Tuesday, June 29, 2010

የቅዳሜው ስብሰባ በስምምነት ተፈጸም ቁጥር ፴፭

ከስተሻል ጠቁረሻል ሆነ ጥያቄአቸው
ሽል አለ  በሆዴ  እንዴት ላሳያቸው።

ብላ  የዘፈነችው ማ ነበረች? ዘመኑ ገፋና  እኛም እየዘነጋን መጣን ማለታችን  ነው። ዘፋኟ ይህንን  ያለችው የወደደችው መኖሩን ለመጠቆም  ነበር። በቅዳሜው ስብሰባ  ላይ ግን ምን ብናደርግ ይሻላል? ለሚለው መልስ ሊፈልጉ የተላኩት 9 የከተማችን አዛውንቶች በቤተክርስቲያኑ የቦርድ ተመራጮች እንቢታ አዝነው መመለሳቸውን ለተሰበሰበው ምእመን ሲያቀርቡ ያላዘነ  አንድም ሰው አልነበረም። "ቤተክርስቲያንን መክሰስ አግባብ አይደለም  ብለን ስንቃወም ከርመናል አሁን ግን ለምን ከሳሾች ወደ ሕግ እንደሄዱ ሙሉ ለሙሉ ገብቶናል" ያሉት ሁለት ሰዎስት ግለሰቦች ሳይሆኑ  ስብሰባውን የተካፈለው በመላ  እንደ ነበር ስንነግራችሁ የሕዝቡ ቆራጥነት እኛንም  አስፈራርቶን   እንደነበር መናገር ደግሞ  እውነተኛ ምስክርነት ነው። "ይህ ክስ ባይመሰረት ኖር ከነቤተሰቦቼ  ከቤተክርስቲያን የምባረረው አንዱ ግለሰብ እኔ  ነበርኩ"  ያሉት አዛውንት "ድሮ  ቤተክርስቲያናችን የነፍሰ ገዳይ እንኴን ሳይቀር የአማልዱኝ ቦታ እንደነበረ ጠቁመው "እነሆኝ ዛሬ ቤተክርስቲያናችን አማንያንን ለማባረር ሲሯሯጥ ማየትን የመሰል የሚዘገንን ነገር ግን አለመኖሩን"  ተናግራዋል።

"ተወያይቶ በሃሳብ መለያየት አንድ ነገር ነው አንወያይም ማለት ግን ያውም በዚህ ዲሞክራሲ በሰፈነበት ሃገር ኋላ ቀርነት ነው" ያሉት የኮሚቴው ተወካይ እሳቸውም እንደ ሌሎች ተናጋሪዎቹ ሁሉ ክሱን አስመልክቶ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደነበራቸው ጠቅሰው አሁን ግን ለቤተክርስቲያኑ ሰላም ያለው አማራጭ ሕግ ብቻ መሆኑን መቀበላቸውን አስምረውበታል። 

የኮሚቴው ወሳኔና አጠቃላይ ገለጻ ከመነበቡም ባሻገር የዘገባው ግልባጭ ለተሰብሳቢዎቹ ታድሏል። ክርስቲያኖች ነንና አሁንም እንዲሰሙን ከመጸለይ ማቆም የለብንም ያሉት መምህር ባህታውያን የሚይዙት የብረት ምርኩዝ ካናቱ መስቀል ከስሩ ደግሞ  አንካሴ  መሆኑን አትዘንጉ ብለው ምናልባት አንካሴው ለአውሬ  መከላከያ ሳይሆን አይቀርም ብለን ሲያስተምሩ ተሰብሳቢውን አስቀውታል።

በእለቱ የተደረገው ስብሰባ ስነስርአት የታየበት መከባበር የሰፈነበት እንደነበረ የተናገሩት የስብሰባው ሰብሳቢ እንደዚህ አይነት ስብሰባ  እኮ ነው የናፈቀን ብለዋል። ስብሰባውን የተካፈለው በሙሉ ከሕግ ውጭ ያለው አማራጭ የጠበበ  መሆኑን ተቀብሎ ያለው ኮሚቴ  እንዳለ  ሆኖ ከሳሾችን የሚደግፍ ኮሚቴ  አቌቁሞ ስራውን እንዲቀጥል ባንድ ቃል ከተስማማና ከወሰነ  በኋላ የስብሰባው ፍጻሜ  ሆኗል። በስብሰባው ላይ ለመጀመሪያ  ጊዜ የተገኙ አባቶች በምእመናኑ የስነስርዓት ስብሰባ የተገረሙ መሆኑንና ስለዚህ ስብስብ የተነገራቸውና ዛሬ  ያዩት ሰማይና  ምድር መሆኑን ሲናገሩም ተደምጠዋል። የሃሰት ወሬ  ማናፈስ የማይሰለቻቸው ግለሰቦች ነገ ሌላ  በሬ  ወለደ ወሬ ይዘው ቢመጡ መደናገጥ አይኖርብንም በማለት ያሳሰቡ ከመኖራቸውም በላይ ብዙ  ግለሰቦች ሕብረቱ ወደ አንድ አመለካከት መምጣቱ ለችግራችን መፍትሄ ለመስጠት ይረዳል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። የስብሰባው ውሳኔ  ቅጂ ለተሰብሳቢዎቹ እንደሚታደል ተነግሮ  የነበሩው ኮሚቴ  አባላት እንዳሉ ሃላፊነቱን ወስደው እንዲቀጥሉ ተስማምቶ ስብሰባው በትምሕርትና  በጸሎት ተደምድሟል። 

