Sunday, June 13, 2010

ምእመንን የሚንቅ እምነት የጎደለው ብቻ ነው ቁጥር ፴፩

ውድ የዳላስ የኦርቶዶክስ አማንያን ወንድሞችና  እህቶች እንዴት ከረማችሁ?
ትእግስታችሁን እንደ ፍርሃት፤ ጸሎታችሁን እንደ ሞኝነት፤ ዝምታችሁን  እንደ ሽንፈት ወስዶ አፍነን እንገዛቸዋለን፤ አስፈራርተን ዝም እናሰኛቸዋለን ካልሆነም ቢያንስ ከቤተክርስቲያን አካባቢ ከመንገድ አዳሪ ዱርዬ የማይጠበቅ አሳፋሪ ስድብና ቅሌት በደጋፊዎቻችን እያጻፍን ስም እናጠፋለን ብለው የተነሱ የሚመስሉት የአስተዳደር ቦርድ አባላት  ዛሬም እንደ ትላንትናው የቀረበላቸውን ዘንባባ ለሰላም ሳይሆን እንዳርጩሜ ሊጠቀሙበት  እየሞሩ  ነው። "ጣር የያዘው ነብር ድንራይ ይቆረጥማል" እንዲሉ የቀረበውን ሁሉ እየተተናኮሉ ዛሬ በጣት የሚቆጠሩ የፖለቲካ ሰዎችን ከመጋረጃ  ጀርባ የተደበቁ ያደባባይ ፍርሃት ያላቸውን ግለሰቦች ይዘው ለመቅረታችው ምስክር የሚያስፈልግ አይመስለንም። ሰሞኑን ደግሞ በየብሎጉ ፦የሚጽፉትን አንብባችሁታል ብለንም እንገምታለን። እንዴው ሂደታቸውን ለማሳያየት ያክል፦

ካገር በመጡ መንፈሳዊ አባት ለእርቅ ተለመኑ እንቢ አሉ
ስብሰባ እንዲጠሩ ካንዴም አራት ጊዜ  ተጠየቁ እንቢኝ አሉ
አማራጭ ፈላጊ ቡድን በሚል የተቌቌሙ ሽማግሌዎች ሊሸመግሉ ተነሱ አሻፈረን አሉ
የሰላም ኮሚቴ በሚል የተቌቌሙ ቡድኖች ለመኗቸው ለማነጋገርም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ
በቦርዱ አባባል "አባላትን" ብቻ ነው የምናናግረው ብለው በተናገሩት መሰረት "አባላት " የሆኑትን ፊርማ አሰባስበው መሰብሰቢያ  አዳራሹን እንኴን ፍቀዱልን ተብሎ ጥያቄ  ቀረበ "እረብሻ እንፈራለን" በሚል ከለከሉ።
200 ምእመናን የመረጡን ነንና ስለሚካኤል ችግር እንነጋገር ያሉትን 9 የምእመናንን ተመራጭ ሽማግሌዎችን አናውቃችሁም ብለው መለሱ።

በተቃራኒ ግን 

ካህናቶችን አባረሩ

ከስብሰባ  ላይ ያልተስማማቸውን በፖሊስ አስወጡ

የብዙሃኑን የመናገር መብት አፈኑ

በተለያየ  ኮሚቴ  ውስጥ በፈቃደኝነት ያገለግሉ የነበሩትን ነባር መስራች አባላንት አባረሩ።

ትላንት ይጠቀሙባቸው የነበሩትን የቦርድ አባላት አሁንስ በዛ  ማለት ሲጀምሩ ከቦርድ አባልነት ገፋፍተው አስወጡ።

የቤተክርስቲያኑን ቁልፍ በሌለ ገንዘብ      $4000 ሺ  አውጥተው አስቀየሩ። የመክፈቻው ቁልፍ ቁጥር ለተወሰኑ ታማኝ የቦርድ አባላት ብቻ እንዲሰጥ አደረጉ።

የቤተክርስቲያኑ ኮምፒውተር በቦርድ አባል ዶክተርና  ተመራጭ ባልሆኑት ባለቤታቸው ቅጥጥር ሥር እንዲወድቅ አደረጉ።

ዶክተሩ የተመኙት እንዲሟላ  የባንኩ ቁልፍ እንደ ቤተክርስቲያኑ ቁልፍ እንዲሰጣቸው አደረጉ።

ነባር የነበሩ መስራች አባላት በዘዴ ለቀው እንዲወጡ ዘመቻ ተጀመረ።

ለስደት ሲኖዶስ መንገድ ቀዳጆች ይሆኑ ዘንድ የሲኖዶሱ አብሪዎች ተጋብዘው እንዲመጡ ተደረገ።
ለጠበቃ  ከ $70  ሺህ ያላነሰ ወጭ አደረጉ፡ አሁንም ከማውጣት አልተቆጠቡም።

