ሰሞኑን ከአንባብያን ለደረሱንን የድጋፍ መግለጫዎች ሁሉ እያመሰገንን ለተሰደቡት ብርታትን፣ ለተወነጀሉት ጽናትን፣ ይስጣቸው እንላለን። ብዙዎቻችሁ በመረዋ ላይ መግለጫ ለመለጠፍ ጠይቃችሁን ነበር። ነገር ግን የመረዋ አነሳስም ሆነ ጉዞ የፖለቲካ ስንክሳር ለማራመድ ባለመሆኑና የአንባቢዎቻችንን ፍላጎትም በመገንዘብ ከአጀማመሩ ያ እንዳይሆን አቋም የወሰድንበት ጉዳይ ስለሆነ ጥያቄአችሁን ባለመቀበላችን ይቅርታ እንጠይቃለን። ያም ቢሆን ለተሰደቡ ደጋፊዎቻችን ያለንን አድናቆት እየገለጽን የተሰደባችሁትና በሃሰት የተወነጀላችሁት እውነት በመናገራችሁ፤ ለመብት በመቆ ማችሁ በመሆኑ ልትኮሩ እንጂ ልታፍሩ አይገባችሁም እንላለን። እውነት የሆነውን ሁሉ ብንጽፍ ደግሞ በሃሰት የተሰለፉትን ከስራ ማፈናቀል ይሆናል። ለመብት የቆሙ ደግሞ ጠንካሮች እንደሆኑ ማስረጃ የሚያስፈልግ አይሆንም። በየቀኑ የምታሳዩን እውነታ ነውና። እናንተን እያየን በየቀኑ እየተማርን ነው። መረዋ እውነትን ይዘው ከቆሙት ጎን በመቆሙ አሁንም ደስተኛ ነው። እውነት ለማሸነፉ ደግሞ ጥርጥር የለንም።
ዛሬ ከመረዋ ከሰነበቱ እትሞች አለፍ አለፍ እያልን ልናስነብባችሁ እንወዳለን።ያለፈውን በማየት መጭውን ዳግም እንድናቃኝ ይረዳናልና።
ከመረዋ ቁጥር ፩
11/26/09
"አሁን ለምን ሽማግሌዎች ሊያስታርቁ ተነሱ" ብሎ መተቸትና መሰናክል ለመፍጠር መነሳት ግን ሌላ ስህተት ነው ብለን ደግሞ እናምናለን። በፍርድ ቤት ትእዛዝ ችግራችን ይፈታል ብሎ የሚያምን ካለ የዋህ ነው ብሎ መናገር ማስፈራት የለበትም። ፍርድ ቤት በሚሰጠው ብያኔ ፍቅር አይመጣም አንድነት አይፈጠርም። ይህ ሊሆን የሚችለው የተለያየ ሃሳብ ይዞ የሚከራከረው ቡድን ተቀምጦ መነጋገር ሲችል ብቻ ነው። ክስ የመሰረቱትን ለምን ክስ መሰረቱ ብሎ መኮነን ደግሞ ሲደረግ የነበረውን መካድ ይህንን ባያደርጉ ኖሮ ዛሬ እንደዚህ ለመናገር የማንችልበት ሁኔታ ላይ እንሆን እንደነበር አለመቀበል ይሆናል። የቤተክርስቲያን ገንዘብ ስላለ ከሳሾቹን ገንዘባቸውን አስጨርሰን እንዲሸነፉ እናደርጋለን የሚሉት የቤተክርስቲያኑ ተመራጮች ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር የተመኩበት ገንዘብ ከምእመናን የተዋጣ መሆኑን ነው። ምእመኑ ካልደገፈ የገንዘቡ ቌት እንደሚሟጠጥ ከሳሾችንም ከአሁኑ በበለጠ እየደጎሙ እየደገፉ እንዲቀጥሉ ሊያበረታቱ እንደሚችሉ ማሰብም የተገባ ነው። ከሳሶችም ሆኑ የቤተክርስቲያኑ ተመራጮች ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር ያለ ምእመን ድጋፍ የትም ሊሄዱ እንደማይሄችሉ ነው። በተናጠል ቤተክርስቲያን አይገነባምና። ተሰዳደብን፡ ተካሰስን፡ ተወነጃጅለን አሁን ደግሞ ወደ አንድነት ለመምጣት ምን አስተዋጽኦ እናድርግ ብሎ መነሳት ክርስቲያናዊ ነውና ሁላችንም በተናጠል እራሳችንን ጠይቀን ለሰላም እንነሳ። እከሌን ብናገረው እንጣላለን ከመሃበር ያባርሩኛል ያልሆንኩትን ስም ይሰጡኛል፡ ዝምድናችን ይፈርሳል ጔደኝነታችን ይቀራል በቡድን ያጠቁኛል ብሎ በመፍራት ለእውነትና ለመብት አለመነሳት ደግሞ በሕሊና ማስጠየቅ ይኖርበታል እንላለን። ስለሆነም ለሁላችሁም ዛሬ ጥያቄዎች ማቅረብ እንወዳለን። በግል ምን እያደረግን ነው? ሰለኛ ሌሎች እስከመቼ ይወስናሉ?መብትና እምነት፡ ሕግና አምልኮን መለየት የምንችለው መቼ ነው?