መረዋም በስብሰባው አካሄድ የተደሰተ  መሆኑን እየገለጸ ስብሰባው ላይ ያልነበሩ ግለሰቦች በቀጣዩ የስራ  ክፍፍል በፈቃደኝነት እየተሳተፉ የቤተክርስቲያኑን ሰላም በፍጥነት የምናስከብርበትን መንገድ እንዲያጣድፉ ጥሪ ያደርል። በተጨማሪም ይህንን ስብሰባ እዚህ ውሳኔ  ላይ ያደረሱትን የኮሚቴ  አባላት መረዋ  ባንባቢዎቹ ስም ከፍ ያለ  ምስጋና ያቀርባል።

ከተባበርን ምንም አይነት ሃይል አያቆመንም። ክርስቲያን ፈጣሪውን እንጂ ሌላ  የሚፈራው ሃይል አይኖረውም።

መልካም ሳምንት።

Saturday, June 26, 2010

መስቀል እኮ ለጌጥም ይደረጋል ቁጥር ፴፬

"To get something you never had, you have to do something you never did"

"ያልነበረህን  ለማግኘት አድርገህ የማታውቀውን ማድረግ ይኖርብሃል" ትርጉሙ የመረዋ።

ይህንን  ጥቅስ የላከልን አንድ በቅርብ የምናውቀው ጔደኛችን ነበር። እኛም ለሌላ  ጔደኛችን  አሳየነው። በጥቅሱ አልተስማማም። "በየቀኑ ሎተሪ የሚገዛን ግለሰብ ሎተሪ  ሲደርሰው ምን  ልትሉት ነው?" አለን። ይህንን  ያቀረብንላችሁ በአባባል እንኴ ልዩነት ሊኖር እንደሚችል ለመጠቆም ያክል ነው። ፈረንጆች ግማሽ ብርጭቆ የሞላ  ውሃ፤ ግማሽ ብርጭቆ የጎደለ ውሃ  እንደሚሉት አይነት። 

እንዴት ከረማችሁ።

ለተሰደባችሁ ጥናቱን: ለተወነጀላችሁ ጥንካሬን፤ ይስጣችሁ ስንል ከዚያ  ማዶ  ያሉ የቦርዱ ጋሻ ጃግሬዎች ስልታቸውን አስፋፍተው ዛሬ  የተጋባን ሊያፋቱ፤ የተከበረውን ሊያዋርዱ፤ የተናቀውን ሊያነግሱ፤ መነሳታቸውን አይታችኋል። እነሱ በወረዱበት አለመውረዳችን  አሳስቧቸው ከተቀመጡበት የቤተክርስቲያን ደጀሰላም ማ ማንን ተኛ? ማ  ከማጋር ተቃቀፈ ማለት ጀምረዋል። "እኛ ድሮ የምናውቀው ጭድ ላይ የተኛ ጎረምሳ  የፍም እንጨት አይንተራስም"  ሲባል ነበር። እነዚህ ግን ቤንዚንና  ክብሪትም ይዘው ሲጫወቱ እያስተዋልን ነው። ስለነሱ ትዳር መናገር ብንጀምር  ተደብቀው እንደሚከርሙ እያወቁ፤ ለምን ይህንን ደካማና አሳፋሪ መንገድ መረጡ?  ብለን ስንጠይቅ ያገኘነው መልስ እየተሸነፉ ነው። ያላቸውን ጥይት ተኩሰው ጨርሰው ዛሬ አጠገባቸው ያለውን ጭራሮ፤ ጉቶ፤ ኩበት ጭምር እየወረወሩ ነው የሚል ሆኖ አገኘነው። "አስፈራራናቸው"  እንደሚሉም  ሰምተናል። ከገባቸው መፍራትም ያዋቂ የነቃ  ሰው መሆኑን እንናገር። እኛ እነሱ ስለዘቀጡ አንዘቅጥም። ከወገብ በታች ባለ ነገር የሚመሰጥ ከቀበቶ  በላይ ባዶ  የሆነ  ብቻ  ነውና።

የተሳዳቢዎቹንና  የተሰደቡትን  ግለሰቦች  ሚዛን ላይ በማስቀመጥ ማ ምን እንደሆነ መመዘን ደግሞ  የያንዳንዱ አማኝ ግዴታ  መሆን ይኖርበታል። ውድ ወንድሞችና  እህቶች። የቦርዱ ደጋፊ ነን ባዬች የቀራቸውና  የሚነግሩን የጭን ወሬ  ከሆነ  እንኴን ደስ ያለን ተሸንፈዋል።

የቦርዱ ደጋፊዎች የሚያዜሙት

ልጅቷ ነች ብዬ እናቷን ሳምኴቸው .......... ከሆነ እንኴን ደስ ያላችሁ  እራሳቸውን እየገደሉ ነው :: 

ነገርን ነገር ያመጣዋልና  የቆየ ተረት ታወሰን። አንድ ግለሰብ የተቀባበለ ጠብመንጃ  ይዞ ይሮጣል ሌላው ከኋላ ዱላውን እየወዘወዘ  "ቁም የት ተሄዳለህ"  እያለ  ያሳድደዋል። ይህንን የተመለከተ ሌላ ተመልካች ባለ ጠብመንጃውን "ወንድሜ  ለምን ትሸሻለህ?"  ቢለው ባለ ጠብመንጃው "ይቅርታ  አድርግልኝ እሬስ እየተከተለኝ ነው"  አለ ይሉ ነበር።

እናም
ካሁን በኋላ  እነዚህ ለልጆቻችን አርአያ  ይሆናሉ ብለን አንጠብቅም።
እነዚህ ልጆቻችንን  አያስተምሩም።
እነዚህ ስለሃይማኖት አይሰብኩንም።
እነዚህ ስለግብረገብ ገለጻ አይሰጡንም።
እነዚህ ስለፖለቲካ  አይቀሰቅሱንም።

