በሚመጣው ሐሙስ DECEMBER 9, 2010 ተቀጥሮ የነበረው የፍርድ ቤታችን ቀጠሮ በዳኛው ጥያቄ መሰረት በማግስቱ ለ 12/10/2010 በ 9:00 ሰዓት መዛወሩን ዛሬ ቀትር ላይ ለማወቅ ችለናል። ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ፈቃድ ጠይቃችሁ ሐሙስ እለት ፍርድ ቤት ለመገኘት ተዘጋጅታችሁ የነበራችሁ በሙሉ በተፈጠረው የቀጠሮ መጋጨት ከልብ እንደምታዝኑ ይገባናል። አሁንም የቻላችሁ ዓርብ እለት በተባለው ሰዓት በፍርድ ቤት በመገኘት ለማዳመጥ ብትሞክሩ ምሥጋናችን የላቀ ነው።
"ሰው ያስባል እግዚአብሔር ይፈጽማል"