ሰሞኑን ያጋጠመን ሐዘን በጣም የከፋ ነው። ሐዘኑን የከፋ የሚያደርገው ቆመን ያዋለድነውን ማቲው ሃይሌን እድገቱን ሳይጨርስ ቆመን ለመቅበር በመነሳታችን ነው። ማቲውን ስናስብ ልጃችን ነውና ልጆቻችን ይታዩናል። ማቲውን ስናስብ የዓለማዊ ሽኩቻችን የእድሜ ገደብ እንደሌለን አድርገን የምናስበውን እንደገና እንድንመረምር ይገፋናል። ስለሆነም መረዋ የዚህን ከመካከላችን የተወለደውን በጨቅላ እድሜ የተቀጨውን ወጣት ዜና እረፍት ምክንያት በማድረግ አስከሬኑ ግብአተ መሬት ሳያርፍ ምንም አይነት እትምት ላለማውጣት ወስኗል።
ለማቲው ደስታዊ ዘላለማዊ እረፍትን
ለቤተሰቡ መጽናናትን እንመኛለን
በዚህ አጋጣሚ በነገው እለት በቅዱስ ሚካኤል አስተባባሪ ኮሚቴ ተጠርቶ የነበረው የምእመናን ስብሰባም በሐዘኑ ምክንያት ለሚመጣው ወር አጋማሽ መተላለፉን ከኮሚቴው የወጣው መግለጫ አስታውቋል። በበለጠ ለመረዳት የምትፈልጉ የኮሚቴውን ጦማር በመጎብኘት መረዳት ትችላላችሁ።
የሳምንት ሰው ይበለን