Saturday, June 26, 2010

መስቀል እኮ ለጌጥም ይደረጋል ቁጥር ፴፬

"To get something you never had, you have to do something you never did"

"ያልነበረህን  ለማግኘት አድርገህ የማታውቀውን ማድረግ ይኖርብሃል" ትርጉሙ የመረዋ።

ይህንን  ጥቅስ የላከልን አንድ በቅርብ የምናውቀው ጔደኛችን ነበር። እኛም ለሌላ  ጔደኛችን  አሳየነው። በጥቅሱ አልተስማማም። "በየቀኑ ሎተሪ የሚገዛን ግለሰብ ሎተሪ  ሲደርሰው ምን  ልትሉት ነው?" አለን። ይህንን  ያቀረብንላችሁ በአባባል እንኴ ልዩነት ሊኖር እንደሚችል ለመጠቆም ያክል ነው። ፈረንጆች ግማሽ ብርጭቆ የሞላ  ውሃ፤ ግማሽ ብርጭቆ የጎደለ ውሃ  እንደሚሉት አይነት። 

እንዴት ከረማችሁ።

ለተሰደባችሁ ጥናቱን: ለተወነጀላችሁ ጥንካሬን፤ ይስጣችሁ ስንል ከዚያ  ማዶ  ያሉ የቦርዱ ጋሻ ጃግሬዎች ስልታቸውን አስፋፍተው ዛሬ  የተጋባን ሊያፋቱ፤ የተከበረውን ሊያዋርዱ፤ የተናቀውን ሊያነግሱ፤ መነሳታቸውን አይታችኋል። እነሱ በወረዱበት አለመውረዳችን  አሳስቧቸው ከተቀመጡበት የቤተክርስቲያን ደጀሰላም ማ ማንን ተኛ? ማ  ከማጋር ተቃቀፈ ማለት ጀምረዋል። "እኛ ድሮ የምናውቀው ጭድ ላይ የተኛ ጎረምሳ  የፍም እንጨት አይንተራስም"  ሲባል ነበር። እነዚህ ግን ቤንዚንና  ክብሪትም ይዘው ሲጫወቱ እያስተዋልን ነው። ስለነሱ ትዳር መናገር ብንጀምር  ተደብቀው እንደሚከርሙ እያወቁ፤ ለምን ይህንን ደካማና አሳፋሪ መንገድ መረጡ?  ብለን ስንጠይቅ ያገኘነው መልስ እየተሸነፉ ነው። ያላቸውን ጥይት ተኩሰው ጨርሰው ዛሬ አጠገባቸው ያለውን ጭራሮ፤ ጉቶ፤ ኩበት ጭምር እየወረወሩ ነው የሚል ሆኖ አገኘነው። "አስፈራራናቸው"  እንደሚሉም  ሰምተናል። ከገባቸው መፍራትም ያዋቂ የነቃ  ሰው መሆኑን እንናገር። እኛ እነሱ ስለዘቀጡ አንዘቅጥም። ከወገብ በታች ባለ ነገር የሚመሰጥ ከቀበቶ  በላይ ባዶ  የሆነ  ብቻ  ነውና።

የተሳዳቢዎቹንና  የተሰደቡትን  ግለሰቦች  ሚዛን ላይ በማስቀመጥ ማ ምን እንደሆነ መመዘን ደግሞ  የያንዳንዱ አማኝ ግዴታ  መሆን ይኖርበታል። ውድ ወንድሞችና  እህቶች። የቦርዱ ደጋፊ ነን ባዬች የቀራቸውና  የሚነግሩን የጭን ወሬ  ከሆነ  እንኴን ደስ ያለን ተሸንፈዋል።

የቦርዱ ደጋፊዎች የሚያዜሙት

ልጅቷ ነች ብዬ እናቷን ሳምኴቸው .......... ከሆነ እንኴን ደስ ያላችሁ  እራሳቸውን እየገደሉ ነው :: 

ነገርን ነገር ያመጣዋልና  የቆየ ተረት ታወሰን። አንድ ግለሰብ የተቀባበለ ጠብመንጃ  ይዞ ይሮጣል ሌላው ከኋላ ዱላውን እየወዘወዘ  "ቁም የት ተሄዳለህ"  እያለ  ያሳድደዋል። ይህንን የተመለከተ ሌላ ተመልካች ባለ ጠብመንጃውን "ወንድሜ  ለምን ትሸሻለህ?"  ቢለው ባለ ጠብመንጃው "ይቅርታ  አድርግልኝ እሬስ እየተከተለኝ ነው"  አለ ይሉ ነበር።

