Wednesday, June 9, 2010

በረንዳ የቆመ ሌባ ከሩቅ ሲያዩት ባለቤት ይመስላል። ቁጥር ፴

ውድ አንባብያን እንዴት ከረማችሁ?

ምነው ጠፉ ለሚሉን ጠላታችን......... እያልን ለምን ዝም ብላችሁ ከረማችሁ ለምትሉን ደግሞ የክርስቲያን ወንድሞችና  እህቶች ግን የግል ሕይወት እሩጫ ሆነና እንጂ መጥፋት ፈልገን እንዳልነበረ ልናወሳችሁ እንወዳለን። ሰሞኑን የምርቃት ወቅት በመሆኑም ከግራ  ቀኝ እየተሯ ሯጥን ስለነበረም የጊዜ መሻማት በዛብን ብንላችሁም እውነት ይሆናል። ባለፉት ሳምንታት ብዙ የተደረጉ ክስተቶች መኖራቸውን ስንታዘብ የሰንበቴ ብሎግ ባለቤቶችም ስማቸውን ቀይረው የተለመደ  ስድብ የሚያሰራጩበት ሌላ  ብሎግ እንደከፈቱ ለማየትም እድል ገጥሞናል። እነዚህ ሃይማኖተኛ ነን እያሉ ሃይማኖት ያልዳሰሳቸው፤ ፖለቲከኛ ነን ብለው ፖለቲካው የተምታታባቸው፤ ተናግረው የማያሳምኑ፡ የሚጽፉት እርስ በራሱ የሚጠላለፍና  የሚቃረን ደራስያን አንቱ የተባሉ ከመሰላቸው በመንደርደሪያ  ያለውን እርእስ ያስታውሱናል። ከትግራይ መወለድ ወንጀል ነው ብለው የሚያምኑ እነዚህ ግራ  የተጋቡ ብድኖች  የግለሰብን  ስም እየጠቀሱ ዘር እየቆጠሩ አገር ቤት ያለው መንግስት ዘመዶች ናቸውና ተጠንቀቁ ብለው ግለሰቦችን የመለስ ዘመዶች በመሆናቸው ብቻ ሲወነጅሉ አይተናል። አሜሪካ  እየኖሩ ያባት ወንጀል ለልጅ  ይተላለፋል ብለው አሁንም የሚያምኑ ግለሰቦችን ምን ሊቀይራቸው እንደሚችል እግዜር ይወቅ።  አገር ቤት ያለውን መንግሥት የምንጠላው በዘረኝነቱ ነው ሲሉን ይቆዩና እነእገሌ የነእገሌ ዘመዶች ናቸውና አታዳምጧቸው ብለው ይነሳሉ። ግለሰቦቹን በሚሰሩት በሚናገሩት ሳይሆን በደም ቋጠሯቸው ይወነጅላሉ። ነጠላ  ለብሶ  የሚያስቀድሰውን ሃጥያተኛ የነሱን ዘመናዊ አለባበስ የጽድቅ መመዘኛ አድርገው ያቀርባሉ። ወንድሞችና  እህቶች የሰንበቴ ተራኪዎች ሁለት ነገር መሆን አይቻልምና አንዱን ብትከተሉ መልካም ነው። የኦርቶዶክስ አማኝ የሆነ  ሁሉ ወንድም እህታችን ነው ማለት፧ ካልሆነ  የኛን ፖለቲካ  ያልተከተለ እኛ የምንለውን ያልተቀበለ ክርስቲያን አይደለም ብሎ መነሳት። መረዋ ባዲሱ ብሎግ ላይ የተጻፈውን በንቀት በመመልከት ትላንት እንዳደረገው ሊያልፈው ወስኖ  ነበር፤ ምን አልባት ስህተታቸው ቢነግሯቸው ሊቀበሉ ይችላሉ በማለት ዛሬ  ላንዴም ለሁሌም መልስ ለመስጠት ተነሳን። የግለሰብን ስም መጥራትና  መሳደብ ደግሞ መብት አይደለም የሚያስከትለው ሃላፊነትም እንዳለ መታወቅ ይኖርበታል። እነዚህ ቡድኖች ስም እየጠሩ ሊሰድቧቸው የተነሱትን ግለሰቦች  ብታስተውሉ በእርግጠኝነት እነሱ ለዚህ ቤተክርስቲያን አደረግን ከሚሉት የበለጠ አስተዋጽኦ ያደረጉ ግለሰቦች ለመሆናቸው ጥርጥር የለንም። ውድ ሰንበቴዎች ግለሰቦች ትላንት ምን ነበሩ ማለት ከመጀመራችሁ በፊት የራሳችሁን ኋላ  ብታዩ  መልካም ነው። አንድ ከማዶ የሚጣራ ሰው "ኧረ  አቶ ግሞ" ብሎ  መጣራቱን የሰማ ሌላ  ግለሰብ "ወይ እኔ በሸቀጥ እንዴት ያለ  ሥም አለ  እባካችሁ?"  አለ  ይሉ ነበርና።