ወንድሞችና እህቶች ይህ ከዚህ በላይ ያነበባችሁት መረዋ የመጀመሪያ እትምቱን ሲያወጣ የዘገበው ነው። እኛ ዛሬ ስናነበው የዛሬ ጽሑፍ መሰለን እናንተስ?
ከመረዋ ቁጥር ፵፬ ደግሞ እስቲ እናንብብ
10/06/10
ይህ ክስ አባላትን ማባረር ከጀመሩ በኋላ የተመሰረት መብትን ለማስከበር የተመሰረት ክስ መሆኑም ለሁላችንም ግልጽ ነው።
ስለሆነም በነገው እለት ምንም ተፈጠረ ምን
መተዳደሪያ ደንቡ ወደነበረበት ካልተመለሰ
የተባረሩ አባላት ካልተመለሱ
የአባላት ክፍያ ወደነበረበት ካልተመለሰ
አንዱ ልጅ ሌላው እንጀራ ልጅ መሆኑ ካልቀረ
የአባላት መብት ካልተጠበቀ
ፖለቲከኞች ከቤተክርስቲያን ውስጥ ፖለቲካቸውን ካላቆሙ
የምእመናንን ጥቅም አስከባሪ ቦርድ እስካልተቋቋመ
ብሎም
ባለፈው እንዳደረጉት ቦርዱ በመሰብሰቢያ አዳራሻቸው እነ አቶ ሃይሉ እጅጉን ጠርተው እየተሳደቡት ክስ ከመሰረቱት ውስጥ ነህና ካላረፍክ እንከስሃለን የክስ አጋሮችህንም አብረን ለፍርድ እናቆማለን እንዳሉት በተናጠል ማስፈራራት እስካላቆሙ ድረስ
በቦርዱ ብሎግ መሳደባቸውን እስካልገቱ ድረስ
መታገላችንን አናቆምም
አንዳዴ ትላንት የተጻፉ ጽሑፎች ዛሬም እንዳዲስ የዛሬውን የሚተርኩ ይመስላሉ።

ይህንን ዳግም ልናስነብባችሁ የተነሳነው መረዋ ትላንትና የዘገበው ዛሬም እውነት መሆኑን ለአንባቢዎቻችን ለማስይረዳል ይጠቅማል ብለን በማሰብ ነው። ከሳሾች በስድብ አልደነበሩም። በማስፈራራት አልተበተኑም። በውሸት ወሬ አልበረገጉም። የሚንበረከኩት ለፍቅር፤ ለእውነት ለመሆኑ ደግሞ ጥርጥር የለንም። ይህንንም በተደጋጋሚ ሊያወያዩ ለተነሱ አዛውንቶች ሁሉ ያረጋገጡት ለመሆኑ መስካሪዎቹ አዛውንቶቹ ይሆናሉ እንላለን። በመወያየት የሚያምኑት የከሳሽ ወገኖች የሚያሸንፉትም ሆነ የሚሸነፉት በውይይት ብቻ እንደሆነ ያምናሉ። ለካሳ አልተነሱም፡ ለመብት መከበር እንጂ። አማንያንን ለመበታተን አልተነሱም የተበተነውን ለመሰብሰብ እንጂ። ለመከፋፈል አልተነሱም አንድነትን ለመፍጠር እንጂ። ይህ ደግሞ ሊመጣ የሚችለው በመነጋገር ብቻ እንደሆነ ጥርጣሬ የላቸውም። የመነጋገር በሩ ከተዘጋ ግን አማራጩ አንድ ብቻ ይሆናል። መብትን በፍርድ ቤት ማስከበር ብቻ። ይህ ሳይሆን ክሱን ተው ብሎ መጠየቅ ግን "ታንክ ከያዘ ጠላት ፊት ቡጢ ይዛችሁ ቅረቡ" እንደ ማለት ይመስላል።