አቶ ሃይሉ ነው ተሳዳቢዎቹ የቤተክርስቲያን ባለውለታዎች? አዜብ ነች ተሳዳቢዎቹ ፈሪሃ  እግዚአብሄር የሚታይባቸው? ሻንበል ግዛው ነው ተሳዳቢዎቹ ቤተክርስቲያኑን ከጽዳት ጭምር በመጠገን የሚያገለግሉት? አቶ ጌታቸውና  ባለቤቱ ናቸው ተሳዳቢዎቹ  ቤተክርስቲያኑ ያገለገሉ። አቶ  ኪዳኔ  ምስክር አቶ  እዬኤል ናቸው ተሳዳቢዎቹ ቤተክርስቲያኑን የገነቡት?
ወንድሞችና  እህቶች ሰዳቢዎቹ ናቸው የተሰደቡት ለቤተክርስቲያኑ ገንዘባቸውን ያፈሰሱት?  ላባቸውን ያንጠፈጠፉት? መልሱን ለናንተ  እንተዋለን ምናልባት ካንዳንዶቹ ጋር ያመለካከት ልዩነት እንደነበረን መናገር ቢቻልም አንድም ቀን ሰድበናቸው አነድም ቀን ያደረጉትን ትሩፋት ተሻምተናቸው አናውቅም። ሰው ትልቅነቱ የሚለካው በሃሳብ እየተፋጨ ምስጋና የሚያስፈልግበት ቦ ታ  ላይ ምስጋና ሲያቀርብ ነው። መረዋ  ትናንት እንዳልነው ዛሬም እዚህ ቤተክርስቲያን ላይ የተከሰተው ችግር እዚህ እንዲደርስ ያደረገው ዝም ያለው ምእመን መሆኑን አሁንም መናገር እንወዳለን። የምናደርገውን ስለምናውቅ እኛ ተራ  ዘለፋ ውስጥ ገብተን አይታችሁን አታውቁም። የቦርዱ ጋሻ ጃግሬዎች የተሳደቡት ስማችሁን የጠቀሱትን ግለሰቦች ሳይሆን እኛን መሆኑን እንድትረዱ እንወዳለን። ለምን ብትሉ የናንተን ስድብ አይተን እኛ  አፋችንን እንድንዘጋ  የተጠነሰሰ  ጥንስስ መሆኑን ስለምናውቅ።

እነዚሁ የቦርድ አፈቀላጤዎች በጽሁፋቸው በዛሬው እለት ስብሰባ  የጠሩትን ተመራጭ ሽማግሌዎች ያልተመረጡ ናቸው ብለው ሲናገሩ አይተናል። የዘለፉት ሽማግሌዎቹን ሳይሆን የመረጣቸውን 200 በላይ የሆነውን ምእመን መሆኑን ግን ሊታያቸው አልቻለም። ስለቦርዱ አሻፈረኝ ማለት በጽሁፍ ያለ  በመሆኑ መከራከር አንፈልግም። ካስፈለገ ልናስነብባቸው ቃል እንገባለን። ነገሩ ግን እነሱ ባባረሩ:: እነሱ ሕግ ያላግባብ በቀየሩ እነሱ መብት በገፈፉ ከሳሾች ለምን ካስ እንደሚከፍሉ ግን ሳይነግሯችሁ አድበስብሰው አልፈዋል። "ጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ የመልከኛው ነው ካሳውን ግን ገበሬው ይካስ" የሚለው የድሮው ቀለድ ታውሷቸው ይሆን? ማን ያውቃል።

በተረፈ ለስብሰባ  የተከለከለው አዳራሽ ለመሸኛ መፈቀዱ ቢገርመንም የሚሄዱት ግለሰብ የሰሩትን ጥሩ ነገር እንጂ ያበላሹትን መጥፎ  ድርጊት ይዘው እንዳይሄዱ ልናስታውሳቸው እንወዳለን።

ሁላችሁንም ስብሰባው ላይ እንያችሁ

መልካም ቀን

Friday, June 18, 2010

ይግባኝን ምን አመጣው? ቁጥር ፴፫

እንደምን  ከረማቸሁ?  እንኴን ለዓመቱ ለሰኔ ሚካኤል   ክብረ በዓል አደረሳችሁ እያልን መጭውን ዓመት የፍቅርና  የደስታ እንዲያደርግልን መረዋ  ከልብ ይመኛል። ባለፈው ዓመት ምን አጣላን ብለን ማሰብ ብቻ  ሳይሆን መጭውን ዓመት እንዴት የሰላም ዓመት ማድረግ ይቻላል ብለንም ከማሰብና ከመጨነቅም አንቆጠብም። ምን ግዜም ጥረታችን ሰላም መፍጠር ነውና።

እስካሁን ድረስ ሰው ስንዘልፍ አላያችሁንም። በመረዋ ምክንያት ግን ግለሰቦች ተዘልፈዋል። እስካሁን ድረስ የማንንም መብት ስንጋፋ  አላያችሁንም። በመረዋ ምክንያት ግን ግለሰቦች ዘራቸው ተቆጥሮ፤  የሞቱት ዘመዶቻቸው ተወስተው፤ የፍቅር ግንኙነታቸው ሳይቀር ተነስቶ፤ የመንፈስ ጥንካሬአቸው ተተችቶ፤ ምስጢረ  ቁርባን መሳለቂያ  ሆኖ የፖለቲካ  ጀርባቸው ታይቶ፤ ባልዋሉበት እንደወንጀለኛ ተፈርጀዋል። ይህ ሁሉ መሸካከርን ከማምጣቱ ሌላ መቀራረብን ይፈጥራል ብሎ ግን መረዋ አያምንም። መረዋ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰላምና  ፍቅር አይመሰረትም  ያለው ቀደም ባለው ሰዓት እንደ ነበር ለአንባብያን በድጋሜ  ማስታወስ ይወዳል።

