESOLUTION COMMITTEE
4509 Beaus Way, Garland, TX 75043 (972) 226-1728
tadesse1@aol.com
በስመ አብ፣ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱስ፣ አሀዱ አምላክ Aሜን።
5-11-10
መግለጫ
ቅዳሜ አንደ አውሮፓ ዘመን Aቆጣጠር ግንቦት 8 ቀን 2010 (አንደ Iትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ግንቦት 1 ቀን 2002), በደብል ትሪ ሆቴል ሪቻርድሰን፡ ቴክሳስ በግምት ወደ 200 የሚጠጉ የቅዱስ ሚካኤል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታይ ምእመናን፣ በቅርቡ በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ክርስቲያናዊ እምነትን የማያንፀባርቅ በAማኝ ወጣቶች፣ እናቶችና አባቶች ላይ የደረሰውን አሳፋሪ ተግባር በመቃወም ቤተክርስቲያናችን አሁን ካለችበት አስከፊ ተግባር ተላቃ የአማኞች ቤትነቷን ለማረጋገጥ የምንችልበትን በጋራ ለመሻት የተደረገ ስብሰባ ነበር።
ይህ ስብሰባ ወይንም ጉባኤ ምእመናኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነፃና ክርስቲያናዊ ገንቢ ሃሳብ የሰጡበት ሲሆን፣ ለወደፊት የአባላት መብት ተከብሮ ሰላምና ፍቅር ተመስርቶ ሕዝቡ ኃይማኖቱንና ባህሉን ተከትሎ አንዴት አንደሚኖርም በሰፊው ተወያይቷል።
ይህንንም ሃሳብ ከግብ ለማድረስ በተለያየ መልክ ተደራጅተው ያሉ ቡድኖችና ግለሰቦች ለሰላም፤ ለAንድነትና ለኃይማኖት መስፋፋት ተገቢውን ሚና በመጫወት ድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ጉባኤው አሳስቧል።
በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ የስብሰባው ታዳሚ መሠረታዊ የሆኑትን የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ችግሮች ካጤነ በኋላ በመፍትሔ ሃሳብ ላይ በማተኮር የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል።
ተሰብሳቢው የሚከተሉትን የAቋም ውሳኔዎች አሳልፎ ለተመረጠው ኮሚቴ ሙሉ የውክልና መብት ሰጥቶታል።
1ኛ. ሁለት መሠረታዊ ሂደቶችን የተከተለ መፍትሔ
ሀ. ልዩነት ከመፈጠሩ በፊት የነበረው የAባላት መብት አንዲከበር
ለ. ሁሉን አቀፍ የሆነ ጊዜአዊ የአመራር ኮሚቴ አሁን ባለው ምትክ Eዲቋቋም
2ኛ. የአቋም መግለጫውም፤
ቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊ እረፍት የምናገኝበት፤ እምነታችንን የምናጠነክርበት፣ ባህላችንን ለልጆቻችን የምናስተምርበት፤ መፈቃቀርን፣ መከባበርን፣ መረዳዳትን የምናሳይበት ቦታ ሆና ቆይታ ነበር። በተደጋጋሚ በሽማግሌዎች ችግሮችን ለመፍታት ተሞክሮ የአስተዳደር ቦርድ ፈቃደኛ ባለመሆኑ መፍትሄ ለማግኘት አልተቻለም። በአሁኑ ወቅት ግን የቤተክርስቲያኑ Aካሄድ ያሳሰባቸው ጥያቄ አለን ሲሉ በፖሊስ የሚወገዱበት፣ አባል ለመሆን የማመልከቻ ተከፍሎ ቦርድ ከፈቀደ ብቻ መቀላቀል የሚቻልበት፤ ክርስቲያን ሆኖ ለመጠመቅ እንኳን ክፍያ የሚጠየቅበት ሆኗል።
ሀ. እኛ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ምእመናን፣ በቤተክርስቲያናችን ከእምነታችን ውጭ በአስተዳደር ቦርዱ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እጅጉን ያሳዘነን ሲሆን ለዚህም ቦርዱ ይቅርታ እንዲጠይቅ።
ለ. የሚደረገው የአባላትን ቁጥር በዘዴ የመቀነስ፣ ቦርዱ ያልተስማማውን የማባረር ሁኔታዎች በአስቸኳይ ቆመው ቤተክርስቲያናችንን ወደነበረበት ይመለስና ፈቃደኛ የሆነው ሁሉ አባል የሚሆንበት ሁኔታ እንዲመቻች።
ሐ. ሳንወያይበት የተቀየረው መተዳደሪያ ደንብ ወደነበረበት ተመልሶ፣ ሁሉን አቀፍ ውይይት ተደርጎ ሁሉም የሚያምንበት ደንብ እንዲሆን ለማድረግ ሁኔታዎች እንዲመቻቹና አዲስ ምርጫ በአስቸኳይ እንዲደረግ።
የተሰብሳቢውን ሃሳብ ተረድቶ ወደ መፍትሔው ተግባራዊነት የሚመራ ኮሚቴ በድምፅ ብልጫ የሚከተሉትን የኮሚቴ አባላትን መስርቷል።
ቅዱስ ሚካኤል ሰላሙን ይስጠን። አሜን።
1ኛ፡ አቶ ተፈራወርቅ አሰፋ ሊቀመንበር
2ኛ፡ አቶ ግርማቸው አድማሴ ም/ሊቀመንበር
3ኛ፡ አቶ ብርሃነማርቆስ ታደሰ ፀሐፊ
4ኛ፡ አቶ ሳሙኤል ደንቢ ፈረጃ ቃለ ጉባኤና የእቅድ ሥራ
5ኛ፡ ዲ/ን አርአያ ኃይለመስቀል የኃይማኖት አማካሪ
6ኛ፡ አቶ ንጉሤ ጀንበሩ የፍትሕና የሕግ Aማካሪ
7ኛ፡ አቶ ቢራቱ ዎዳ የፍትሕና የሕግ አማካሪ
8ኛ፡ አቶ ደመላሽ ደበበ የሕዝብ ግንኙነት
9ኛ፡ ወ/ሮ በየነች መኮንን የሕዝብ ግንኙነት 2