ከሳሽ የምንላቸው ግለሰቦች ገንዘባቸውንና ጊዜአቸውን የማባከን ሱስ የለባቸውም። ለመብታቸው ትግል ባይጀምሩ ኖሮ ግን እንደማይሰደቡም ያውቃሉ። እንደ ቦርድ አባላት በ ሺ የሚቆጠር እንደፈለጉት የሚያጠፉት የባንክ ደብተርም የላቸውም። ከደጋፊዎች የሚሰበሰብ የድጋፍ መዋጮ እንጂ። ታዲያ የሚያገኙት ምንድነው ለሚሉ ግለሰቦች መልሱ መብታቸውን ማስከበ ይሆናል። ትላንት ፍርድ ቤት ባይሄዱ ኖሮ 81 የቤተክርስቲያን አባላት ከቤተክርስቲያን በፖሊስ ተባረው ነበር። ፍርድ ቤት ባይሄዱ ኖሮ ቤተክርስቲያን ለአምልኮ እንኳን እንዳይደርሱ ተከልክለው ነበር። ይህንን እንዳያደርጉ በፍርድ ቤት ሲታዘዙ አይደለም እንዴ የቦርድ አባላት ይግባኝ ብለው ዛሬም የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በጉጉት የሚጠብቁት። ለምን እንደባበቃለን። ከሳሾች አባላት አይደሉም አናውቃቸውም ያሉት የቦርድ አባላት አይደሉምን?ለምን እንደባበቃለን። ከሳሾች የጀርመን ናዚ ፋሽስት የወጣት አባላት አይነት ናቸው ብለው ለፍርድ ቤት ቃላቸውን የሰጡት አሁንም የቦርዱ አባላት አይደሉምን?
ለምን እንደብቃለን? ከሳሾች ልጆች እንደሌላቸው ሁሉ፣ ሕጻናቶችን ከጫማ ጋር ከፎቅ ላይ ወደ መሬት ሊወረውሩ ነበር ተብለው በፍርድቤት አልተወነጀሉምን? ይኸ ልክ አይደለም ያሉ ሁሉ ከሳሾችን ለመርዳት ቃል እንዲገቡ አደረጋቸው እንጂ እነሱ እንዳሰቡት ደጋፊ አላሳጣቸውም። የቦርድ ደጋፊ ነን ባይ ጦማርም "they are inocent till they are prooven gilty" ሲሉ አላዳመጥንም። ብቻ ሆድ ይፍጀው። አገሩ ደግሞ የዲሞክራሲና የመብት አገር የሕግ የበላይነት ያለበት ምድር መሆኑ እረዳን።
ይህንን በዚህ እናጣፋና ወደ ሌላ ጉዳይ እንግባ
ከዚህ በፊት በደረሰው በወጣቱ ሐዘን ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፎ የነበረው የተባበሩት የሰላምና ፍትሕ አስተባባሪ ኮሚቴ አጠቃላይ ስብሰባ እሁድ
January 23, 2011 ከቀኑ 1:00 PM
በ DREAMZ CLUB
እንደሚደረግ የደረሰን ማሳሰቢያ ይገልጻል። በወቅቱ ከስብሰባው በፊት ምሳ እንደሚኖርም ለመረዳት ችለናል።
ሳንረሳው መጥቀስ የምንወደው ሌላ ጉዳይ አለ። ሰሞኑን በሌላው ጦማር እንደ ተለመደው በአቶ ተኮላ መኮንን ላይ የተሰነዘረውን የሃሰት ውንጀላ አስመልክቶ የተጻፉ መልሶች
በ WWW.ASSIMBA.COM
እየተለጠፉ እንደሆነ መገንዘባችንን ለአንባቢዎቻችን እንገልጻለን።
የከርሞ ሰው ይበለን።