ይህ እንዳለ  ሆኖ  ባለፈው ተመስርቶ  በነበረው ክስ ማለትም ከቤተክርስቲያኑ ሰው ማባረር አትችሉም፡ ያልረበሸን ግለሰብ በፖሊስ አታባርሩም፡ መረጃዎችን አታጠፉም: የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ ያላግባብ ማጥፋት አትችሉም ተብሎ ተመስርቶ በነበረው ክስ ዳኛው የሰጠውን ብያኔ ለምእመናን በቤተክርስቲያኑ መንበር ቆመው "እንኴን  ደስ ያላችሁ አሸነፍን"  ብለው ተናግረው የነበሩት የቦርድ አባላት አሁን ለምን ይግባኝ  ጠየቁ?

ያሸነፈ እንዴት ይግባኝ ይጠይቃል?
ካልሆነ የተሰጠው ውሳኔ ያስፈራቸው ከምኑ ላይ ነው?  
ይግባኙ ምእመንን ማባረር አለብን፡
ዶሴዎችን መረጃዎችን ማጥፋት ይፈቀድልን፡
በፖሊስ ታጅበን ቅዳሴ እንድናደርግ ይፈቀድልን ማለት ይሆን?

ይህንን ያነሳነው ገንዘብን አስመልክቶ  የተነሳው ጥያቄ  ለጊዜው ዳኛው አልተቀበለውምና እንደፈለጋቸው ቼክ እየጻፉ መክረምን ለምን ጠሉት?  በማለት ነው።

መረዋ   የራሱ መልስ አድርጎ የወሰደው መሸነፋቸውን ተቀብለዋል  ባይሆንማ  ኖሮ ይግባኝ መጠየቅን ምን አመጣው?  የሚል ይሆናል።

በተጨማሪ ቀደም ብሎ ተመስርቶ  የነበረውና  ቦርዱ አሸንፎ ከሳሾች ይግባኝ ያሉበት ሌላው ክስ የቦርድ አባላት በያዝነው ወር JUNE 17,  2010 መልስ እንዲሰጡ ተወስኖ  የነበረውን ቀነ  ቀጠሮ  በጠበቃቸው በኩል ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ  አቅርበው ተጨማሪ አንድ ወር እንደተሰጣቸው ማወቃችንን ለአንባብያን መግለጽ  እንወዳለን። በሚመጣው  እትማችን ሰፋ  ያለ  ዘገባ  የምናቀርብበት ሌላ ጉዳይ እንዳለ  እየነገርናችሁ ለዛሬ  በዚሁ እንሰናበታለን። እንዴ ው ለማሳሰቢያ  ያክል፦ 

ማንም ሰው ከየትም ይወለድ ትወለድ   ክርስቲያን ከሆነ ወንድም ነው ከሆነች እህት ነች።
ማንም ሰው ምንም የፖለቲካ አመለካከት ይኑረው ይኑራት በኦርቶዶስ እምነታችን አምኖ ከተጠመቀ አምና ከተጠመቀች ቤተክርስቲያናችንን ከተቀላቀለ ከተቀላቀለች ወንድም ነው ወይም እህት ነች። 

በሰላም ይግጠመን።

  

Monday, June 14, 2010

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በዳኛው ተፈረመ ቁጥር ፴፪

ውድ አንባብያን መረዋ  በዛሬው እለት በዳላስ 101 ዲስትሪክት ፍርድ ቤት ዳኛ ተፈርሞ ለሁለቱም ጠበቃዎች የተላከውን ውሳነኔ እንዳለ ለአንባብያን ያቀርባል።  በውሳኔው ላይ እንደምታነቡት ይህ የዳኛው ውሳኔ  በ JUNE 2, 2010 የተፈረመ  ሲሆን ዳኛው በከሳሾችና  በተከሳሾች የቀረበውን የፍርድ ሃሳብ ተመልክቶ በከሳሾች ቀርቦ  የነበረውን ሃሳብ እንዳለ  ተቀብሎ መፈረሙ የመጀመሪያ  ድል መሆኑን ልንናገር እንወዳለን። ይህ ውሳኔ እስከ  ቀጠሮው ቀን ማለትም እስከ December 6, 2010 ድረስ የጸና  ከመሆኑም በላይ እስካሁን ካለን መረጃ  ሁኔታውን በቀጠሮው ቀን የሚያዩት እኝሁ የ 101 ዲስትሪክት ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት የተከበሩ ማርቲን ሎይ እንደሆኑ ለመረዳት ችለናል። የከሳሾችን የፍርድ ሃሳብ እንዳለ  ተቀብለው የፈረሙት ዳኛም በዚሁ የፍርድ ሃሳብ ላይ ለመወሰን በፊታችን June 26, ተይዞ  የነበረውን ቀጠሮ እንደሰረዙትም ለመረዳት ችለናል።

C6,LSE NO.1 0-05578-E


TEKOLA MEKONEN & TSEHAYE TSIDK BETEMARIAM ,       THE 101 ST DISTRICT COURT
                        P!aintifl.                                                                        DALLAS COl'NTY. TEXAS

v.

YOSEF RETTA, MlUJALEM FA1\TAl-IUN. DR. GIRMA WOLDE RUFAEL. ABEBE EWNE ru. EYOEL NEGGA. ABERA FITTA, MRS. TEWABECH TADESSE, MR. BIZUAYEHl GETACHEW, MRS. SOLOME MEKONNEN.

                      Defendants.