እናም
ካሁን በኋላ  እነዚህ ለልጆቻችን አርአያ  ይሆናሉ ብለን አንጠብቅም።
እነዚህ ልጆቻችንን  አያስተምሩም።
እነዚህ ስለሃይማኖት አይሰብኩንም።
እነዚህ ስለግብረገብ ገለጻ አይሰጡንም።
እነዚህ ስለፖለቲካ  አይቀሰቅሱንም።

አቶ ሃይሉ ነው ተሳዳቢዎቹ የቤተክርስቲያን ባለውለታዎች? አዜብ ነች ተሳዳቢዎቹ ፈሪሃ  እግዚአብሄር የሚታይባቸው? ሻንበል ግዛው ነው ተሳዳቢዎቹ ቤተክርስቲያኑን ከጽዳት ጭምር በመጠገን የሚያገለግሉት? አቶ ጌታቸውና  ባለቤቱ ናቸው ተሳዳቢዎቹ  ቤተክርስቲያኑ ያገለገሉ። አቶ  ኪዳኔ  ምስክር አቶ  እዬኤል ናቸው ተሳዳቢዎቹ ቤተክርስቲያኑን የገነቡት?
ወንድሞችና  እህቶች ሰዳቢዎቹ ናቸው የተሰደቡት ለቤተክርስቲያኑ ገንዘባቸውን ያፈሰሱት?  ላባቸውን ያንጠፈጠፉት? መልሱን ለናንተ  እንተዋለን ምናልባት ካንዳንዶቹ ጋር ያመለካከት ልዩነት እንደነበረን መናገር ቢቻልም አንድም ቀን ሰድበናቸው አነድም ቀን ያደረጉትን ትሩፋት ተሻምተናቸው አናውቅም። ሰው ትልቅነቱ የሚለካው በሃሳብ እየተፋጨ ምስጋና የሚያስፈልግበት ቦ ታ  ላይ ምስጋና ሲያቀርብ ነው። መረዋ  ትናንት እንዳልነው ዛሬም እዚህ ቤተክርስቲያን ላይ የተከሰተው ችግር እዚህ እንዲደርስ ያደረገው ዝም ያለው ምእመን መሆኑን አሁንም መናገር እንወዳለን። የምናደርገውን ስለምናውቅ እኛ ተራ  ዘለፋ ውስጥ ገብተን አይታችሁን አታውቁም። የቦርዱ ጋሻ ጃግሬዎች የተሳደቡት ስማችሁን የጠቀሱትን ግለሰቦች ሳይሆን እኛን መሆኑን እንድትረዱ እንወዳለን። ለምን ብትሉ የናንተን ስድብ አይተን እኛ  አፋችንን እንድንዘጋ  የተጠነሰሰ  ጥንስስ መሆኑን ስለምናውቅ።

እነዚሁ የቦርድ አፈቀላጤዎች በጽሁፋቸው በዛሬው እለት ስብሰባ  የጠሩትን ተመራጭ ሽማግሌዎች ያልተመረጡ ናቸው ብለው ሲናገሩ አይተናል። የዘለፉት ሽማግሌዎቹን ሳይሆን የመረጣቸውን 200 በላይ የሆነውን ምእመን መሆኑን ግን ሊታያቸው አልቻለም። ስለቦርዱ አሻፈረኝ ማለት በጽሁፍ ያለ  በመሆኑ መከራከር አንፈልግም። ካስፈለገ ልናስነብባቸው ቃል እንገባለን። ነገሩ ግን እነሱ ባባረሩ:: እነሱ ሕግ ያላግባብ በቀየሩ እነሱ መብት በገፈፉ ከሳሾች ለምን ካስ እንደሚከፍሉ ግን ሳይነግሯችሁ አድበስብሰው አልፈዋል። "ጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ የመልከኛው ነው ካሳውን ግን ገበሬው ይካስ" የሚለው የድሮው ቀለድ ታውሷቸው ይሆን? ማን ያውቃል።

በተረፈ ለስብሰባ  የተከለከለው አዳራሽ ለመሸኛ መፈቀዱ ቢገርመንም የሚሄዱት ግለሰብ የሰሩትን ጥሩ ነገር እንጂ ያበላሹትን መጥፎ  ድርጊት ይዘው እንዳይሄዱ ልናስታውሳቸው እንወዳለን።

ሁላችሁንም ስብሰባው ላይ እንያችሁ

መልካም ቀን