በቆዩበት አገር ችግር የነበረባቸውን ዲያቆን እንዲቀጠሩ ተደረገ። 

ባባረሯቸው ካህን ምትክ አሜን ብዬ  ያላችሁትን እሰብካለሁ ያልወደዳችሁትን እደግፋለሁ ብለው ውል ሊፈርሙ የሚዘጋጁ ቄስ አስመጥተው ለመቅጠር  ሽማግሌዎች እንዲያጸድቁላቸው ጥያቄ አቀረቡ።

የስደት ሲኖዶስን ለማስመጣት ሽርጉዱን ተያያዙ

ገፍተው ባስወጧቸው የቦርድ  አባላት ምትክ የስደት ሲኖዶስ ደጋፊ በመሆናቸው የሚታወቁትን ግለሰቦች  መርጦ ለማስገባትና ቤተክርስቲያኑን ላንዴም ለሁሌም ለመቆጣጠር መሯሯጣቸውን ቀጠሉ።

የቢተክርስቲያኑን ዘማርያንን አባረሩ በምትኩ ደጋፊ ነን የሚሉትን በመመልመል (የእናቶች መዘምራን በማለት ከባለቤቶቻቸው  ጋር የተደባለቀ ቡድን ፈጠሩ)

የወጣቶች ሕጻናትን የሰንበት ስብስብ በተኑ።

አባላትን አስኮበለሉ
ቤተክርስቲያኑን በፖሊስ አስደፈሩ

አልወደድናቸውም  ያሏቸውን 22  ምእመናን  ከቤተክርስቲያን በፖሊስ ለማባረር ወሰኑ።  ነገር ግን  በፍርድ ቤት ትእዛዝ ምእመንን ከቤተክርስቲያን መከልከል እንደማይችሉ ስለተወሰነባቸው ሕልማቸው ከሸፈ።


ውድ ምእመናን ፍልሚያው የእምነት ሳይሆን የመብት ጥያቄ  ነው። ይህንን እንዲያደርጉ የሚደግፏቸው ደግሞ  መብት ተረገጠ ዲሞክራሲ ታፈነ  የሚል፡ አገር ቤት ገብቼ  ስልጣን እይዛለሁ ብሎ  የሚያታግል የፖለቲካ  ድርጅት መሪዎች መሆናቸውን ያየ ሁሉ ፈዞ  ቢቀር የመገረም እንጂ የፍርሃት እንዳልሆነ ሊገባን ይገባል ።

ስለሆነም ለዛሬ ባለፈው በምእመናን ተመርጠው የነበሩ 9  ሽማግሌዎች የደረሱበትን መደምደሚያ  ለምእመናን ለመናገር የቤክርስቲያኑን አዳራሽ  በመከልከላቸው በሆቴል አዳራሽ የጠሩትን ስብሰባ ለማዳመጥ እንድትችሉ ጥሪ በማቅረባቸው ሁላችሁም ትገኙ ዘንድ መረዋም  ጥሪያቸውን ያስተላልፋል።  ምርጫው እየጠበበ  መጥቷልና ለመብት ትግሉ ስኬት የሁላችንንም ተሳትፎ  ስለሚጠይቅ  ሁላችሁም በስብሰባው እንድትገኙ  እናሳስባለን። ምን እየተደረገ  ነው? ብላችሁ የተቸገራችሁ ካላችሁም ተገኝታችሁ እንድታዳምጡ ጥያቄ  እንድትጠይቁ እናበረታታችኋለን። የሽማግሌዎቹ የስብሰባ  ጥያቄ እነሆ


 ታላቅ መንፈሳዊ የስብሰባ  ጥሪ

የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመፍትሄ ኮሚቴ


UNITED ST. MICHAEL CHURCH RESOLUTION COMMITTEE

በስመ አብ፣ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱስ፣ አሀዱ Aምላክ Aሜን።

ታላቅ መንፈሳዊ

የስብሰባ ጥሪ።

ቁጥር፣ 2

ውድ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምእመናን።

በ 5-8-10 በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያናችን ስለ አለው Aጠቃላይ ችግር Aስመልክቶ በተደረገው የምእመናን ጉባኤ፣ 9 Aባላትን የያዘ ኮሚቴ መቋቋሙ የሚታወስ ነው። ይህ ኮሚቴ ጉባኤው የወሰናቸውን አቋሞች ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የAስተዳደር ቦርድ Aባላት ጋር በመነጋገር እንዲያስፈጽም ሙሉ ውክልና ተሰጥቶታል። ኮሚቴው በውክልናው መሠረት ከቦርዱ ጋር ያደረገውን ጥረትና ውጤቱን፣ ሪፖርት ለማድረግና የወደፊቱን የመፍትሔ ሃሳብ ለማቅረብና ለመወያየት እንዲቻል፣ በ 6-26-10, በ 3፡30 p.m., Crowne Plaza, 780 Alpha Road, Dalas, TX 75240, ስብሰባ ጠርቷል። ቀደም ሲል የወከሉን ምእመናንና በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ ለመወያየት ፈቃደኛ የሆነውን ሁሉ እንዲገኙለት በአክብሮት ጠርቷል።

እግዚአብሔር ሰላምና ፍቅሩን ይስጠን።