TEMPORARY INJUNCTION

On the 18th day of May. 2010. came to be heard the request for a temporary injunction of Plaintiffs Tekola Mekonen and Tsehaye Tsidk Betemariam. as set forth in their Original Petition and Application for Injunctive Relief ("Petition"). All parties appeared in person and through counsel of record. and a record was made of the proceedings. The Court. after considering the pleadings. arguments. evidence and applicable law. finds that Plaintiffs are entitled to a temporary injunction pending a trial on the merits.

More specifically. it appears from the facts before the Court that absent a temporary injunction. Defendants will deny or otherwise interfere with Plaintiffs and other members of The Ethiopian Orthodox Tewahedo Dabre Mehret St. Michael's Church access to the church's religious services, It further appears that Defendants will hide. destroy. or otherwise dispose of church documents. including financial records all of which belong to the membership collectively.

The Court further finds that such activity will cause irreparable harm to Plaintiffs and other members of the church and that Defendants should be enjoined from such activity pending a final trial on the merits. The Court further finds that Plaintiffs have shown a probable right and probable injury if this order is not granted.

The Court further finds that any of the above-described actions would deprive Plaintiffs of the free exercise of their religion.

IT IS THEREFORE ORDERED that Plaintiffs' application for temporary injunction is hereby GRANTED in part. and that Defendants Yosef Retta. Mulualem Fantahun. Dr. Girma Wolde RufaeL Abebe Ewnetu Negatu. Eyoel Negga. Abera Fitta. Mrs. Tewabech Tadesse, Mr. Bizuayehu Getachew, Mrs. Solome Mekonnen. individually and collectively. as well as their agents, officers. servants, employees. attorneys, representatives. including in pal1icular any security guard or service or on-or off-duty law enforcement officers. and other parties in concert or participation with said Defendants. are hereby temporarily enjoined from prohibiting any person from entering the church located at 1106 N. Jupiter Road. Garland, Texas and peaceably participating in worship services or associated activities. Any period of announcements made at the beginning or the end of the traditional worship service are included in this Court's definition of the worship service. The foregoing persons and entities are further temporarily enjoined from forcibly removing or causing to be forcibly removed from the worship services any person who has not first been asked by a member of the Board of Trustees or an authorized official of the church to leave peaceably. The foregoing persons and entities are further temporarily enjoined from asking any person to leave the worship services unless that person is causing an actual disruption of the service as viewed from the perspective of a reasonable person under the same or similar circumstances.

IT IS FURTHER ORDERED that Defendants Yosef Retta, Mulualem Fantahun, Dr. Girma Wolde RufaeL Abebe Ewnetu Negatu, Eyoel Negga, Abera Fitta, Mrs. Tewabech Tadesse, Mr. Bizuayehu Getachew, Mrs. Solome Mekonnen, individually and collectively, as well as their agents, officers, servants, employees, attorneys, representatives, and other parties in concert or participation with said Defendants, are hereby temporarily enjoined from hiding, secreting, destroying or otherwise disposing of any church documents or records, including without limitation tinancial records of the church, or any audio or video recordings whether from the church's security system or otherwise.

IT IS FURTHER ORDERED that PlaintitTs' $2,000 cash previously posted in lieu of a TRO bond shall
continue in force and effect in support of this temporary injunction.

IT IS FURTHER ORDERED that the trial of this cause is set for the 6th day of December 2010 at 9:00 a.m. in the 101st Judicial District Court of Dallas County, Texas.

IT Is FlRTHER ORDERED that this temporary injunction is valid and binding upon all Defendants as of the Court's oral pronouncement at the conclusion of the May 18,2010 hearing.


SIGNED this 2nd day of june 20l0

                                                                                                              JUDGE
                                                                                                   MARTIN LOWY, PRESIDING




Sunday, June 13, 2010

ምእመንን የሚንቅ እምነት የጎደለው ብቻ ነው ቁጥር ፴፩

ውድ የዳላስ የኦርቶዶክስ አማንያን ወንድሞችና  እህቶች እንዴት ከረማችሁ?
ትእግስታችሁን እንደ ፍርሃት፤ ጸሎታችሁን እንደ ሞኝነት፤ ዝምታችሁን  እንደ ሽንፈት ወስዶ አፍነን እንገዛቸዋለን፤ አስፈራርተን ዝም እናሰኛቸዋለን ካልሆነም ቢያንስ ከቤተክርስቲያን አካባቢ ከመንገድ አዳሪ ዱርዬ የማይጠበቅ አሳፋሪ ስድብና ቅሌት በደጋፊዎቻችን እያጻፍን ስም እናጠፋለን ብለው የተነሱ የሚመስሉት የአስተዳደር ቦርድ አባላት  ዛሬም እንደ ትላንትናው የቀረበላቸውን ዘንባባ ለሰላም ሳይሆን እንዳርጩሜ ሊጠቀሙበት  እየሞሩ  ነው። "ጣር የያዘው ነብር ድንራይ ይቆረጥማል" እንዲሉ የቀረበውን ሁሉ እየተተናኮሉ ዛሬ በጣት የሚቆጠሩ የፖለቲካ ሰዎችን ከመጋረጃ  ጀርባ የተደበቁ ያደባባይ ፍርሃት ያላቸውን ግለሰቦች ይዘው ለመቅረታችው ምስክር የሚያስፈልግ አይመስለንም። ሰሞኑን ደግሞ በየብሎጉ ፦የሚጽፉትን አንብባችሁታል ብለንም እንገምታለን። እንዴው ሂደታቸውን ለማሳያየት ያክል፦