ከዚህ በፊት ተደርጎ  በነበረው የኦርቶዶክስ አማንያን ስብሰባ  ላይ ተመራጭ ሆነው የተመረጡት 9 ግለሰቦች ከቦርዱ የፈቃደኝነት መልስ እንዳላገኙ ለመስማት ችለናል። ቦርዱ እራሱ ያላቌቌመውን ኮሚቴ  እንደማያውቅም መናገሩን ለመስማትም ችለናል። በእኛ በኩል እንዴው የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት እንጂ መረዋ የቦርዱ ተመራጮች ሰላምን እንደማይፈልጉ ቀደም ብሎም እናውቅ ስለነበር አልተገረምንም።   የምንገረመው ለመነጋገር ፈቃደኛ ቢሆኑ  ብቻ ነበር። የማያልቅ የሕዝብ ገንዘብ ለጠበቃ የሚያስረክቡት ተመራጮች ገንዘቡ እስከሚያልቅ እንዋጋለን ማለታቸው ስንሰማ  አዘንን እንጂ አልተገረምንም። ጠበቃቸውም ቢሆን ሁኔታዎች እየተበላሹ  ሄደው ክርክሩ እስካልቀጠለ  ድረስ ገቢ አይኖረውምና  ያሁኑ ሁኔታ እያስደሰተው ቢመጣ ምን ይገርማል? በሚመጣው  ቦርዱ በጠራው ስብሰባ  ላይም ከበጀትና  ከውጭ ተቀጣሪ የገንዘብ አጣሪ ዘገባ  ውጭ ክስን አስመልክቶ  መወያየት እንደማይቻል ከወዲሁ የቦርድ አባላቱ  እያሰጠነቀቁ መሆኑን ስንሰማ የተናገርነው ትንቢት መሆኑ ቀርቶ እውነትነቱ ተረጋገጠ  እንጂ አዲስ አልሆነብንም። ለምን ቢሉ ሰላም ከተፈጠረ  ተመራጮቹ አይኖሩምና።

በሌላ  በኩል ባሁኑ ወቅት እንደ ቦርዱ አባባል "አባላት ናቸው"  የተባሉትን አስፈርመው ስብሰባ  የጠሩት እናት እንቢ እንደተባሉ ስንሰማ "በመተዳደሪያ  ደንባችን መሰረት" የሚሉት ግለሰቦች መልሳቸው ምን ይሆን?  ብለን እራሳችንን ጠየቅን።

ካሁን በኋላ  ያለው ምርጫ አንድ ብቻ  ነው ይኸውም ነገሩ የእምነት ሳይሆን የመብት መሆኑን ተቀብሎ በፍርድ ቤት መፋለም ብቻ ነው። ይህንን ደግሞ ዶክተሮቹና ከግሪክና ከራሺያ የመጡ አማካሪዎቻቸው ከቦስተን የመጡት ደጋፊቸው ጭምር ሊረዱት ይገባል እንላለን።
ስማችሁ በብሎግ ተጠቅሶ የተወቀሳችሁ ግለሰቦች ሁሉ ደስ ሊላችሁ የሚገባው ነገር ቢኖር የሰራችሁት ፍሬ  እያፈራ መምጣቱን እውነትን የማይከተሉ ግለሰቦች ደግሞ ማታለል እንዳልቻሉ እየተገነዘቡ መሆኑን፤ አካሄዳችሁ እንዳስፈራቸው መጭው ጨለማ  እንደሆነባቸው ነው።

ውይይትን የሚፈራ  ሁሉ መሸነፉን የተቀበለ  ብቻ  ነውና።

በዚሁ አዲስ ብሎግ ላይ የቀድሞ  የኢሕአፓ አባላት የሚለው የተጠቀሰው ምን ለማለት የሆን?

ለዚህ ነው እንዴ ወይዘሮ በየነች መኮንን የምትወቅሱት?  ወቀሳችሁ  ባሳለፈችው የትግል ተመክሮ ነው ወይንስ ለቤተክርስቲያኑ ባበረከተችው ተሳትፎ ይሆን? ያለችው ሴት እሷ ብቻ ነች በማለት ነው ስሟን ያነሳነው።

ፍቅሩን ያድለን
ልቦና  ይስጣችሁ።