ካገር በመጡ መንፈሳዊ አባት ለእርቅ ተለመኑ እንቢ አሉ
ስብሰባ እንዲጠሩ ካንዴም አራት ጊዜ  ተጠየቁ እንቢኝ አሉ
አማራጭ ፈላጊ ቡድን በሚል የተቌቌሙ ሽማግሌዎች ሊሸመግሉ ተነሱ አሻፈረን አሉ
የሰላም ኮሚቴ በሚል የተቌቌሙ ቡድኖች ለመኗቸው ለማነጋገርም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ
በቦርዱ አባባል "አባላትን" ብቻ ነው የምናናግረው ብለው በተናገሩት መሰረት "አባላት " የሆኑትን ፊርማ አሰባስበው መሰብሰቢያ  አዳራሹን እንኴን ፍቀዱልን ተብሎ ጥያቄ  ቀረበ "እረብሻ እንፈራለን" በሚል ከለከሉ።
200 ምእመናን የመረጡን ነንና ስለሚካኤል ችግር እንነጋገር ያሉትን 9 የምእመናንን ተመራጭ ሽማግሌዎችን አናውቃችሁም ብለው መለሱ።

በተቃራኒ ግን 

ካህናቶችን አባረሩ

ከስብሰባ  ላይ ያልተስማማቸውን በፖሊስ አስወጡ

የብዙሃኑን የመናገር መብት አፈኑ

በተለያየ  ኮሚቴ  ውስጥ በፈቃደኝነት ያገለግሉ የነበሩትን ነባር መስራች አባላንት አባረሩ።

ትላንት ይጠቀሙባቸው የነበሩትን የቦርድ አባላት አሁንስ በዛ  ማለት ሲጀምሩ ከቦርድ አባልነት ገፋፍተው አስወጡ።

የቤተክርስቲያኑን ቁልፍ በሌለ ገንዘብ      $4000 ሺ  አውጥተው አስቀየሩ። የመክፈቻው ቁልፍ ቁጥር ለተወሰኑ ታማኝ የቦርድ አባላት ብቻ እንዲሰጥ አደረጉ።

የቤተክርስቲያኑ ኮምፒውተር በቦርድ አባል ዶክተርና  ተመራጭ ባልሆኑት ባለቤታቸው ቅጥጥር ሥር እንዲወድቅ አደረጉ።

ዶክተሩ የተመኙት እንዲሟላ  የባንኩ ቁልፍ እንደ ቤተክርስቲያኑ ቁልፍ እንዲሰጣቸው አደረጉ።

ነባር የነበሩ መስራች አባላት በዘዴ ለቀው እንዲወጡ ዘመቻ ተጀመረ።

ለስደት ሲኖዶስ መንገድ ቀዳጆች ይሆኑ ዘንድ የሲኖዶሱ አብሪዎች ተጋብዘው እንዲመጡ ተደረገ።
ለጠበቃ  ከ $70  ሺህ ያላነሰ ወጭ አደረጉ፡ አሁንም ከማውጣት አልተቆጠቡም።

በቆዩበት አገር ችግር የነበረባቸውን ዲያቆን እንዲቀጠሩ ተደረገ። 

ባባረሯቸው ካህን ምትክ አሜን ብዬ  ያላችሁትን እሰብካለሁ ያልወደዳችሁትን እደግፋለሁ ብለው ውል ሊፈርሙ የሚዘጋጁ ቄስ አስመጥተው ለመቅጠር  ሽማግሌዎች እንዲያጸድቁላቸው ጥያቄ አቀረቡ።

የስደት ሲኖዶስን ለማስመጣት ሽርጉዱን ተያያዙ

ገፍተው ባስወጧቸው የቦርድ  አባላት ምትክ የስደት ሲኖዶስ ደጋፊ በመሆናቸው የሚታወቁትን ግለሰቦች  መርጦ ለማስገባትና ቤተክርስቲያኑን ላንዴም ለሁሌም ለመቆጣጠር መሯሯጣቸውን ቀጠሉ።

የቢተክርስቲያኑን ዘማርያንን አባረሩ በምትኩ ደጋፊ ነን የሚሉትን በመመልመል (የእናቶች መዘምራን በማለት ከባለቤቶቻቸው  ጋር የተደባለቀ ቡድን ፈጠሩ)

የወጣቶች ሕጻናትን የሰንበት ስብስብ በተኑ።

አባላትን አስኮበለሉ
ቤተክርስቲያኑን በፖሊስ አስደፈሩ

አልወደድናቸውም  ያሏቸውን 22  ምእመናን  ከቤተክርስቲያን በፖሊስ ለማባረር ወሰኑ።  ነገር ግን  በፍርድ ቤት ትእዛዝ ምእመንን ከቤተክርስቲያን መከልከል እንደማይችሉ ስለተወሰነባቸው ሕልማቸው ከሸፈ።


ውድ ምእመናን ፍልሚያው የእምነት ሳይሆን የመብት ጥያቄ  ነው። ይህንን እንዲያደርጉ የሚደግፏቸው ደግሞ  መብት ተረገጠ ዲሞክራሲ ታፈነ  የሚል፡ አገር ቤት ገብቼ  ስልጣን እይዛለሁ ብሎ  የሚያታግል የፖለቲካ  ድርጅት መሪዎች መሆናቸውን ያየ ሁሉ ፈዞ  ቢቀር የመገረም እንጂ የፍርሃት እንዳልሆነ ሊገባን ይገባል ።

ስለሆነም ለዛሬ ባለፈው በምእመናን ተመርጠው የነበሩ 9  ሽማግሌዎች የደረሱበትን መደምደሚያ  ለምእመናን ለመናገር የቤክርስቲያኑን አዳራሽ  በመከልከላቸው በሆቴል አዳራሽ የጠሩትን ስብሰባ ለማዳመጥ እንድትችሉ ጥሪ በማቅረባቸው ሁላችሁም ትገኙ ዘንድ መረዋም  ጥሪያቸውን ያስተላልፋል።  ምርጫው እየጠበበ  መጥቷልና ለመብት ትግሉ ስኬት የሁላችንንም ተሳትፎ  ስለሚጠይቅ  ሁላችሁም በስብሰባው እንድትገኙ  እናሳስባለን። ምን እየተደረገ  ነው? ብላችሁ የተቸገራችሁ ካላችሁም ተገኝታችሁ እንድታዳምጡ ጥያቄ  እንድትጠይቁ እናበረታታችኋለን። የሽማግሌዎቹ የስብሰባ  ጥያቄ እነሆ


 ታላቅ መንፈሳዊ የስብሰባ  ጥሪ

የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመፍትሄ ኮሚቴ


UNITED ST. MICHAEL CHURCH RESOLUTION COMMITTEE

በስመ አብ፣ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱስ፣ አሀዱ Aምላክ Aሜን።

ታላቅ መንፈሳዊ

የስብሰባ ጥሪ።

ቁጥር፣ 2

ውድ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምእመናን።

በ 5-8-10 በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያናችን ስለ አለው Aጠቃላይ ችግር Aስመልክቶ በተደረገው የምእመናን ጉባኤ፣ 9 Aባላትን የያዘ ኮሚቴ መቋቋሙ የሚታወስ ነው። ይህ ኮሚቴ ጉባኤው የወሰናቸውን አቋሞች ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የAስተዳደር ቦርድ Aባላት ጋር በመነጋገር እንዲያስፈጽም ሙሉ ውክልና ተሰጥቶታል። ኮሚቴው በውክልናው መሠረት ከቦርዱ ጋር ያደረገውን ጥረትና ውጤቱን፣ ሪፖርት ለማድረግና የወደፊቱን የመፍትሔ ሃሳብ ለማቅረብና ለመወያየት እንዲቻል፣ በ 6-26-10, በ 3፡30 p.m., Crowne Plaza, 780 Alpha Road, Dalas, TX 75240, ስብሰባ ጠርቷል። ቀደም ሲል የወከሉን ምእመናንና በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ ለመወያየት ፈቃደኛ የሆነውን ሁሉ እንዲገኙለት በአክብሮት ጠርቷል።

እግዚአብሔር ሰላምና ፍቅሩን ይስጠን።

Wednesday, June 9, 2010

በረንዳ የቆመ ሌባ ከሩቅ ሲያዩት ባለቤት ይመስላል። ቁጥር ፴

ውድ አንባብያን እንዴት ከረማችሁ?

ምነው ጠፉ ለሚሉን ጠላታችን......... እያልን ለምን ዝም ብላችሁ ከረማችሁ ለምትሉን ደግሞ የክርስቲያን ወንድሞችና  እህቶች ግን የግል ሕይወት እሩጫ ሆነና እንጂ መጥፋት ፈልገን እንዳልነበረ ልናወሳችሁ እንወዳለን። ሰሞኑን የምርቃት ወቅት በመሆኑም ከግራ  ቀኝ እየተሯ ሯጥን ስለነበረም የጊዜ መሻማት በዛብን ብንላችሁም እውነት ይሆናል። ባለፉት ሳምንታት ብዙ የተደረጉ ክስተቶች መኖራቸውን ስንታዘብ የሰንበቴ ብሎግ ባለቤቶችም ስማቸውን ቀይረው የተለመደ  ስድብ የሚያሰራጩበት ሌላ  ብሎግ እንደከፈቱ ለማየትም እድል ገጥሞናል። እነዚህ ሃይማኖተኛ ነን እያሉ ሃይማኖት ያልዳሰሳቸው፤ ፖለቲከኛ ነን ብለው ፖለቲካው የተምታታባቸው፤ ተናግረው የማያሳምኑ፡ የሚጽፉት እርስ በራሱ የሚጠላለፍና  የሚቃረን ደራስያን አንቱ የተባሉ ከመሰላቸው በመንደርደሪያ  ያለውን እርእስ ያስታውሱናል። ከትግራይ መወለድ ወንጀል ነው ብለው የሚያምኑ እነዚህ ግራ  የተጋቡ ብድኖች  የግለሰብን  ስም እየጠቀሱ ዘር እየቆጠሩ አገር ቤት ያለው መንግስት ዘመዶች ናቸውና ተጠንቀቁ ብለው ግለሰቦችን የመለስ ዘመዶች በመሆናቸው ብቻ ሲወነጅሉ አይተናል። አሜሪካ  እየኖሩ ያባት ወንጀል ለልጅ  ይተላለፋል ብለው አሁንም የሚያምኑ ግለሰቦችን ምን ሊቀይራቸው እንደሚችል እግዜር ይወቅ።  አገር ቤት ያለውን መንግሥት የምንጠላው በዘረኝነቱ ነው ሲሉን ይቆዩና እነእገሌ የነእገሌ ዘመዶች ናቸውና አታዳምጧቸው ብለው ይነሳሉ። ግለሰቦቹን በሚሰሩት በሚናገሩት ሳይሆን በደም ቋጠሯቸው ይወነጅላሉ። ነጠላ  ለብሶ  የሚያስቀድሰውን ሃጥያተኛ የነሱን ዘመናዊ አለባበስ የጽድቅ መመዘኛ አድርገው ያቀርባሉ። ወንድሞችና  እህቶች የሰንበቴ ተራኪዎች ሁለት ነገር መሆን አይቻልምና አንዱን ብትከተሉ መልካም ነው። የኦርቶዶክስ አማኝ የሆነ  ሁሉ ወንድም እህታችን ነው ማለት፧ ካልሆነ  የኛን ፖለቲካ  ያልተከተለ እኛ የምንለውን ያልተቀበለ ክርስቲያን አይደለም ብሎ መነሳት። መረዋ ባዲሱ ብሎግ ላይ የተጻፈውን በንቀት በመመልከት ትላንት እንዳደረገው ሊያልፈው ወስኖ  ነበር፤ ምን አልባት ስህተታቸው ቢነግሯቸው ሊቀበሉ ይችላሉ በማለት ዛሬ  ላንዴም ለሁሌም መልስ ለመስጠት ተነሳን። የግለሰብን ስም መጥራትና  መሳደብ ደግሞ መብት አይደለም የሚያስከትለው ሃላፊነትም እንዳለ መታወቅ ይኖርበታል። እነዚህ ቡድኖች ስም እየጠሩ ሊሰድቧቸው የተነሱትን ግለሰቦች  ብታስተውሉ በእርግጠኝነት እነሱ ለዚህ ቤተክርስቲያን አደረግን ከሚሉት የበለጠ አስተዋጽኦ ያደረጉ ግለሰቦች ለመሆናቸው ጥርጥር የለንም። ውድ ሰንበቴዎች ግለሰቦች ትላንት ምን ነበሩ ማለት ከመጀመራችሁ በፊት የራሳችሁን ኋላ  ብታዩ  መልካም ነው። አንድ ከማዶ የሚጣራ ሰው "ኧረ  አቶ ግሞ" ብሎ  መጣራቱን የሰማ ሌላ  ግለሰብ "ወይ እኔ በሸቀጥ እንዴት ያለ  ሥም አለ  እባካችሁ?"  አለ  ይሉ ነበርና።

ከዚህ በፊት ተደርጎ  በነበረው የኦርቶዶክስ አማንያን ስብሰባ  ላይ ተመራጭ ሆነው የተመረጡት 9 ግለሰቦች ከቦርዱ የፈቃደኝነት መልስ እንዳላገኙ ለመስማት ችለናል። ቦርዱ እራሱ ያላቌቌመውን ኮሚቴ  እንደማያውቅም መናገሩን ለመስማትም ችለናል። በእኛ በኩል እንዴው የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት እንጂ መረዋ የቦርዱ ተመራጮች ሰላምን እንደማይፈልጉ ቀደም ብሎም እናውቅ ስለነበር አልተገረምንም።   የምንገረመው ለመነጋገር ፈቃደኛ ቢሆኑ  ብቻ ነበር። የማያልቅ የሕዝብ ገንዘብ ለጠበቃ የሚያስረክቡት ተመራጮች ገንዘቡ እስከሚያልቅ እንዋጋለን ማለታቸው ስንሰማ  አዘንን እንጂ አልተገረምንም። ጠበቃቸውም ቢሆን ሁኔታዎች እየተበላሹ  ሄደው ክርክሩ እስካልቀጠለ  ድረስ ገቢ አይኖረውምና  ያሁኑ ሁኔታ እያስደሰተው ቢመጣ ምን ይገርማል? በሚመጣው  ቦርዱ በጠራው ስብሰባ  ላይም ከበጀትና  ከውጭ ተቀጣሪ የገንዘብ አጣሪ ዘገባ  ውጭ ክስን አስመልክቶ  መወያየት እንደማይቻል ከወዲሁ የቦርድ አባላቱ  እያሰጠነቀቁ መሆኑን ስንሰማ የተናገርነው ትንቢት መሆኑ ቀርቶ እውነትነቱ ተረጋገጠ  እንጂ አዲስ አልሆነብንም። ለምን ቢሉ ሰላም ከተፈጠረ  ተመራጮቹ አይኖሩምና።

በሌላ  በኩል ባሁኑ ወቅት እንደ ቦርዱ አባባል "አባላት ናቸው"  የተባሉትን አስፈርመው ስብሰባ  የጠሩት እናት እንቢ እንደተባሉ ስንሰማ "በመተዳደሪያ  ደንባችን መሰረት" የሚሉት ግለሰቦች መልሳቸው ምን ይሆን?  ብለን እራሳችንን ጠየቅን።

ካሁን በኋላ  ያለው ምርጫ አንድ ብቻ  ነው ይኸውም ነገሩ የእምነት ሳይሆን የመብት መሆኑን ተቀብሎ በፍርድ ቤት መፋለም ብቻ ነው። ይህንን ደግሞ ዶክተሮቹና ከግሪክና ከራሺያ የመጡ አማካሪዎቻቸው ከቦስተን የመጡት ደጋፊቸው ጭምር ሊረዱት ይገባል እንላለን።
ስማችሁ በብሎግ ተጠቅሶ የተወቀሳችሁ ግለሰቦች ሁሉ ደስ ሊላችሁ የሚገባው ነገር ቢኖር የሰራችሁት ፍሬ  እያፈራ መምጣቱን እውነትን የማይከተሉ ግለሰቦች ደግሞ ማታለል እንዳልቻሉ እየተገነዘቡ መሆኑን፤ አካሄዳችሁ እንዳስፈራቸው መጭው ጨለማ  እንደሆነባቸው ነው።

ውይይትን የሚፈራ  ሁሉ መሸነፉን የተቀበለ  ብቻ  ነውና።

በዚሁ አዲስ ብሎግ ላይ የቀድሞ  የኢሕአፓ አባላት የሚለው የተጠቀሰው ምን ለማለት የሆን?

ለዚህ ነው እንዴ ወይዘሮ በየነች መኮንን የምትወቅሱት?  ወቀሳችሁ  ባሳለፈችው የትግል ተመክሮ ነው ወይንስ ለቤተክርስቲያኑ ባበረከተችው ተሳትፎ ይሆን? ያለችው ሴት እሷ ብቻ ነች በማለት ነው ስሟን ያነሳነው።

ፍቅሩን ያድለን
ልቦና  ይስጣችሁ።